ስለ እኛ

ስለ ሥነ ጤና

በየትኛውም ሥፍራ እና ሆኔታ ውስጥ ሆነው በጥራት የቀረበ የሕክምና ትምህርት ለማግኘት ይፈልጋሉ?

መልሶዎት አዎ ከሆነ  ድረ ገጻችን በየትኛውም የዓለም ክፍል ውስጥ ሆነው ስለጤና እና የጤና ሳይንስ ለመማር ለሚፈለጉ በየትኛውም የዕድሜ እና የትምህርት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰዎች እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ስለሆነ ዛሬውኑ ቤተሰብ በመሆን የጤና ሳይንስ ዕውቀቶን በማሳደግ መተኪያ የሌለውን የእርሶዎን እና የቤተሰቦዎን ጤና በሳይንሳዊ ዕውቀት ላይ ተመርኮዘው መንከባከብ ይጀምሩ። ። የሕክምና ሳይነስ ዕወቅቱን ለማሳድግ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው፣  ሙያቸውን በዕውቀት ለማሳደግ ለሚፈልጉ በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ፣ የጤና ትምህርት ለሚያጠኑ ተማሪዎች እንዲሁም ወደፊት የጤና ሳይንስ ለማጥናት ለሚፈልጉ ሰዎች  የሚያስፈልጋቸውን ዕውቅት እንዲያጋኙ የተለያዩ ትምህርቶችን እና ስልጠናዎችን አዘጋጅተናል።

ከዋና ዋና የሕክምና እና የጤና ሳይንስ ጽንሰ ሐሳቦች ጀምሮ እስከ ልዩ ልዩ የሕክምና ዘርፎች ድረስ በጥራት እና በጥልቀት የተዘጋጁ ትምህርቶችን እና ስልጠናዎችን እንሰጣለን።  ዛሬውኑ  በመመዝገብ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ እውቀቶን በማሳደግ  በዋጋ የማይተመነውን የርስዎን እና የቤተሰብዎን ጤና ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ  የሚያስችልዎትን በቂ ዕውቀት ይሸምቱ። 

የምናቀርባቸው ትምህርቶች

ድረ ገጻችንን ማሰስ ቀላል ነው፦ ከአስተማሪዎችና ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ቅርርብ ለመፍጠር የሚያስችልና የተጠቃሚ የሚመች ነው።
አለም አቀፍ ተሞክሮን እና ጥራትን ያማከለ

በሕክምናው ዘርፍ በአለም አቅፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ ፣  ግዜያቸውን የጠብቁ እንዲሁም በሳይንሳዊ መንገዶች ተፈትነው ያለፉ ዕውቀቶችን ብቻ ለማስጨበጥ ጠንክረን እንሰራልን። በአለም ጤና ድርጅት እና በብዙ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ የጤና ማኅከላት የሚተገብሩ የሕክምና እና የምክር ሃሳቦችን በማካፈል ተማሪዎች እና ስልጣኞች ጥራቱን የጠበቀ የጤና እና ሕክምና ሳይንስ ዕውቀት እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት እናደርጋልን። 

የተሟላ የጤና እና የሕክምና ሳይንስ ትምህርቶች

በድረ ገጻችን ላይ እውቀት ፣ ክህሎትና ችሎታዎት እንዲጎለብት የሚያስችሉ በጥንቃቄ የተመረጡ የጤና እና የሕክምና ሳይንስ ዘርፎችን በመምረጥ አጠቃላይ የሆነ ዕወቅት የሚያገኙበትን መንገድ ፈጥራናል። በሰውነት ውስጥ የሚገኙ የሰውነት ሥርዓቶችን (body systems) መሰረት ባደረገ መልኩ የተደራጀው ትምህርት እና ስልጠና፣  ስለአጠቃላይ የጤና እና የሕክምና ሳይንስ እንዲሁም በተወሰነ ወይም በሚፈልጉት የሰውነት ሥርዓት ላይ በማተኮር የሚያስፈልጎትን ዕውቀት እንዲያገኙ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። 

ዕውቀት እና ልምድ ያላቸው አስተማሪዎች

የምንሰጠውን ትምህርት እና ስልጠና ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ለማረጋገጥ ሁሉም ኮርሶቻችን ተዘጋጅተው የሚቀርቡት ዕውቀት እና ልምድ ባላቸው የሕክምና ባለሙያዎች እና  አስተማሪዎች ነው። ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን በማረጋገጥ ግዜው የሚጠይቀውን የጤና እና የሕክምና ሳይንስ እውቀት አዘጋጅተን እናቀርባለን። 

ለመማር በቀላሉ ይመዝገቡ

የጤና እና የሕክምና ሳይንስ ዕውቀትዎን በማሳደግ መተኪያ የሌለውን የእርስዎን እና የቤተስብዎን ጤና በዕውቀት ላይ በመመርኮዝ ለመንከባከብ እና ለመጠበቅ የሚረዳዎትን ዕውቀት እና ልምድ ለመሸመት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ዛረውኑ በመወስን ቤተሰብ ይሆኑ። ድረ ገጻችንን ዛሬ በመቀላቀል የጤና እና የሕክምና ሳይንስ አለምን ይቀላቀሉ። ስለጤናዎ በዕውቀት ላይ ተመርኮዘው ይወስኑ።