የኩላሊት ጠጠር አፈጣጠር ፣ ዓይነቶች እና ሕክምና (Renal stones: Development, types and Treatment)

Uncategorized
Wishlist Share
Share Course
Page Link
Share On Social Media

About Course

ይህ ትምህርት የተዘጋጀው በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ የሚፈጠሩ ጠጠሮች  አፈጣጠር ሂደት እና  የጠጠር ዓይነቶች እንዲሁም  በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ ለሚፈጠሩ ጠጠሮች ሕክምና በጥቅም ላይ ስለሚውሉ የሕክምና መንገዶች አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ታስቦ ነው። የዚህ ትምህርት ዋና አላማ በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ ስለሚፈጠሩ የተለያዩ ዓይነት ጠጠሮች ፣ ለጠጠር መፈጠር አጋላጭ ሊሆኑ ስለሚችሉ ሁኔታዎች፣ ከጠጠር መፈጠር ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች ፣ ጠጠር መፈጠሩን ለማወቅ ስለሚረዱ የምርመራ መንገዶች  እንዲሁም ለሚፈጠሩ ጠጠሮች በጥቅም ላይ  ሊወሉ ስለሚችሉ የህክምና አማራጮች እና እና ለጠጠር መፈጠር የመከላኪያ  መንገዶች እውቀትን እና ግንዛቤን በማዳበር በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ የሚፈጠር ጠጠርን በተመለከተ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔን መስጠት የሚያስችል ግንዛቤ እንዲፈጠር ማገዝ ነው።  

     በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች አላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም  እውቀት በሽታን ለማወቅ ወይም በሽታን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ህከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም። በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም በሽታው እንደተፈጠረ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት ወደሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በፍጥነት በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር መመካከር እና ተገቢውን ሕክምና ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን እንመክራለን። 

      በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በመቀበል እንዲተገብሩ እናሳስባለን። 

Show More

Course Content

1. የሰውነት ፈሳሽ መጠን እና ይዘት (Body fluids)

  • .1. የሰውነት ፈሳሽ መጠን እና ይዘት (Body fluids) 
    00:00
  • 1.1. የሰውነት ፈሳሽ የሚገኝባቸው የሰውነት ክፍሎች (Body fluid compartments)
    00:00
  • 1.2. በሰውነት ፈሳሽ ውስጥ የሚገኙ ሟሚ ነገሮች ( Body fluid solutes)
    00:00
  • 1.3. የሰውነት ፈሳሽ ተነጻጻሪ የውኃ እና የሟሚ ነገሮች መጠን (Osmolarity)
    00:00

2. የሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች (Urinary System)

3. የኩላሊት ክፍሎች (Kidney parts)

4. የኩላሊት የደም ዝውውር ሥርዓት (Renal Blood Circulation)

5. የኩላሊት ተግባራት (Kidney function)

6, የኩላሊት የማጣራት ተግባር (Kidney’s filtration function)

7, የኔፍሮን ቧንቧ (Nephrons)

8. በሰውነት ፈሳሽ ውስጥ የሚገኙ ኤሌክትሮላይቶችን ይዘት ማመጣጠን (Balancing electrolytes)

9. የሽንት መጠን እና ይዘት መለያየት (Urine concentration)

10. የኩላሊት የደም ግፊት መጠንን የመቆጣጠር ተግባር (Controlling blood pressure)

11, በሰውነት ፈሳሽ ውስጥ የሚኖረውን የአሲድ-ቤዝ ማመጣጠን (Acid-base balance)

12. በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ የሚፈጠሩ ጠጠሮች  (Renal stones / Urolithiasis)

13. በኩላሊት እና በሌሎች የሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ የሚፈጠሩ የጠጠር ዓይነቶች (Types of Urolithiasis) 

14. በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ ከሚፈጠሩ ጠጠሮች ጋር የሚታዩ ምልክቶች እና የስሜት ለውጦች (signs and symptoms)

15.  በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ የሚፈጠሩ ጠጠሮችን ለመለየት የሚደርጉ ምርመራዎች (Diagnostics)

16. በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ ለሚፈጠሩ ጠጠሮች የሚሰጡ ሕክምናዎች (Treatment) 

17. በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ ጠጠር የመፈጠር ዕድልን ለመቀነስ የሚደረጉ የመከላከያ መንገዶች (Prevention) 

ማጣቀሻ መጽሃፍት እና ድህረ ገጾች (Reference)