በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
በሥነ ጤና ትምህርት እና ሥልጠና ማዕክል ድህረ ገጽ ውስጥ በጥራት ፣ በትክክለኛ መረጃ እና በቀላል አቀራረብ የተዘጋጁ መሰረታዊ የጤና እና የሕክምና ሳይንስ ትምህርቶችን ያገኛሉ። ከመሰረታዊ የሰውነት ሥርዓት አስራር እና ተግባር (Physiology) ጀምሮ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ሊከሰቱ ስለሚችሉ የጤና ችግሮች መንስሄዎች (Etiologies) ፣ አጋላጭ ሁኔታዎች (Risk factors) ፣ ከጤና ችግሩ ጋር በተገናኘ ስለሚከሰቱ ምልክቶች እና ለውጦች (Signs and symptoms) ፣ የጤና ችግር መከሰቱን ለማወቅ የሚረዱ የምርመራ መንገዶች (Diagnostics) ፣ የጤና ችግሩን ለማከም ወይም ከጤና ችግሩ ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ ምልክቶችነ እና ለውጦችን ለመቆጣጠር የሚረዱ የሕክምና መንገዶችን (Treatment) እንዲሁም የጤና ችግሮችን ለመከላከል የሚረዱ መንገዶችን (Prevention) በጥልቀት የምንመለከት ይሆናል።
በሥነ ጤና የትምህርት እና ስልጠና ማዕከል የሚዘጋጁ የጤና እና የሕክምና ሳይንስ ትምህርቶች ለተለያዩ የማኅብረሰብ ክፍሎች ጠቃሚ እንዲሆኑ የተዘጋጁ ናቸው። እነዚህ ትምህርቶች በትክክለኛ እውቀት ላይ ተመስረተው ጤናቸውን ለመጠብቅ ለሚፈልጉ ፣ ለተለያዩ የጤና ችግሮች ሕክምና ለሚወስዱ ሰዎች፣ ከተለያዩ የጤና ችግሮች ጋር የሚኖሩ ሰዎችን ለሚያስታምሙ ሰዎች ፣ ለመካከለኛ ደረጃ የጤና ባለሙያዎች ፣ የጤና ትምሀርት በመወሰድ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ፣ ወደ ፊት የጤና እና የሕክምና ሳይንስ ትምህርት ለማጥናት ለሚፈልጉ ተማሪዎች እንዲሁም ማንኛውም ስለ ጤና እና ሕክምና ሳይንስ ለመማር እና ለማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች በሙሉ ጠቃሚ እንዲሆን ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው።
በሥነ ጤና ትምህርት እና ሥልጠና ማዕከል ተዘጋጅተው የቀረቡ ትምህርቶችን በየትኛውም ሥፍራ ሆነው ፣ በማንኛውም ግዜ በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ኮርሶች የሚለውን መስፈንጠሪያ በመጫን ከተዘጋጁ አማራጭ ትምህርቶች ውስጥ የሚፈልጉትን ኮርስ በመምረጥ የሚፈልጉትን ትምህርት ማግኘት ይችላሉ።
የመረጡትን ትምህርት በፈለጉት ጊዜ ፣ በትኛውም ሁኔታ እና አካባቢ ውስጥ ሆነው መከታተል ይችላሉ።
ኮርሶችን ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ትምህርቶቹ የሚዘጁት እና የሚሰጡት የርጅም ግዜ የጤና እና የሕክምና ሳይንስ እውቀት እና ልምድ ባላቸው የሕክምና ባለሙያዎችና አስተማሪዎች ነው። የትምህርቶቹ ዝግጅት በየግዜው ክልሳ የሚደረግበት ስለሆነ በየግዜው ክሚቀያየረው የጤና እና የሕክምና ሳይንስ ጋር አብረው እንዲራመዱ ሆነው የሚዘጋጁ ናቸው። የሚዘጋጁት ትምህርቶች መሰረታዊ የስወነት አሰራርን እና ተግባርን ከማስተማር ስለሚጀምሩ የተለያዩ የጤና ችግሮችን አፈጣጠር እና ከጤና ችግሮቹ ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶችን ለመረዳት ቀላል መንገድን ይፈጠራል።
ሥነ ጤና የትምህርት እና ስልጠና ማዕከል ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ በኦሮሚኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች የጤና እና የሕክምና ሳይንስ ኮርሶችን ለማዘጋጀት እቅድ አለው።