በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ክፍሎች አፈጣጠር ሂደት ላይ ከሚከሰት እክል ወይም ጉድለት ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ( Congenital heart diseases)
About Course
ይህ ትምህርት የተዘጋጀው በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ክፍሎች አፈጣጠር ሂደት ላይ ከሚከሰት እክል ወይም ጉድለት ጋር በተገናኘ ስለሚፈጠሩ የጤና ችግሮች (Congenital heart diseases) በቂ አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ታስቦ ነው። በዚህ ትምህርት በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ክፍሎች አፈጣጠር ሂደት ላይ ከሚከሰት እክል ወይም ጉድለት ጋር በተገናኘ ለሚፈጠሩ የጤና ችግሮች (Congenital heart diseases) አጋላጭ ሁኔታዎች (risk factors) ፣ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ክፍሎች አፈጣጠር ሂደት ላይ ከሚከሰት እክል ወይም ጉድለት ጋር በተገናኘ ስለሚፈጠሩ የጤና ችግር ዓይነቶች (types of congenital heart diseases) ፣ ከጤና ችግሮቹ ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች (signs and symptoms)፣ የጤና ችግሮቹን ተከትሎ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች (signs and symptoms) ፣ የጤና ችግሮቹ መከሰታቸውን ለማወቅ ስለሚረዱ የምርመራ መንገዶች diagnosis) እንዲሁም በጥቅም ላይ ሊውሉ ስለሚችሉ የሕክምና መንገዶች (treatment) በጥልቀት ይቀርባል።
በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች አላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም እውቀት በሽታን ለማወቅ ወይም በሽታን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ሕከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም። በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም በሽታው እንደተፈጠረ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት በሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር በሚደርግ ምክከር ተገቢውን ምርመራ እና ሕክምና ማግ ኘት አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን።
በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና መቀበል እና መተግበር አስፈላአጊ ይሆናል።
Course Content
1. የልብ እና የደም ቧንቢ ሥርዓት (Cardiovascular system)
-
1. የልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት (Cardiovascular system)
00:00 -
1.1. በልብ እና በሳንባ መካከል የሚከናወን የደም ዝውውር ወይም የፑልሞናሪ የደም ዝውውር (Pulmonary circulation)
12:00 -
1.2. በልብ እና ከሳንባ ውጭ በተቀረው የሰውነት ክፍሎች መካከል የሚከናወን የደም ዝውውር ሥርዓት (Systemic circulation)
00:00