የሚጥል በሽታ (Epilipsy)
About Course
ይህ ትምህርት የተዘጋጀው ስለየሚጥል በሽታ (Epilepsy) አጠቃላይ አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ታስቦ ነው። የዚህ ትምህርት ዋና አላማ ስለየሚጥል በሽታ በሽታ ምንነት (Epilepsy) ፣ ለሚጥል በሽታ መፈጠር መንስሄ ወይም አጋላጭ ሊሆኑ ስለሚችሉ ሁኔታዎች (risk factors) ፣ ስለየሚጥል በሽታ ዓይነቶች (types of epilepsy) ፣ የሚጥል በሽታ መፈጠሩን ለማወቅ ስለሚረዱ የምርመራ መንገዶች (Diagnostics) እንዲሁም ከሚጥል በሽታ ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ ምልክቶችን እና ለውጦችን ለመቆጣጠር ስለሚረዱ የሕክምና መንገዶች (treatment) በቂ እወቀትን በማስረፅ በእውቀት ላይ ተመስርቶ የምክር እና የሕክምና ድጋፍ የሚጠይቅ ማዕብረስብ መፈጠር ነው። ይህ ትምህርት በጽሁፍ እና በቪዲዩ መልክ ተዘጋጅቶ በፈለጉት አማራጭ መጠቀም እንዲቻል ሆኖ የተዘጋጀ ነው።
በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች ዓላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም እውቀት የእህምሮ የጤና ችግሮችን ለማወቅ ወይም የአህምሮ የጤና ችግር መከሰቱን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ሕከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም። በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም እንደተፈጠሩ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት ወደ ሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር መመካከር እና አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት ተገቢ ይሆናል።
በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ አንባቢው ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና እንዲቀበል እንዲሁም እንዲተገብር እናሳስባለን።
Course Content
1. የሚጥል በሽታ (Epilepsy)
-
1. የሚጥል በሽታ (Epilepsy)
00:00