የልብ ድካም በሽታ (Heart failure)

Uncategorized
Wishlist Share
Share Course
Page Link
Share On Social Media

About Course

ይህ ትምህርት የተዘጋጀው ስለ የልብ ድካም በሽታ (Heart failure) በቂ አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ታስቦ ነው።  በዚህ ትምህርት ስለ የልብ ድካም በሽታ (Heart failure)፣ ስለ የልብ ድካም በሽታ ዓይነቶች (Types of Heart failure )፣ ከልብ ድካም በሽታ ጋር በተገናኘ ስለሚከሰቱ ምልክቶች እና ለውጦች (signs and symptoms) ፣ የልብ ድካም በሽታ መፈጠሩን ለመለየት ስለሚረዱ የምርመራ መንገዶች (diagnostics) እንዲሁም የልብ በሽታን ለማከም ስለሚረዱ የሕክምና መንገዶች (Treatment) ጥልቀት ያለው ትምህርት ለመስጠት ነው። 

     በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች አላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም  እውቀት በሽታን ለማወቅ ወይም በሽታን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ሕከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም።  በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም በሽታው እንደተፈጠረ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት በሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር በሚደርግ ምክከር ተገቢውን ምርመራ እና ሕክምና ማግ ኘት አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን። 

      በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና መቀበል እና መተግበር አስፈላአጊ ይሆናል። 

Show More

Course Content

1. የልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት (Cardiovascular system) 

  • 1. የልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት (Cardiovascular system) 
    00:00
  • 1.1. በልብ እና በሳንባ መካከል የሚከናወን የደም ዝውውር ወይም የፑልሞናሪ የደም ዝውውር (Pulmonary circulation) 
    00:00
  • 1.2. በልብ እና ከሳንባ ውጭ በተቀረው የሰውነት ክፍሎች መካከል የሚከናወን የደም ዝውውር ሥርዓት (Systemic circulation)

2. ልብ እና የልብ ክፍሎች (Heart Parts) 

3. የልብ የኤሌክትሪክ እንቀሰቃሴ ሥርዓት  እና ተኮማታሪ ሴሎች (Electrical system and Myocardial cells) 

4.  የልብ ጡንቻ የመኮማተር እና የመሥራት አቅም (Myocardial contraction) 

5. የደም ቧንቧዎች (Blood vessels) 

6. በደም ዝውወር ሥርዓት ውስጥ የደም ፍሰት እና የደም ዝውውር ፍጥነት (Blood flow and velocity) 

7. በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ ከሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች (Signs and Symptoms) 

8. የልብ ድካም በሽታ  (Heart failure) 

9. ከልብ ከሚረጨው የደም መጠን ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ ድካም (High / Low output heart failure) 

10. ከቬንትሪክል መኮማተር እና መለጠጥ ብቃት ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ ድካም በሽታ (Systolic / Diastolic heart failure)  

11. በቀኝ ወይም በግራ የልብ ክፍል ውስጥ ከሚፈጠር ጉዳት ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ ድካም (Right / Left sided heart failure) 

12. በቬንትሪክል ውስጥ ከሚገባው ደም ውስጥ በየአንድ አንዱ የቬንትሪክል መኮማተር ወቅት ከቬንትሪክል የሚረጨው የደም መጠን (Left Ventricular Ejection Fraction / LVEF)

13. የልብ ድካም መንስሄዎች (Causes of Heart failure)

14. ከልብ ድካም በሽታ ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች (Signs and symptoms) 

15. የልብ ድካም በሽታ መፈጠሩን ለማወቅ የሚረዱ የምርመራ መንገዶች (Diagnostics) 

16. ለልብ ድካም በሽታ ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ ምልክቶችን ለመቆጣጠር የሚረዱ የሕክምና መንገዶች (Treatment)

ማጣቀሻ መጽሃፍት እና ድህረ ገጾች (References)