በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases) 

Uncategorized
Wishlist Share
Share Course
Page Link
Share On Social Media

About Course

ይህ ትምህርት የተዘጋጀው በልብ በሮች ላይ ስለሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases) በቂ አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ታስቦ ነው።  በዚህ ትምህርት ስለ ልብ በሮች ዓይነት (Heart valves)፣ ስለ ልብ በሮች ተግባር (function)፣ በልብ በሮች ላይ ስለሚከሰቱ የተለያዩ የጤና ችግሮች (valvular diseases)፣ በልብ በሮች ላይ ከሚከሰቱ የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ ስለሚከሰቱ ምልክቶች እና ለውጦች (signs and symptoms) ፣ በልብ በሮችን ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን ለመለየት ስለሚረዱ የምርመራ መንገዶች (diagnostics) እንዲሁም በልብ በሮች ላይ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን ለማከም ስለሚረዱ የሕክምና መንገዶች (Treatment) ጥልቀት ያለው ትምህርት ለመስጠት ነው። 

     በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች አላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም  እውቀት በሽታን ለማወቅ ወይም በሽታን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ሕከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም።  በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም በሽታው እንደተፈጠረ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት በሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር በሚደርግ ምክከር ተገቢውን ምርመራ እና ሕክምና ማግ ኘት አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን። 

      በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና መቀበል እና መተግበር አስፈላአጊ ይሆናል። 

Show More

Course Content

1. የልብ እና የደም ቧንቢ ሥርዓት (Cardiovascular system)

  • 1. የልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት (Cardiovascular system) 
    00:00
  • 1.1. በልብ እና በሳንባ መካከል የሚከናወን የደም ዝውውር ወይም የፑልሞናሪ የደም ዝውውር (Pulmonary circulation) 
    00:00
  • 1.2. በልብ እና ከሳንባ ውጭ በተቀረው የሰውነት ክፍሎች መካከል የሚከናወን የደም ዝውውር ሥርዓት (Systemic circulation)
    00:00

2. ልብ እና የልብ ክፍሎች (Heart Parts) 

3. የልብ የኤሌክትሪክ እንቀሰቃሴ ሥርዓት  እና ተኮማታሪ ሴሎች (Electrical system and Myocardial cells) 

4.  የልብ ጡንቻ የመኮማተር እና የመሥራት አቅም (Myocardial contraction) 

5. የደም ቧንቧዎች (Blood vessels) 

6. በደም ዝውወር ሥርዓት ውስጥ የደም ፍሰት እና የደም ዝውውር ፍጥነት (Blood flow and velocity) 

7. በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ለማወቅ የሚረዱ የምርመራ ዘዴዎች (Diagnostics)

8. በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ ከሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች (Signs and Symptoms) 

9. በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases) 

10. ከስትሪፕቶኮካል ባክቴሪያ ኢንፌክሽን ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ የጤና ችግር (Rheumatic heart disease) 

16. በልብ ውስጥ የሚከሰት ኢንፌክሽን  (Infective Endocarditis)

11. በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጉዳት ዓይነቶች (Types of valvular heart diseases) 

12. በሚትራል በር ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ  የልብ የጤና ችግሮች (Mitral valve problems)

13. በትራይካስፒድ በር ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Tricuspid valve problems) 

14. በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Aortic valve problems) 

15. በፑልሞናሪ በር ላይ የሚክሰቱ የጤና ችግሮች (Pulmonary valve problems) 

ማጣቀሻ መጽሃፍት እና ድህረ ገጾች (Reference)