የአህምሮ ጤና እና የአህምሮ የጤና ችግሮች (Mental Health and Mental Illnesses)
About Course
አንደ የአለም ጤና ድርጀት (World Health Organization / WHO) መረጃ መሰረት በአለም ውስጥ በቁጥር ወደ አንድ ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በተለያዩ ደረጃዎች ላይ ከሚገኙ የአህምሮ የጤና ችግሮች ጋር እንዲሚኖሩ ይታመናል። በአሜሪካ ሀገር ውስጥ ከሚኖሩ ከአምስት አዋቂ ሰዎች ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከአህምሮ የጤና ችግር ጋር እንደሚኖር የተለያዩ ጥናቶች አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በድህነት ፣ በጦርነት በሥራ አጥነት እንዲሁም በጎስቁልና እና በስደት ህይወት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ለአህምሮ የጤና ችግሮች የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።
ይህ የአህምሮ ጤና እና የአህምሮ የጤና ችግሮች (Mental health and Mental Illnesses) ትምህርት የተዘጋጀው ስለ የአህምሮ ጤና እንዲሁም የአህምሮ የጤና ችግሮች አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ታስቦ ነው። የዚህ ትምህርት ዋና አላማ ስለ የእህምሮ ጤና የሚኖር አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ማዳበር እንዲሁም ሰለ አህምሮ የጤና ችግሮች በቂ እወቀትን በማስረፅ የአህምሮ የጤና ቸግሮችን የሚከላከል እንዲሁም አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት በእውቀት ላይ ተመስርቶ የምክር እና የሕክምና ድጋፍ የሚጠይቅ ማዕብረስብ መፈጠር ነው። ይህ ትምህርት በጽሁፍ እና በቪዲዩ መልክ ተዘጋጅቶ በፈለጉት አማራጭ መጠቀም እንዲቻል ሆኖ የተዘጋጀ ነው።
በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች ዓላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም እውቀት የእህምሮ የጤና ችግሮችን ለማወቅ ወይም የአህምሮ የጤና ችግር መከሰቱን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ሕከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም። በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም እንደተፈጠሩ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት ወደ ሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር መመካከር እና አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት ተገቢ ይሆናል።
በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ አንባቢው ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና እንዲቀበል እንዲሁም እንዲተገብር እናሳስባለን።
Course Content
ምዕራፍ አንድ ፡ የአህምሮ ጤና (Mental health) እና የአህምሮ የጤና ችግሮች (Mental illness)
-
1. የአህምሮ ጤና እና የአህምሮ የጤና ችግሮች (Mental health & Mental illness)
10:15 -
1.1. የአህምሮ ጤና (Mental health)
05:42 -
1.2. የአህምሮ የጤና ችግሮች (Mental illness)
00:00 -
1.3. የአህምሮ የጤና ችግር መንስሄ ወይም አጋላጭ ሁኔታዎች (Etiologies or risk factors)
00:00 -
1.4. የአንጎል ክፍሎች እና ተግባራቸው (Brain parts and function)
09:06 -
1.4.1. የፊተኛው የሰረበረም ኮርቲክሰ ክፍል (Frontal cerebral cortex)
00:00 -
1.4.2. የፓሪይታል የሰረበረም ኮርቲክስ ክፍሎች (Parietal cerebral cortex)
00:00 -
1.4.3. የቴምፖራል የሰረበረም ኮርቲክስ ክፍሎች (Right and left temporal cerebral cortex)
00:00 -
1.4.4. የኋለኛው የአንጎል ኮርቲክስ ክፍል (Occipital cerebral cortex)
00:00 -
1.5. የሊምቢክ ሥርዓት (Limbic system)
00:00 -
1.5.1. ታላመስ (Thalamus)
00:00 -
1.5.2. ሃይፖታላመስ (hypothalamus):
-
1.5.3. አሚግዳላ (Amygdala)
00:00 -
1.5.4. ኢፖካምፐስ (Hippocampus)
00:00 -
1.6. የነርቭ ሥርዓት መልዕክት አመላላሽ ኬሚካሎች መጠን መዛባት (Neurotransmitters imbalance)
00:00 -
1.7. የአህምሮ የጤና ችግሮችን ለማወቅ የሚደረጉ ምርመራዎች (Diagnostics)
00:00