የጭንቀት የአህምሮ የጤና ችግሮች (Anxiety disorders) 

Uncategorized
Wishlist Share
Share Course
Page Link
Share On Social Media

About Course

ይህ ትምህርት የተዘጋጀው ስለየጭንቀት የአህምሮ የጤና ችግሮች (Anxiety disorders) አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ታስቦ ነው። የዚህ ትምህርት ዋና አላማ ስለ የእህምሮ ጤና በተለይም ስለ የጭንቀት የአህምሮ የጤና ችግር ዓይነቶች (Types of Anxiety disorders) ፣ ከጭንቀት የአህምሮ የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ ስለሚከሰቱ ምልክቶች እና ለውጦች (sings and symptoms)፣  የአህምሮ የጤና ችግር መከሰቱን ለማወቅ ስለሚረዱ የምርመራ መንገዶች (diagnostics)  እንዲሁም ከጭንቀት የአህሞሮ የጤና ችግር ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ ምልክቶችን እና ለውጦችን ለመቆጣጠር ስለሚረዱ የሕክምና መንገዶች (treatment) የሚኖር አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ማዳበር እንዲሁም ሰለ አህምሮ የጤና ችግሮች በቂ እወቀትን በማስረፅ የአህምሮ የጤና ቸግሮችን የሚከላከል እና አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት በእውቀት ላይ ተመስርቶ የምክር እና የሕክምና ድጋፍ የሚጠይቅ ማዕብረስብ መፈጠር ነው።  

ይህ ትምህርት በጽሁፍ እና በቪዲዩ መልክ ተዘጋጅቶ በፈለጉት አማራጭ መጠቀም እንዲቻል ሆኖ የተዘጋጀ ነው። 

    በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች ዓላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም  እውቀት የእህምሮ የጤና ችግሮችን ለማወቅ ወይም የአህምሮ የጤና ችግር መከሰቱን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ሕከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም።  በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም እንደተፈጠሩ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት ወደ ሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር መመካከር እና አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት ተገቢ ይሆናል።       

        በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ አንባቢው ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና  እንዲቀበል እንዲሁም እንዲተገብር እናሳስባለን። 

Show More

Course Content

1. የአህምሮ ጤና (Mental health) እና የአህምሮ የጤና ችግሮች (Mental illness)

  • 1. የአህምሮ ጤና (Mental health) እና የአህምሮ የጤና ችግሮች (Mental illness) 
    00:00
  • 1.1.  የአህምሮ ጤና (Mental health)
    00:00
  • 1.2.  የአህምሮ የጤና ችግሮች (Mental illness) 
    00:00

2. የአህምሮ የጤና ችግር መንስሄ ወይም አጋላጭ ሁኔታዎች (Etiologies or risk factors) 

3. የአንጎል የተለያዩ ክፍሎች እና ተግባራቸው (Brain parts and function) 

4. የነርቭ ሥርዓት መልዕክት አመላላሽ  ኬሚካሎች  (Neurotransmitters)

5. የአህምሮ የጤና ችግሮችን ለማወቅ የሚደረጉ ምርመራዎች (Diagnosis)

6. የባህሪ ወይም የፀባይ  ለውጥ የሚያስከትሉ  የአህምሮ የጤና ችግሮች (Mood disorders) 

7. የጭንቀት የአህምሮ የጤና ችግሮች (Anxiety disorders) 

8. የጭንቀት የእህምሮ የጤና ችግር ዓይነቶች እና መንሰሄዎቻቸው (Etiology and risk factors of Anxiety) 

9. ሳይጠበቅ እና በተደጋጋሚ የሚከሰት ከፍተኛ የሆነ የስሜት መረበሽ ወይም መጨናነቅ (Panic disorder) 

10. እንድን ነገር ወይም ሁኔታን በከፍተኛ መጠን ወይም በተጋነነ ደረጃ መፍራት (Specific Phobia) 

11.  ለማምለጥ ወይም እርዳታ ለማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ  ውስጥ ሲገኙ በከፍተኛ ፍርኃት  ወይም ጭንቀት ውስጥ መግባት (Agoraphobia)

12. በአንድ ግዜ ስለተለያዩ ነገሮች በማሰብ በከፍተኛ ሥጋት ፣ ፍርኃት ወይም ጭንቀት ውስጥ መገባት (Generalized anxiety disorder)

13. ልጆች በተወሰነ ሁኔታ ውስጥ ወይም ቦታ ላይ በሚሆኑበት ባልተለመደ መልኩ ፍርኃት ውስጥ መግባት እና መናገር አለመቻል (Selective mutism) 

14. ሰዎች በተሰበሰቡበት ወይም በቁጥር የበዙ ሰዎች በሚገኙባቸው ሥፍራዎች ውስጥ መገኘትን ተከትሎ የሚፈጠር ከፍተኛ የሆን ፍርኃት  ወይም ሥጋት  (Social anxiety disorder) 

15. ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ወይም ከአሳዳጊዎቻቸው በሚለዩበት ወይም እንዲለዩ በሚደረጉበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ የፍርኃት ወይም የጭንቅት ስሜት መሰማት (Separation anxiety disorder) 

16. ከፍረኃት ወይም ጭንቀት የተነሳ የአተነፋፈስ ፍጥነት እንዲጨምር የሚያደርግ የጤና ችግር (Hyperventilation syndrome)

17. የአድንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶችን ወይም የተለያዩ የጤና ችግሮችን ለማከም የሚረዱ መድኃኒቶችን ከመጠቀም ጋር በተገናኘ የሚከሰት ፍርኃት ወይም ጭንቀት (Substance / Medication induced anxiety disorder) (copy)

18. ከሌሎች የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ የሚከሰት የጭንቀት የጤና ችግር  (Anxiety due to another medical condition) 

19. በሕይወት ወስጥ ከሚያጋጥሙ አደጋዎች ወይም መጥፎ አጋጣሚዎች ጋር በተገናኘ የሚከሰት ጭንቀት (Posttraumatic stress disorder / PTSD)

20. ማጠቃሻ መጽሃፍት እና ድህረገጾች (References)