የሚጥል በሽታ (Epilipsy)

Uncategorized
Wishlist Share
Share Course
Page Link
Share On Social Media

About Course

ይህ  ትምህርት የተዘጋጀው ስለየሚጥል በሽታ (Epilepsy) አጠቃላይ አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ታስቦ ነው። የዚህ ትምህርት ዋና አላማ ስለየሚጥል በሽታ በሽታ ምንነት (Epilepsy) ፣  ለሚጥል በሽታ መፈጠር መንስሄ ወይም አጋላጭ ሊሆኑ ስለሚችሉ ሁኔታዎች (risk factors) ፣ ስለየሚጥል በሽታ ዓይነቶች (types of epilepsy) ፣ የሚጥል በሽታ መፈጠሩን ለማወቅ ስለሚረዱ የምርመራ መንገዶች (Diagnostics) እንዲሁም ከሚጥል በሽታ ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ ምልክቶችን እና ለውጦችን ለመቆጣጠር ስለሚረዱ የሕክምና መንገዶች (treatment) በቂ እወቀትን በማስረፅ በእውቀት ላይ ተመስርቶ የምክር እና የሕክምና ድጋፍ የሚጠይቅ ማዕብረስብ መፈጠር ነው።  ይህ ትምህርት በጽሁፍ እና በቪዲዩ መልክ ተዘጋጅቶ በፈለጉት አማራጭ መጠቀም እንዲቻል ሆኖ የተዘጋጀ ነው። 

    በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች ዓላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም  እውቀት የእህምሮ የጤና ችግሮችን ለማወቅ ወይም የአህምሮ የጤና ችግር መከሰቱን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ሕከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም።  በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም እንደተፈጠሩ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት ወደ ሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር መመካከር እና አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት ተገቢ ይሆናል።       

        በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ አንባቢው ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና  እንዲቀበል እንዲሁም እንዲተገብር እናሳስባለን። 

Show More

Course Content

1. የሚጥል በሽታ (Epilepsy)

  •  1. የሚጥል በሽታ (Epilepsy) 
    00:00

2. እንፍርፍሪት እና  የሚጥል በሽታ (Seizure and epilepsy) 

3. ለእንፍርፍሬት (Seizure) እና / ወይም ለሚጥል በሽታ (Epilepsy) መንስሄ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎች (Etiology) 

4. የእንፍርፍሪት ዓይነቶች (Types of seizure)

5. በተወሰነ የሰውነት ክፍል ላይ የሚከሰት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ የሚያስከትል እንፍርፍሪት (Focal seizure) 

6. አጠቃላይ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚከሰት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የሰውነት እንቅስቃሴን የሚያስከትል አንፍርፍሪት (Generalized seizure) 

7. ለሰከንዶች የሚቆይ አራስን መሳት የሚያስከትል እንፍርፍሪት (Absence seizure)

8. የሰውነት ጡንቻ መዛል ወይም መልፈስፈስ የሚያስከትል አንፍርፍሪት (Atonic seizure)

9. የሰውነት ጡንቻዎች መኮማተር (twitches) እና ማወናጨፍ የሚያስከትል አንፍርፍሪት  (Myoclonic seizure)

10. የሰውነት ጡንቻ መገታተትር የሚያስከትል አንፍርፍሪት (Tonic seizure)   

11. የሰውነት ጡንቻ መኮማተር (stiffness) እና መወናጨፍ (jerking) የሚያስከትል እንፍርፍሪት (Tonic-clonic seizure /grand mal seizure)

12. እንፍርፍሪት ወይም የሚጥል በሽታ መከሰቱን ለማወቅ እንዲሁም መንስሄ ሊሆን የሚችለውን ሁኔታ ለመለየት የሚረዱ የምርመራ መንገዶች (Diagnosis) 

13. የሚጥል በሽታን ለማከም በጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ መድኃኒቶች (Antiepileptic medications) 

14. የሚጥል በሽታን ለማከም በጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ የመድኃኒት ዓይነቶች (Types of Antiepileptic medications) 

15. በሁለተኛ ትውልድ ለሚጥል በሽታ ሕክምና ላይ ከሚውሉ መድኃኒቶች (Second generation antiepileptic medications)

16. የእንፍርፍሪት ወይም የሚጥል በሽታን ለማከም የሚረዱ መድኃኒቶችን ከመጠቀም ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ የጎኒዮሽ ጉዳቶች (Side effects of Antiepileptic medications) 

ማጣቀሻ መጽኃፍት እና ድህረ ገጾች (References)