የምግብ መውረጃ ቧንቧ ተግባር እና በምግብ መውረጃ ቧንቧ ክፍሎች ውስጥ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Esophagus: Physiology and Disorders)
About Course
ይህ ትምህርት የተዘጋጀው ስለ ምግብ መውረጃ ቧንቧ ተግባር እንዲሁም በምግብ መውረጃ ቧንቧ ውስጥ ሊፈጠሩ ስለሚችሉ የጤና ችግሮች አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ታስቦ ነው። የዚህ ትምህርት ዋና አላማ ስለ ምግብ መውረጃ ቧንቧ ተግባር (physiology of esophagus) ፣ በምግብ መውረጃ ቧንቧ ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሩ ስለሚችሉ የጤና ችግሮች (esophageal diseases) ፣ በምግብ መውረጃ ክፍሎች ውስጥ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን ለማከም ወይም ለመከላክል በጥቅም ላይ ሊውሉ ስለሚችሉ የሕክምና መንገዶች (treatment and prevention) እንዲሁም በምግብ መውረጃ ቧንቧ ክፍሎች ውስጥ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን ተከትሎ ሊከሰቱ ስለሚችሉ የጤና ችግሮች (complications) ለማወቅ የሚያስችል እውቀትን እና ግንዛቤን በማዳበር ጤናን በተመለከተ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔን መስጠት የሚያስችል ብቃት እንዲፈጠር ማገዝ ነው።
በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች አላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም እውቀት በሽታን ለማወቅ ወይም በሽታን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ህከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም። በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም በሽታው እንደተፈጠረ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት ወደሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በፍጥነት በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር መመካከር እና ተገቢውን ሕክምና ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን እንመክራለን።
በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በመቀበል እንዲተገብሩ እናሳስባለን።
Course Content
ምዕራፍ አንድ ፡ የምግብ መውረጃ ቧንቧ (Esophagus)
-
1. የምግብ መውረጃ ቧንቧ ( Esophagus)
-
1.1. በምግብ መውረጃ ቧንቧ ክፍሎች ውሰጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Diseases of the Esophagus)