የኩላሊት ጠጠር አፈጣጠር ፣ ዓይነቶች እና ሕክምና (Renal stones: Development, types and Treatment)
About Course
ይህ ትምህርት የተዘጋጀው በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ የሚፈጠሩ ጠጠሮች አፈጣጠር ሂደት እና የጠጠር ዓይነቶች እንዲሁም በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ ለሚፈጠሩ ጠጠሮች ሕክምና በጥቅም ላይ ስለሚውሉ የሕክምና መንገዶች አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ታስቦ ነው። የዚህ ትምህርት ዋና አላማ በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ ስለሚፈጠሩ የተለያዩ ዓይነት ጠጠሮች ፣ ለጠጠር መፈጠር አጋላጭ ሊሆኑ ስለሚችሉ ሁኔታዎች፣ ከጠጠር መፈጠር ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች ፣ ጠጠር መፈጠሩን ለማወቅ ስለሚረዱ የምርመራ መንገዶች እንዲሁም ለሚፈጠሩ ጠጠሮች በጥቅም ላይ ሊወሉ ስለሚችሉ የህክምና አማራጮች እና እና ለጠጠር መፈጠር የመከላኪያ መንገዶች እውቀትን እና ግንዛቤን በማዳበር በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ውስጥ የሚፈጠር ጠጠርን በተመለከተ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔን መስጠት የሚያስችል ግንዛቤ እንዲፈጠር ማገዝ ነው።
በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች አላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም እውቀት በሽታን ለማወቅ ወይም በሽታን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ህከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም። በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም በሽታው እንደተፈጠረ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት ወደሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በፍጥነት በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር መመካከር እና ተገቢውን ሕክምና ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን እንመክራለን።
በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በመቀበል እንዲተገብሩ እናሳስባለን።
Course Content
1. የሰውነት ፈሳሽ መጠን እና ይዘት (Body fluids)
-
.1. የሰውነት ፈሳሽ መጠን እና ይዘት (Body fluids)
00:00 -
1.1. የሰውነት ፈሳሽ የሚገኝባቸው የሰውነት ክፍሎች (Body fluid compartments)
00:00 -
1.2. በሰውነት ፈሳሽ ውስጥ የሚገኙ ሟሚ ነገሮች ( Body fluid solutes)
00:00 -
1.3. የሰውነት ፈሳሽ ተነጻጻሪ የውኃ እና የሟሚ ነገሮች መጠን (Osmolarity)
00:00