አደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶችን ለመጠቀም ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Substance related disorders)
About Course
ይህ ትምሀርት የተዘጋጀው አደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶችን ከመጠቀም ጋር በተገናኘ ስለሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Substance related disorders) በቂ አውቀትን እና ግንዛቤን ለመስጠት ነው። በዚህ ትምህርት ስለ አደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒት ዓይነቶች (Types of substances)፣ ከአደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶች ጋር በተገናኘ ስለሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Substances related disorders)፣ አደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶችን በከፍተኛ መጠን መጠቀም ጋር በተገናኘ ስለሚከሰቱ ምልክቶች እና ለውጦች (Substances intoxication) እንዲሁም አደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶችን መጠቀምን መቀነስ ወይም ማቋረጥ ጋር በተገናኘ ስለ ሚከሰቱ ምልክቶች እና ለውጦች (Substances withdrawal) ጥልቀት ባለው መልኩ በዝርዘር ይቀርባል።
በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ እውነታዎችን ፣ ምስሎችን እና ቁጥሮችን አጠቃላይ እውቀትን እና ግንዛቤን ለማዳበር ከመጠቀም ውጭ ለሌሎች አላማዎች መጠቀም አይመከረም። ከዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም እውቀት በሽታን ለማወቅ ወይም በሽታን በማወቅ ያለ ጤና ባለሞያ ምክር እና ትህዛዝ ሕከምና ለማድረግ ወይም ለመስጠት በጥቅም ላይ ማዋል አይመከረም። በዚህ ትምህርት ውስጥ የተገለጹ የጤና ችግሮች ምልክቶች እና ለውጦች እንደተከሰቱ ወይም በሽታው እንደተፈጠረ በሚጠረጠርበት ወቅት በቅርብት በሚገኘው የጤና አገልግሎት መስጫ በመሄድ ከጤና ባለሙያ ጋር በሚደርግ ምክከር ተገቢውን ምርመራ እና ሕክምና ማግ ኘት አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን።
በዚህ ትምህርት ወስጥ የተካተቱ የጤና ምክሮች እና የሕክምና መንገዶች በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና በፍፁም ሊተኩ ሰለማይችሉ ከጤና ባለሞያ የሚሰጠውን ምክር እና ሕክምና መቀበል እና መተግበር አስፈላአጊ ይሆናል።
Course Content
1. ከአደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶችን መጠቀም ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Substance related disorders)
-
ከአደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶችን መጠቀም ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Substance related disorders)
00:00