
ስለ ሥነ ጤና
በየትኛውም ሥፍራ እና ሆኔታ ውስጥ ሆነው በጥራት የቀረበ የሕክምና ትምህርት ለማግኘት ይፈልጋሉ?
መልሶዎት አዎ ከሆነ ድረ ገጻችን በየትኛውም የዓለም ክፍል ውስጥ ሆነው ስለጤና እና የጤና ሳይንስ ለመማር ለሚፈለጉ በየትኛውም የዕድሜ እና የትምህርት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰዎች እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ስለሆነ ዛሬውኑ ቤተሰብ በመሆን የጤና ሳይንስ ዕውቀቶን በማሳደግ መተኪያ የሌለውን የእርሶዎን እና የቤተሰቦዎን ጤና በሳይንሳዊ ዕውቀት ላይ ተመርኮዘው መንከባከብ ይጀምሩ። ። የሕክምና ሳይነስ ዕወቅቱን ለማሳድግ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው፣ ሙያቸውን በዕውቀት ለማሳደግ ለሚፈልጉ በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ፣ የጤና ትምህርት ለሚያጠኑ ተማሪዎች እንዲሁም ወደፊት የጤና ሳይንስ ለማጥናት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ዕውቅት እንዲያጋኙ የተለያዩ ትምህርቶችን እና ስልጠናዎችን አዘጋጅተናል።
ከዋና ዋና የሕክምና እና የጤና ሳይንስ ጽንሰ ሐሳቦች ጀምሮ እስከ ልዩ ልዩ የሕክምና ዘርፎች ድረስ በጥራት እና በጥልቀት የተዘጋጁ ትምህርቶችን እና ስልጠናዎችን እንሰጣለን። ዛሬውኑ በመመዝገብ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ እውቀቶን በማሳደግ በዋጋ የማይተመነውን የርስዎን እና የቤተሰብዎን ጤና ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ የሚያስችልዎትን በቂ ዕውቀት ይሸምቱ።