14. በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
ጤነኛ የሆነ የልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት በትክክል ተግባራቸውን ማከናወን የሚችሉ በተገቢው መጠን እና ቅርጽ ላይ የሚገኙ የልብ ክፍሎችን ፣ የልብ በሮችን ፣ የልብ ክፍሎችን የሚከፍሉ ግድግዳዎችን ፣ የልብ ጡንቻን እና የልብ የደም ቧንቧዎችን ፣ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች የስፋት መጠን ፣ ቅርጽ እና ተግባር እንዲሁም በደም ቧንቧዎች ውሰጥ የሚገኘውን የግፊት መጠን ያካተተ መሆን አለበት።
በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠር የጤና ችግር የሚከሰተው በፅንስ አፈጣጠር እና ዕድገት ሂደት ወሰጥ በልብ የተለያዩ ክፍሎች እንዲሁም በደም ቧንቧዎች በተለይም በልብ እና በትልልቅ የደም ቧንቧዎች መዋቀራዊ አስራር ወይም አፈጣጠር ወቅት ከሚፈጠር እክል ወይም ጉድለት የተነሳ በተወሰነ የልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት ክፍል ላይ የቅርጽ ፣ የመጠን እንዲሁም የተግባር ለውጥ በሚፈጠርበት ወቅት ነው።
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት ከሚፈጠሩ የጤና ችግሮች መካከል ዋንኞቹ በልብ ክፍሎች አፈጣጠር ወቅት ከሚከሰቱ ጉድለቶች ወይም እክሎች የተነሳ በልብ መጠን ፣ ቅርጽ እና ተግባር ላይ የሚፈጠር የጤና ችግር ፣ የልብን ክፍሎች የሚከፍሉ ግድዳዎች አፈጣጠር ወቅት ከሚከሰቱ እክሎች ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ ግድግዳ መሽንቆርን የሚያስከትል የጤና ችግር ፣ በልብ በሮች አፈጣጠር ወቅት ከሚከሰቱ እከሎች ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ በር መጥበብን ፣ በትክክል መዘጋት አለመቻልን ወይም የልብ በር አለመፈጠርን የሚያስከትል የጤና ችግር እንዲሁም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች አፈጣጠር ወቅት ከሚከሰቱ እክሎች ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደም ቧንቧዎች የጤና ችግር ዋንኞቹ ናቸው።
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ላይ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን በፍጥነት ማወቅ ወይም መለየት እና አስፈላጊውን ህክምና ማድረግ በህይወት ለመቆየት ወይም ለጤናማ ዕድገት በጣም አስፈላጊ ነው።
የልብ ዋና ተግባር ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚቀበለውን ደም በሳንባ በኩል አጣርቶ መልሶ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ይደረስ ዘንድ መርጨት ነው። በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት በሚፈጠሩ የተለያዩ የጤና ችግርች የተነሳ ልብ ለሰውነት ክፍሎች አስፈላጊውን የተጣራ ደም በመርጨት በበቂ መጠን ማድረስ በማይችልበት ወቅት ከሚታዩ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ህጻናቱ በሚወለዱበት ወቅት የሚከሰት የቆዳ ቀለም ለውጥ ነው።
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት ከሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ የተጣራ ደም ለሰውነት ክፍሎች በሚፈለገው መጠን በማይደርስበት ወቅት በተለይ በህጻናት ላይ የቆዳ ቀለም ወደ ሰማያዊ ወይም ግራጫነት ሊቀየር ይችላል። በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የልብ እና የደም ቧንቧ የጤና ችግሮችን ህጻናቱ በሚወለዱበት ወቅት በህጻናቱ ቆዳ ላይ ከሚታየው የቆዳ ቀለም አንጻር ለሁለት ክፍሎ ማየት ይቻላል። እነዚህም፣ የቆዳ ቀለም ለውጥ የሚያስከትሉ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች (cyanotic congenital heart disease / CCHD) እና የቆዳ ቀለም ለውጥ የማያስከትሉ በልብ እና በደም ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች (non cyanotic congenital heart disease / NCCHD) ናቸው።
የቆዳ ቀለም ለውጥ የሚያስከትሉ በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ብዙሁን ጊዜ መከሰታቸው የሚታወቀው በእርግዝና ወቅት በህጻናቱ ላይ በሚደረግ የጤና ምርመራ ወይም ህጻናቱ እንደተወለዱ በሚያሳዩት ምልክት እና ለውጥ የተነሳ ነው። በህጻናት ላይ በውልደት ወቅት የሚታየው የቆዳ ቀለም ለውጥ የሚከሰትበት ምክንያት በልብ በቀኝ በኩል ያለው ያልተጣራ (deoxygenated) ደም ወደ ግራ የልብ ክፍል ውስጥ በመግባት በግራ የልብ ክፍል ወሰጥ ከሚገኘው የተጣራው (oxygenated) ደም ጋር ስለሚቀላቅል እና በደም ውስጥ የሚኖረው አጠቃላይ የኦክስጂን መጠን በከፍተኛ መጠን እንዲቀንስ ስለሚያደርግ ነው። ይህ ዝቅተኛ የኦክስጂን መጠን ያለው ደም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውሰጥ በሚደርስበት ወቅት የከንፈር እና የቆዳ ቀለም ወደ ሰማያዊነት የሚቀየር ይሆናል። ስለሆነም በደም ውስጥ የሚገኘው የኦክስጂን መጠን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ የተነሳ ህጻናቱ እንደተወለዱ የቆዳቸው ቀለም ወደ ሰማያዊ የተቀየረ (cyanotic) ይሆናል።
ህጻናት በሚወለዱበት ወቅት በቆዳችው ላይ በሚከሰተው የቆዳ ቀለም ለውጥ የተነሳ አንድ አንድ ግዜ እነዚህ ህጻናት ሰማያዊ ቀለም ያላቸው ህጻናት (Blue babies) ተብለው ይጠራሉ። የቆዳ ቀለም ለውጥ በሚያስከትሉ በልብ አፈጣጠር ወቅት በሚፈጠሩ የጤና ችግሮች የተጠቁ ህጻናት በህይወት ለመቆየት አፋጣኝ የሆነ የልብ ወይም የደም ቧንቧ የቀዱ ጥገና ህክምና ማግኘት ያስፈልጋቸዋል።
ልብ የተለያየ የግፊት መጠን ባላቸው የግራ እና የቀኝ ክፍሎች የተሰራ የሰውነት ክፍል ነው። የግራ የልብ ክፍል ደም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ለመረጨት ከፍተኛ የሆነ የግፊት ሃይል ስለሚያስፈልገው በግራ የልብ ክፍል ውስጥ የሚገኘው የግፊት መጠን በቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ ከሚገኘው የግፊት መጠን የበለጠ ነው። በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች በሚከሰቱበት ወቅት እነዚህ የተለያየ የግፊት መጠን ያላቸው የልብ ክፍሎች እንዲገናኙ ወይም በእነዚህ ሁለት የልብ ክፍሎች መካከል ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት እንዲፈጠር እና በመካከላቸው የሚኖረውም የግፊት መጠን ልዩነት እንዲለወጥ ሊያደርጉ ይችላሉ።
በግራ እና በቀኝ የልብ ክፍሎች መካከል ግንኙነት በሚፈጠርበት ወቅት በቀኝ እና በግራ የልብ ክፍሎች ውስጥ በሚኖረው የግፊት መጠን ልዩነት ላይ በመመስረት ደም ከቀኝ የልብ ክፍል ወደ ግራ የልብ ክፍል (right to left shunt) ወይም ከግራ የልብ ክፍል ወደ ቀኝ የልብ ክፍል (left to right shunt) ውሰጥ ሊገባ ወይም ሊፈስ እና የተጣራ እና ያልተጣራው ደም መደባለቅ እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት ከሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ጋር በተያያዘ በግራ እና በቀኝ የልብ ክፍሎች መካከል ግንኙነት እንዲፈጠር እና የደም መደባለቅ እንዲፈጠር ሊያደርጉ ከሚችሉ በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፍጣጠር ወቅት ሊከሰቱ ከሚችሉ የጤና ችግሮች መካከል በግራ እና በቀኝ አትሪየም መካከል በሚገኘው ግድግዳ ወይም በአትሪየም ሴፕተም ላይ የሚከሰት መሽንቆር ( atrial septal defect / ASD) ፣ በግራ እና በቀኝ ቬንትሪክል መካከል በሚገኘው ግድግዳ ወይም በቬንትሪክል ሴፕተም ላይ የሚከሰት መሽንቆር ( ventricular septal defect / VSD) እንዲሁም ከቀኝ የልብ ክፍል እና ከግራ የልብ ክፍሎች በሚነሱ የደም ቧንቧዎች መካከል የሚፈጠር ተገቢ ያልሆነ ግንኙነት ዋንኞቹ ናቸው።
በልብ እና በበደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት ከሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ጋር በተያያዘ ደም ከግራ የልብ ክፍል ወደ ቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ በሚፈስበት ወቅት በሳንባ የተጣራው ደም ከግራ የልብ ክፍል ወደ ቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ የሚገባ ይሆናል ፣ በቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ የሚኖረው የደም መጠን ይጨምራል ፣ ወደ ቀኝ የልብ ክፍል በሚገባው ክፍተኛ መጠን ያለው ደም የተነሳ የሚፈጠረውን ግፊት ለመቋቋም እና ይህን ክፍተኛ መጠን ያለው ደም በፑልሞናሪ አርተሪ በኩል ወደ ሳንባ ለመርጨት ይችል ዘንድ የቀኝ ቬንትሪክል ግድግዳ በመጠን መጨመር እንዲሁም መወፈር ይጀምራል።
በቀኝ ቬንትሪክል ወደ ፑልሞናሪ አርተሪ የሚረጨው የደም መጠን በከፍተኛ መጠን በሚጨምርበት ወቅት በፑልሞናሪ አርተሪ ግድግዳ ውስጥ የሚገኘው ጡንቻ እየወፈረ ይመጣል። በዚህም የተነሳ የፑልሞናሪ አርተሪ መጥበብ ይጀመራል። የፑልሞናሪ አርተሪ ጡንቻ መወፈርን ተከትሎ በሚፈጠረው የፑልሞናሪ አርተሪ መጥበብ የተነሳ በቀኝ ቬንትሪክል በፑልሞናሪ አርተሪ በኩል በሚረጨው የደም ፍሰት ወይም ዝውውር ላይ መስተጓጓል እንዲፈጠር ያደርጋል። ይህም ሆኔታ የቀኝ ቬንትሪክል ደምን በፑልሞናሪ አርተሪ በኩል በሚፈለገው መጠን ለመርጨት አለመቻል ወይም በቀኝ የልብ ክፍል ላይ የሚፈጠር የልብ ድካም ( right side heart failure) እንዲከሰት ሊያድርግ ይችላል።
ከግራ የልብ ክፍል ወደ ቀኝ የልብ ክፍል የሚፈሰው የተጣራ ደም ስለሆነ በዚህ ዓይነት የጤና ችግር የተጠቁ ህጻናት በሚወለዱበት ወቅት የቆዳ ቀለም ለውጥ የሚታይባቸው አይሆንም።
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት ከሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ጋር በተያያዘ የደም ከቀኝ የልብ ክፍል ወደ ግራ የልብ ክፍል ውሰጥ መግባት ወይም መፍሰስ ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የተሰብሰበው ያልተጣራ ደም ወደ ግራ የልብ ክፍል እንዲገባ ያደርጋል። በዚህም በግራ ቬንትሪክል በመረጨት ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚደርሰው ደም ውስጥ የሚኖረው የኦክስጂን መጠን በጣም ዝቅተኛ እንዲሆን ያደርጋል። ይህ ዓይነት በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠር የጤና ችግር በደም ውስጥ ከሚፈጠረው የኦክሰጂን በከፍተኛ መጠን መቀነስ የተነሳ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንዲሁም ሌሎች ከውልደት ግዜ ጀምሮ የሚታዩ የበሽታው ምልክቶች እና የስሜት ለውጦች እንዲከሰቱ ያደርጋል።
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች መንስሄ ብዙሁን ግዜ በትክክል የሚታወቅ ባይሆንም በዘረ መል ወይም በክሮሞዞም ላይ የሚከሰቱ ለውጦች ፣ በእርግዝና ወቅት በእናትየው ለተለያዩ የጤና ችግሮች የሚወስዱ መድኃኒቶች ፣ የአልኮል መጠጥ ፣ በእርግዝና ወቅት በእናትየው ወይም በፅንሱ ላይ የሚፈጠሩ ኢንፌክሽኖች እንዲሁም በእርግዝና ወቅት እናትየው ለተለያዩ ቶክሲኖች መጋለጥ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፍጣጠር ወቅት ለሚፈጠሩ የጤና ችግሮች አጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሆኔታዎች ናቸው።
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን በፅንሱ ላይ በእርግዝና ወቅት በሚደረግ ምርመራ በመለየት ፅንሱ ከመወለዱ በፊት በእርግዝና ወቅት ወይም ህጻኑ ከተወለደ በኃላ የተለየዩ የህክምና መንገዶችን በመጠቀም ማከም ይቻላል።