18. በልብ ጡንቻ ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Myocardial Diseases)
ከልብ ጡንቻ ለተለያዩ ጉዳቶች መጋለጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የልብ የጤና ችግር የልብ ጡንቻ መጉዳት ወይም በልብ ጡንቻ ላይ የሚከሰት የልብ የጤና ችግር (cardiomyopathy) ተብሎ ይጠራል። በልብ ጡንቻ ላይ የሚከሰቱ ጉዳቶች በልብ ተግባር ላይ በሚያስከትሉት ችግር መሰረት በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ ። እነዚህም ሦስት ዓይነት በልብ ጡንቻ ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች የልብ ጡንቻ ከመጠን በላይ የመለጠጥ እና የልብ ክፍሎች መስፋት (dilated cardiomyopathy) ፣ የልብ ጡንቻ ከመጠን በላይ መወፈር (hypertrophic cardiomyopathy) እና የልብ ጡንቻ መለጠጥ እና መኮማተር አለማቻል (restrictive cardiomyopathy) ዋንኞቹ ናቸው።