17.1 በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጉዳት ዓይነቶች (types of valvular heart diseases)
በልብ ውስጥ አራት ዓይነት በሮች ይገኛሉ። እነዚህም የልብ በሮች የሚትራል በር ፣ የትራይካስፒድ በር ፣ የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር እና የፑልሞናሪ በር ናቸው። በእነዚህ በሮች ላይ የልብ በር መጥበብ ወይም የልብ በር በትክክል መዘጋት አለመቻል ወይም የልብ በር በተክክለኛው የልብ ክፍል ላይ አለመገኘት የጤና ችግር ሊከሰት ይችላል። ስለሆነም በአጠቃላይ በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጉዳት ዓይነቶችን በሚትራል በር ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች ፣ በትራይካስፒድ በር ላይ የሚከሰቱ የጤና ችገሮች ፣ በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች እና በፑልሞናሪ በር ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች በማለት መመደብ ወይም መክፈል ይቻላል።