Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

23.3 በልብ እና በሳንባ መካከል ከሚገኙ የደም  ቧንቧዎች ጋር በተገናኘ የሚከሰት የጤና ችግር (Pulmonary diseases)

      የልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት እና የአተነፋፈስ ሥርዓት በጋራ በቅንጀት የሚሰሩ እና ለሰውነት የሚያስፈልገው ኦክስጂን ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እንዲደርስ የሚያደርጉ እንዲሁም ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚመጣውን ካርቦንዳይኦክሳይድ ከሰውነት እንዲወገድ የሚይደርጉ ሥርዓቶች ናቸው። በልብ እና በሳንባ መካከል በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ወይም ከፑልሞናሪ የደም ዝውውር ሥርዓት ጋር በተገናኘ የሚከሰት የጤና ችግር የሚፈጠረው በልብ እና በሳንባ መከካል የሚገኙ እና ደምን ከልብ ወደ ሳንባ እንዲሁም ከሳንባ ወደ ልብ የሚያመላልሱ የደም ቧንቧዎች ላይ የጤና ችግር ሲያጋጥም ነው።  

  በልብ እና በሳንባ መካከል የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ያልተጣራ ደም ክልብ ወደ ሳንባ እንዲሁም የተጣራ ደም ከልብ ወደ ሳንባ እንዲደርስ የሚያደርጉ የደም ቧንቧዎች ናቸው። በልብ እና በሳንባ መካከል የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ የጤና ችግር ከሚያስከትሉ ሆኒታዎች መካከል በፑልሞናሪ አርተሪዎች ውስጥ የሚገኘው የደም የግፊት መጠን መጨመር ፣ በፑልሞናሪ ቬን ውስጥ የሚገኘው የደም ግፊት መጠን መጨመር እንዲ‍ሁም በፑልሞናሪ የደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠር የደም መርጋት ወይም የፑልሞናሪ አርተሪ በረጋ ደም ወይም በስብ ከምችት ስብርባሪ መዘጋት (pulmonary embolism) ዋንኞቹ በልብ እና በሳንባ መካከል ከሚገኙ የደም ቧንቧዎች ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች ናቸው።