Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

19.2. በውጭኛው እና በውስጠኛው ፔሪካርዲየሞች መካከል በሚገኘው ክፍተት ውስጥ የፈሳሽ መጠራቀም (pericardial effusion)

   በሴረስ ፔሪካርዲየሞች መካከል በሚገኘው ክፍተት ውስጥ የፈሳሽ መጠራቀም በዙሁን ገዜ የሚፈጠረው ከላይ እንደተገለጸው በሴረስ ፔሪካርዲየም ላይ ብግነት ወይም ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ከሚያደርጉ ሆኔታዎች የተነሳ ነው። ከላይ ከተገለፁት ሆኔታዎች በተጨማሪ የልብ ድካም ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የአልቡሚን ፕሮቲን መጠን መቀነስ ፣ የታይሮይድ ሆርሞን መጠን መቀነስ ፣ በፔሪካርዲየም ላይ የሚፈጠር ጉዳት ወይም አደጋ ፣ በሴረስ ፔሪካርዲየሞች መካከል በሚገኘው ክፍተት ውስጥ ደም አንዲፈስ የሚያደርጉ ሆኔታዎች ( በልብ ላይ የሚፈጠር አደጋ እና ወደ ልብ ሴሎች የሚደርሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን መቀነስን ተከትሎ በልብ ጡንቻ ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ የልብ ግድግዳ መሽንቆር) እና የመሳስሉት ሆኔታዎች ዋንኞቹ በሴረስ ፔሪካርዲየሞች መካከል በሚገኘው ክፍተት ውስጥ የፈሳሽ መጠራቀም እንዲፈጠር የሚያደርጉ ሆኔታዎች ናቸው።

  በልብ ጥንድ የሴረስ ፔሪካርዲየሞች መካከል በሚገኘው ክፍተት ውስጥ የፈሳሽ መጠራቀምን ተከትሎ የሚፈጠሩ ምልክቶች እና ለውጦች ለፈሳሹ መጠን መጨመር መንሰሄ በሆነው ሆኔታ ፣ የፈሳሽ መጠራቀሙ በሚፈጠርበት ፍጥነት እንዲሁም በፈሳሹ መጠን ፣ ዓይነት እና ይዘት ላይ የሚወሰን ይሆናል። ከዚህ የጤና ችግር ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል የትንፋሽ ማጠር ፣ ሳል ፣ በጎሮሮ አካባቢ የሚሰማ ድረቅት እና ማሳከክ ፣ በደረት ላይ የሚሰማ ህመም ፣ በአንገት አካባቢ የሚገኙ የደም መልስ የደም ቧንቧዎች  መገታተር ፣ በደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚፈጠረው የደም ቧንቧ ትርታ ግፊት መቀነስ ፣ በአካለዊ ምርመራ የልብ ደምጾችን ማደመጥ አለመቻል እና የልብ ሽፋኖች ፍትጊያ ድምጽ ( pericardial friction rub) መሰማት ዋንኞቹ ናቸው። 

   በኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ የቲ ሞገድ (T wave) አለመኖር ወይም የ አር ሞገድ ( R wave)  መጠን የተለያየ ሆኖ ሊታይ ይችላል። የኢኮካርዲዩግራም ምርመራ በውሰጠኛው እና በውጭኛው የሴረስ ፔሪካርዲየሞች መካከል የተጠራቀመውን  ፈሳሽ መጠን ሊያሳይ ይችላል። የደረት ራጅ ምርመራ የልብ መጠን መጨመርን ሊያሳይ ይችላል።

  በሴረስ ፔሪካርዲየሞች መካከል በሚገኘው ክፍተት ውስጥ ለሚፈጠር የፈሳሽ መጠራቀም የሚሰጠው ህክምና በፈሳሹ መጠን ላይ የሚወስን ይሆናል። የፈሳሹ መጠን ከፍተኛ ሆኖ የልብን ተግባር የሚገድብ በሚሆንበት ወቅት በፍጥነት ፈሳሹን በመቅዳት ማስወገድ የሚያስፈልግ ሲሆን የፈሳሽ መጠኑ ዝቅተኛ በሚሆንበት ወቅት ደግሞ በኢኮካርዲዮግራም ምርመራ ክትትል ማደረግ አስፈላጊ ይሆናል። በተጨማሪም የበሽታው መንስሄ የሆኑ ሆኔታዎችን በትክክል ለማወቅ የሚረዱ የምርመራ መንገዶችን መጠቀም እና መከታተል አስፈላገ‍ኢ ሊሆን ይቻላል። በሴረስ ፒሪካርዲየሞች መካከል ከሚፈጠረው የፈሳሽ መጠራቀም ላይ ናሙና በመወሰድ በሚደረግ ምርመራ የፈሳሽ መጠራቀሙ መንስሄ ከኢንፌክሽን ፣ ከካንሰር ወይም ከሌላ የጤና ችግር ጋር የተገናኘ መሆኑን በመለየት ተገቢውን ሀከምና መሰጠት አስፈላጊ ይሆናል።