ሀ) በቴምፖራል አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ብግነት (Temporal arteritis)
ይህ ዓይነት የደም ቧንቧ ብግነት በጆሮ በኩል ወይም በጎን የፊት እና የጭንቅላት አካባቢ በሚገኙት የቀኝ እና የግራ የቴምፖራል አርተሪዎች ላይ ብግነት ወይም ቁስለት እንዲፈጠር የሚያደርግ በሽታ ዓይነት ነው። የቴምፖራል አርተሪ የሚነሳው ከካሮቲድ አርተሪ ላይ ሲሆን የካሮቲድ አርተሪ ደግሞ ከትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ላይ በመነሳት ደም ለፊት እና በጭንቅላት ውስጥ ለሚገኙ የሰውነት ክፍሎች የሚያደርስ የደም ቧንቧ ነው።
የቴምፕራል አርተሪ ብግነት ወይም ከካሮቲድ አርተሪ ላይ በሚነሱ ዋና የቴምፕራል አርተሪ ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ቁስለት ወይም ብግነት እንዲፈጠር የሚያደርግ የጤና ችግር ብዙሁን ጊዜ የሚከሰተው በእድሜ በገፉ ሴቶች ላይ ነው።
በግራ ወይም በቀኝ ጆሮ በኩል በሚገኘው የፊት እና የጭንቅላት አካባቢ ላይ የሚፈጠር የህመም ወይም የራስ ምታት እና የማየት ችግር ዋንኛ ከዚህ በሽታ ጋር የሚከሰቱ ምልክቶች ናቸው።
የቴምፖራል አርተሪ ብግነት ትከክለኛ መንስሄ የማይታወቅ ሲሆን የሰውነት የበሽታ መከላኪያ ሥርዓት በደም ቧንቧዎች ላይ በሚያደርሰው ጉዳት ፣ በተለያዩ ኢንፌክሽኖች እንዲሁም በአንድ አንድ መድኃኒቶች የተነሳ ሊፈጠር እንዲሚችል ይታመናል። ከቴምፖራል አርተሪ ብግነት ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች አና ለውጦች መካከል የራስ ምታት ፣ የድካም ስሜት ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ፣ የሰውነት ሙቀት መጨመር ወይም ትኩሳት ፣ የክብደት መጠን መቀነስ ፣ በመንጋጋ አካባቢ የሚከሰት ህመም ፣ የማየት ችግር ፣ በጭንቅላት አጥንት እንዲሁም በጆሮ በኩል በሚገኘው የፊት እና የጭንቅላት አካባቢ ሲነካካ የሚሰማ ህመም ዋንኞቹ ናቸው።
ከቴምፖራል አርተሪ ብግነት ወይም ቁስለት የጤና ችግር ጋር በተገናኘ ሊከስቱ ከሚችሉ ሌሎች የጤና ችግሮች መካከል በካሮቴድ አርተሪ እና ከካሮቴድ አርተሪ ቅርንጫፎች እንዲሁም በሌሎች በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚከሰት ብግነት ወይም ቁስለት ፣ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ መሳሳት እና መሰርጎድ (aneurysm) ፣ የማየት ችግር ወይም እውርነት እንዲሁም ስትሮክ ዋንኞቹ ናቸው።
በደም ምረምራ ወቅት የቀይ የደም ሴሎች በፍጥነት መዝቀጥ ወይም ለረጅም ግዜ የቆየ ኢንፌክሽን ወይም ብግነት መከሰቱን የሚያሳዩ የላብራቶሪ ውጤት (ESR) እንዲሁም በሽታው ከሚታይበት የሰውነት ክፍል ላይ በሚወሰድ ናሙና ላይ የሚደረግ የፓቶሎጂ ምርመራዎች በሽታውን ለማወቅ የሚረዱ የምርመራ ዘዴዎች ናቸው።
የኮምፒዩትድ ቶሞግራፊ (CT) እና የኤም አር አይ (MRI) ምርመራዎችም በሽታውን ለማወቅ እጀግ ጠቃሚ የምርመራ መንገዶች ናቸው።