Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

ሀ). የካዋሳኪ በሽታ (Kawasaki disease)

       ህጻናትን በተለይም እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሚገኙ ህጻናትን የሚያጠቃ መካከለኛ መጠን ባላቸው የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ቁስለት ወይም ብግነት የሚያስከትል በሽታ ነው። የካዋሳኪ በሽታ በተለየ ሆኔታ የኮሮናሪ አርተሪ ላይ ቁስለት በማስከትል በልብ ላይ ክፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ሲሆን ይህ የጤና ችግር በህጻናት ላይ የልብ በሽታን ከሚያስከትሉ የጤንነት ችግሮች ውስጥ አንዱ ነው። 

   የካዋሳኪ በሽታ በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት ክፍሎች ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት በተጨማሪ በአንጎል ፣ በቆዳ ፣ በአፍንጫ ፣  በአፍ እና በጎሮሮ ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። የካዋሳኪ በሽታ መንስሄ በትክክል የሚታወቅ ባይሆንም የዘር ግንድ ወይም በዘር መተላለፍ ፣ የቫይረስ አና የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖች እንዲሁም አንድ አንድ ኬሜካሎች ለካዋሳኪ በሽታ ተጋላጭነትን ሊጨምሩ እንደሚችሉ ይታመናል። የካዋሳኪ በሽታ ከሚያስከትላቸው ምልክቶች እና ለውጦች መካከል ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ሙቀት መጠን መጨመር ወይም ትኩሳት ፣ በቆዳ ላይ የሚታይ ሽፍታ ፣ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚከሰቱ የቆዳ መላላጥ ፣ የሊምፍ እጢዎች ዕብጠት ፣ በአጥንት እና በአጥንት መገጣጠሚያዎች ላይ የሚሰማ ህመም ፣ የምላስ መቅላት ፣ በእጅ እና እግር ላይ የሚታይ መቅላት አና ዕብጠት ፣ የሆድ ህመም ፣ ተውከት እና ተቅማጥ ዋንኞቹ ናቸው። 

የካዋሳኪ በሽታን ተከትሉ ሊከሰቱ ከሚችሉ ሌሎች የጤና ችግሮች መካከል በልብ ጡንቻ ሴሎች ላይ የሚፈጠር ብግነት (myocarditis) ፣ የልብ ምት መዛባት እንዲሁም የደም ቧንቧዎች ግድግዳ መለጠጥ እና መሰርጎድ ጥቂቶቹ ናቸው።

    በደም ምረመራ ለረጅም ጊዜ የቆይ ኢንፌክሽን ወይም ብግነት መኖሩን የሚያሳይ የደም ላብራቶሪ (ESR) ምርመራ ፣ የኢኮካርዲዮግራም (Echo) ፣ የኤሌክትሮግራም (ECG) እና የደረት ራጅ ምርመራዎች በሽታው መከሰቱን እና በየሰውነት ክፍሎች ላይ የተከሰቱ ለውጦችን ለመለየት የሚረዱ የምርመራ ዘዴዎች ናቸው። 

  የካዋሳኪ በሽታን ለረጅም ጊዜ በሚወሰድ አስፕሪን ፣ የደም ማቅጠኛ መደኃኒቶችን እንዲሁም የኮሮናሪ አርተሪን መጥበብ እና መዘጋት ለማከም የሚረዱ የህክምና ዘዴዎችን መጠቀም አሰፈላጊ ይሆናል።