Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

16.2. በልብ ውስጥ የሚከሰት ኢንፌክሽን  (Infective Endocarditis)

በልብ ውስጥ የሚክሰት ኢንፌክሽን ማለት በኢንፌክሽን አምጭ ህዋሶች የተነሳ በልብ ውስጥ ከሚፈጠር ኢነፌክሽን ወይም ብግነት ጋር በተገናኘ በልብ የወስጥ ክፍሎች እና የልብ በሮች ላይ ጉዳት የሚያደርስ የልብ የጤና ችግር ማለት ነው። በልብ ውስጥ የሚከሰት ኢንፌክሽን አብዛኛውን ግዜ የሚከሰተው በተለያዩ ባክቲሪያዎች የተነሳ ቢሆንም ከባክቲሪያ ውጭ በሆኑ ህዋሶች ማለትም ቫይረሶች እና ፈንገሶች ጭምር ሊከሰት ይችላል።  

በልብ ውስጥ የሚከሰት ኢንፌክሽን በፍጥነት የሚከሰት (acute) ወይም ቀስ በቀስ በሳምንታት እና በወራት  ውስጥ  የሚከሰት (subacute)  ሊሆን ይችላል።

 በፍጥነት የሚከሰት የልብ ውስጥ ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ከሚያደርጉ የባክቲሪያ ዓይነቶች መካከል ስታፊሎኮከስ አውሬስ (staphylococcus aureus) የሚባለው ባክቲሪያ በፍጥነት በልብ ግድግዳ ጡንቻ  እና በሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ሲሆን ቀስ በቀስ የሚከሰት የልብ ውስጥ ኢንፌክሽን አንዲፈጠር ከሚያደርጉ ባካቲሪያዎች መካከል ደግሞ ስትሬፕቶኮካል ቪሪዳንስ / Streptococcus viridans ተብሎ የሚጠራው ባክቲሪያ ዋንኛው እና በተለይም አስቀድሞ ጉዳት በደረሰበት የልብ በር ላይ ወይም የሰውሰራሽ የልብ በር በተገጠመላቸው ወይም በልብ አጠቃላይ አፈጣጠር እና ተግባር ላይ ችግር ያለበት ልብ ባላቸው ሰዎች ላይ በልብ ውስጥ የሚከሰት ኢንፌክሽንን የሚያስከትል ባክቲሪያ ነው።

     በልብ ውስጥ ኢንፌክሽን በሚፈጠርበት ወቅት ከሚታዩ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል አጠቃላይ የደካም ስሜት መስማት ፣ የሰውነት ሙቀት መጨመር ወይም ትኩሳት ፣ ብርድ ብርድ ማለት ፣ አዲስ የተፈጠረ ጤነኛ ያልሆነ የልብ ምት ድምጽ እና በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ በሚከሰቱ ጉዳቶች (በኩላሊት ግሉመሩለስ ላይ የሚከሰት ጉዳት ፣ በልብ ውስጥ ከሚከሰት እንፌክሽን ጋር በተገናኘ በሚፈጠሩ የደም ሴሎች እና የስብ ክምችት ስብርባሪዎች በአንጎል ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች መዘጋት (septic embolic stroke) ፣ በቆዳ ወስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧ) የተነሳ የሚፈጠሩ ምልክቶች እና ለውጦች ሊከሰቱ ይችላሉ።

   በልብ ውስጥ የሚከሰት ኢንፌክሽን መከሰቱን ለማወቅ የሚረዳ፣ ኢንፌክሽን አምጭ የሆነውን ህዋስ ለመለየት እና በሽታ አምጭ የሆነውን ህዋስ ሊገድል የሚችል ትክክለኛ መድኃኒት ለመመረጥ የሚያስችል የደም ምርመራ ( blood culture and sensitivity test) በተደጋጋሚ ማድረግ እንዲሁም በልብ ውስጥ የተፈጠረውን ጉዳት የሚያሳይ የኢኮካርዲዮግራም ምርመራ በማድረግ በሽታው መከሰቱን መለየት ይቻላል። በተጨማሪም በልብ ውሰጥ ከተፈጠረው ኢንፌክሽን ጋር በተገናኘ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከሚፈጠሩ ጉዳቶች የተነሳ የሚከሰቱ ምልክቶችን እና ለውጦችን ለመለየት የሚረዳ ጥልቀት ያለው አካላዊ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል።

    በልብ ውስጥ የሚከሰት ኢንፌክሽን መከሰቱ በሚጠረጠርበት ወቅት በፍጥነት የጸረ ባክትሪያ ህክምና ማስጀመር እና የተከሰተውን ኢንፌክሽን መቆጣጠር ሊከሰት የሚችለውን የሞት አደጋ በመቀነስ ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው። በተጨማሪም በልብ በሮች ላይ የሚደረስው ጉዳት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚገኝበት ወቅት የቀዶ ጥገና ህክምና አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። የልብ የጤና ችግር ያለባቸው እና የጥርስ ወይም በተወሰኑ የሰውነት ክፍሎች ላይ የቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ሰዎች በልብ ውስጥ የሚከሰት ኢንፌክሽንን መፈጠር ለመከላከል የሚያገለግል ጸረ ህዋስ መድኃኒቶችን መጠቀም ያስፈልጋቸዋል። በልብ ውስጥ የሚከሰት ኢንፌክሽን እንደተከሰተ በአፋጣኝ በተገቢው ሆኔታ መታከም ካልቻለ ለሞት የሚያደርስ ይሆናል።