13.6. በልብ እና የደም ቧንቧ ሥር ዓት አፈጣጠር ሂደት ውስጥ ለሚፈጠሩ የጤና ችግሮች አጋላጭ ሆኔታዎች (Risk factors for congenital heart diseases)
በአጠቃላይ በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት ለሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ሊያጋልጡ ከሚችሉ ሆኔታዎች መካከል የአልኮል መጠጥ ፣ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የሩቤላ ወይም የጀርመን ኩፍኝ ኢንፌክሽን ፣ የማርፋን ሲንድሮም (Marfan’s syndrome) ፣ የእናትየው በስኳር በሽታ መጠቃት ፣ እናትየው ለሊትየም (lithium) መድኃኒት መጋለጥ እንዲሁም በዘረ መል ወይም በክሮሞዞም ላይ ከሚፈጠር ለውጥ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ እንደ የዳውን ሴንድሮም (Downs syndrome) ፣ የተርነር ሲንድረም (Turner syndrome) ፣ የዊሊያም ሲንድሮም (William”s syndrome) እና ዳይጆርጅ ሲንድሮም (Digeorge syndrome) ያሉ ሆኔታዎች ዋንኞቹ ናቸው።
የአልኮል መጠጥ (fetal alcohol syndrome) ፡ የቬንትሪክል ሴፕተም መሸንቆር (VSD) ፣ የአትሪየም ሴፕተም መሸንቆር (ASD) ፣ የደክተስ አርተሪኦሰስ እንደተከፈተ መቅረት (PDA) ፣ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ውስጥ በአንድ ላይ የሚከሰቱ አራት የልብ ጤና ችግሮች (ToF)
በእርግዝና ወቅት የሚክሰት የሩቤላ ወይም የጀርመን ኩፍኝ ኢንፌክሽን ( Congenital rubella) ፣ የቬንትሪክል ሴፕተም መሸንቆር (VSD) ፣ የአትሪየም ሴፕተም ግድግዳ መሸንቆር (ASD) ፣ የድክተስ አርተሪኦሰስ እንደተከፈተ መቅረት (PDA) ፣ የፑልሞናሪ አርተሪ በር መጥበብ (Pulmonary stenosis)
በስኳር በሽታ መጠቃት ፡ የትልቁ ደም ቅዳ እና የፑልሞናሪ አርተሪ ከተቃራኒ የልብ ክፍሎች ላይ መነሳት (TPGA)
የዳውን ሲንድሮም (Down’s syndrome) ፡ የቬንትሪክል ሴፕተም መሸንቆር (VSD) ፣ የእትሪየም ሴፕተም መሸንቆር (ASD)
የማርፋን ሲንድሮም (Marfan’s syndrome)፡ የሚትራል በር ወደ አትሪየም ወስጥ መግባት (MVP) ፣ የትልቁ ደም ቅዳ ግድግዳ መለጠጥ እና መሰርጎድ ( aortic aneurysm) ፣ የትልቁ ደም ቅዳ ግድግዳ መቀደድ (Aortic rupture) ፣ የትልቁ ደም ቅዳ በር በትክክል መዘጋት አለመቻል ( Aortic regurgitation)
ለሊቲየም መድኃኒት መጋለጥ ( Lithium exposure) ፡ በቀኝ አትሪየም እና ቬንትሪክል መካክል የሚገኘው የትራይካስፒድ በር ከትክክለኛው የልብ ክፍል ዝቅ ብሎ በቬንትሪክል ውስጥ መገኘት (Ebstein’s anomaly)
የተርነር ሲንድረም (Turner’s syndrome)፡ የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር ባለ ሁለት ካስፒድ ብቻ ሆኖ መፈጠር (bicuspid valve) ፣ የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ (Coarctation of the aorta)
የዊሊያም ሲንድሮም (William’s syndrome) ፡ የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ከትልቁ ደም ቧንቧ በር በላይ በሚገኘው ክፍል ላይ መጥበብ (Supravalvular aortic stenosis)
ዳይጀኦርጅ ሲንድሮም (DiGeorge syndrome) ፡ የደክተስ አርተሪኦሰስ እንደተከፈተ መቅረት (PDA) ፣ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ውስጥ በአንድ ላይ የሚከሰቱ አራት የጤና ችግሮች (ToF)