Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

14.2.6. ኢሴንመንገር ሲንድሮም (Eisenmenger syndrome)

       በቀኝ እና በግራ የልብ ክፍሎች መካከል በሚገኘው ግድግዳ መሽንቆር የተነሳ በሁለቱ የልብ ክፍሎች መካከል ግንኙነት በሚፈጠርበት ወቅት ደም ከግራ የልብ ክፍል ወደ ቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ በቀላሉ የሚገባ ይሆናል። ይህም ሆኔታ በቀኝ የልብ ክፍል ውሰጥ የሚኖረው የደም እና የግፊት መጠን በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ያደርጋል። በቀኝ የልብ ከፍል ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው ደም በፑልሞናሪ አርተሪ በኩል ወደ ሳንባ በሚረጭበት ወቅት በፑልሞናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ  በሚፈጥረው ከፍተኛ ግፊት የተነሳ የፑልሞናሪ አርተሪ ግድግዳ መወፈር ይጀምራል። 

     የፑልሞናሪ አርተሪ ግድግዳ እየወፈረ መምጣትን ተከትሎ የፑልሞናሪ አርተሪ እየተጠበበ ሲመጣ በፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ የሚኖረው ግፊት እየጨመረ ይመጣል። በፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ የሚፈጠረው ግፊት እየጨመረ ሲመጣ ደግሞ የቀኝ የልብ ክፍል ወይም የቀኝ ቬንትተሪክል ይህን ግፊት ለመቋቋም እየወፈረ እንዲሁም በቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ የሚፈጠረው የግፊት መጠንም እየጨመረ የሚመጣ ይሆናል። ስለሆነም በቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ የሚፈጠረው የግፊት መጠን በግራ የልብ ክፍል ውስጥ ከሚፈጠረው ግፊት የበለጠ እየጨመረ ይመጣል። በዚህም የግፊት መጠን ልዩነት መለወጥ የተነሳ ደም ከቀኝ የልብ ክፍል ወደ ግራ የልብ ክፍል ውስጥ አልፎ መግባት ይጀምራል።  

   ደም ከቀኝ የልብ ክፍል ወደ ግራ የልብ ክፍል ውስጥ በሚገባበት ወቅት ያልተጣራው ደም ከተጣራው ደም ጋር አየተደባለቀ በግራ ቬንትሪክል በኩል ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚረጭ ይሆናል። ይህ የጤና ችግር በሂደት ከቀኝ የልብ ክፍል የሚመጣው ያልተጣራ ደም በግራ የልብ ከፍል ውስጥ ከሚገኘው የተጣራው ደም ጋር እንዲቀላቀል እና በደም ውስጥ የሚገኘው የኦክስጂን መጠን በከፍተኛ መጠ እንዲቀንስ በማድረግ  በሰውነት ቆዳ ላይ የሚታይ ለውጥ እና ሌሎች ምልክቶች እንዲታዩ ያደርጋል። 

    ይህ የጤና ችግር በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላይ ሊከሰት ይችላል።