Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

 15.1. የልብ ምት መዛባት (arrhythmia)

   የልብ ምት መጠን በእድሜ የሚለያይ ሲሆን የአንድ ጤነኛ አዋቂ ሰው የልብ ምት ፍጥነት መጠን በደቂቃ በ 60 እና 100 መካከል መሆን ይኖርበታል። በደቂቃ ውስጥ የሚኖረው የህጻናት የልብ ምት ፈጣን ሲሆን እድሜ እየጨመር ሲመጣ የልብ ምት ፍጥነት መጠን እየቀነሰ ይመጣል።  የልብ ምት መዛባት ማለት በልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ላይ ከሚከሰቱ የተለያዩ የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ የልብ ምት ፍጥነት መጨመርን ፣ የልብ ምት ፍጥነት መቀንስን ፣ የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ከሳይነስ ኖድ ውጭ መነሳትን እንዲሁም የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ፍስት ከትከከለኛው መስመር ውጭ በሆነ መንገድ መጓዝን ወይም የተዛባ የልብ ምት ድግግሞሽን የሚያጠቃልል የጤና ችግር ነው። በሌላ አነጋገር የተዛባ የልብ ምት ማለት ጤነኛ ከሆነው የልብ ምት ፍጥነት እና ድግግሞሽ ውጭ በሆነ ሆኔታ ውስጥ ያለ ልብ ምት ማለት ነው።

     የልብ ምት ጤነኛ የልብ ምት ነው ለማለት ቢያንስ የሚከተሉት አራት ሆኔታዎች ተሟልተው መገኘት ይኖርባቸዋል። አንደኛው ሆኔታ የልብ ምት ፍጥነት በደቂቃ  በ 60 እና 100 መካከል መሆን አለበት ። ስለሆነም የልብ ምት ከ 60 በታቻ ወይም 100 በላይ በሚሆንበት ወቅት የልብ ምት መዛባት ተከስቷል ማለት ይቻላል። በሁለተኛ ደረጃ መሟላት ያለበት ሆኔታ የልብ ምት እንዲፈጠር የሚያደርገው የኤሌክትሪክ አንቅስቃሴ መነሻ ክፍል የሳይኖአትሪያል ሴሎች ክምችት ወይም ሳይነስ ኖድ መሆን አለበት። ክሳይነስ ኖድ ውጭ በሚነሳ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የሚመራ የልብ ምት ከጤነኛ የልብ ምት ውጭ የሆነ ወይም የተዛባ የልብ ምት ነው። በሦስተኛ ደረጃ ለጤነኛ የልብ ምት መፈጠር መሟላት ያለበት ሆኔታ የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በሳትኖአትሪያል ኖድ ከመመራት በተጨማሪ በሳይኖአትሪያል ኖድ ውስጥ የተፈጠረው የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ትክክለኛ የፍሰት መንገዱን (conduction pathway) ጠብቆ የቬንትሪክል ሴሎች ውስጥ እስከሚደርስ ድረስ በተገቢው የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መንገድ ውስጥ መፍሰስ ይኖርበታል። አራተኛው ለጤነኛ የልብ ምት መፈጠር መሟላት የሚኖርበት ሆኔታ በሳይኖአትሪያል ኖድ ውስጥ የተፈጠረው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በትክክለኛው የኤሌከትሪክ መንገድ ውስጥ ከመፈሰስ በተጨማሪ ፍሰቱ ወይም የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በተገቢው ፍጥነት ውስጥ መሆን ይኖርበታል።  

   ስለሆነም ጤነኛ የልብ ምት የልብ ምት ፍጥነት በ 60 እና 100 መካከል መሆን ፣ የልብ ምት ከሳይኖአትሪያል ኖድ በሚነሳ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መመራት ፣ በሳይኖአትሪያል ኖድ ውስጥ የሚነሳው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ከሳይኖአትሪያል ኖድ ተነስቶ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ በኩል አልፎ በዋናው የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ማሳለፊያ በኩል አድርጎ በግራ እና በቀኝ ማሳለፊያ መንገዶች በኩል ከደረሰ በኋላ በፑርኪንጂ ድሮች ውስጥ አልፎ ወደ ቬንትሪክል ሴሎች መድረስ ይኖርበታል። የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ከሳይኖአትሪያል ኖድ ተነስቶ ወደ ፑርኪንጂ ድሮች ለመድረስ የሚውስደው ፍጥነትም በተገቢው የግዜ መጠን ውስጥ መሆን ይኖርበታል። ስለሆነም ከላይ የተገለጹትን አራት ሆኔታዎች ውስጥ እንዱን እንኳን የማያሟላ የልብ ምት ሂደት የተዛባ የልብ ምት ተብሎ ሊጠራ  ይችላል።

        በሳይነስ ኖድ ወይም በአትሪኦቬንትሪኪዩላር  ኖድ ውሰጥ በሚፈጠር የጤና ችግር የተነሳ የልብ ምት ፍጥነት በደቂቃ ከ 60 በታች የሚሆንበት ሆኔታ የልብ ምት ፍጥነት መዘግየት (bradycardia ተብሎ ይጠራል። በአትሪየም ውስጥ በኤሌክትሪክ አንቅስቃሴ ላይ ከሚፈጠር እክል (supraventricular) ወይም በቬንትሪክል ውስጥ በኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ላይ ከሚፈጠር እክል (ventricular) ጋር በተገናኘ የልብ ምት ፍጥነት በደቂቃ ከ 100 በላይ የሚሆንበት ሆኔታ ደግሞ ፈጣን የልብ ምት (tachycardia) ተብሎ ይጠራል። በአትሪየም ውስጥ የሚከሰት የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የሚፈጠረው በሳይነስ ኖድ ወይም በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ላይ በሚከሰቱ የጤና ችግሮች የተነሳ ሲሆን በቬንትሪክል ውስጥ የሚከሰት የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ እክል የሚፈጠረው ደግሞ ከአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ በታች በሚገኘው የቬንትሪክል ክፍል ውስጥ ነው።

  ፈጣን የልብ ምት (tachycardia) ሊከሰት የሚችለው በተለያዩ የልብ ክፍሎች ውስጥ በልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቅሴ ላይ በሚፈጠሩ እክሎች የተነሳ ሲሆን በሚኖረው የልብ ምት ፍጥነት እና የልብ ምቱ በሚፈጠርበት ሂደት ላይ በመመርኮዝ በተለያዩ ምድቦች ሊከፈል ይችላል። የልብ ምት ፍጥነት ከ 100 አስከ 150 በደቂቃ የሚጨምርበት ሆኔታ ቀላል የልብ ምት ፍጥነት መጨመር (simple tachyarrhythmia) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የልብ ምት ፍጥነት ከ 150 እስከ 250 በደቂቃ የሚጨምርበት እና በድንገት ከመጣ በኋላ ተመልሶ ወደ ጤነኛው የልብ ምት የሚመለስ ሆኖ ሲገኝ በድንገት የሚከሰት የልብ ምት ፍጥነት መጨመር (paroxysmal tachyarrhythmia) ተብሎ ይጠራል። በተጨማሪም በልብ የአትሪየም ክፍል ላይ በሚከሰት ጤነኛ ያለሆነ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የተነሳ የልብ ምት ፍጥነት በ 250 እና 350 በደቂቃ ሆኖ የልብ ምት ባለተዘበራረቀ ድገግሞሽ የሚገኝበት ሆኔታ የአተሪየም ፍልተር (flutter ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በልብ የአትሪየም ክፍል ላይ በሚከሰት ጤነኛ ያለሆነ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የተነሳ የልብ ምት ፍጥነት በ 250 እና 350 በደቂቃ ሆኖ  በተዘበራረቀ  ድግግሞሽ የሚገኝበት ሆኔታ ደግሞ የአትሪየም ፊብሪሌሽን (fibrillation) ተብሎ ይጠራል። 

  ጤነኛ ባልሆነ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የተነሳ በተዘበራረቀ ድግግሞሽ የልብ ፍጥነት መጨመር በአትሪየም (atrial fibrillation) ወይም በቬንትሪክል / (ventricular fibrillation) ውስጥ ሊነሳ ይቻላል።

      የልብ ምት ፍጥነት ከ 60 በታች በደቂቃ የሚሆንበት ሆኔታ የዘገየ የልብ ምት (bradyarrhythmia) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የልብ ምት ፍጥነቱ በሚቀንስበት ደረጃ መካከለኛ ወይም በጣም የዘገየ የልብ ምት ተብሎ ሊመደብ ይችላል።

  የልብ ምት መዛባት በሚነሳበት የልብ ክፍል ላይ በመመስረት በተለያዩ ምድቦች ሊመደብ ይችላል። በሳይኖአትሪያል ኖድ ውስጥ በሚከሰት የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ እክል የተነሳ የሚፈጠር የልብ ምት መዛባት የሳይኖአትሪያል የልብ ምት መዛባት (sinus arrhythmia) ተብሎ የሚመደብ ሲሆን በአትሪየም ውስጥ በሚከሰት የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ እክል የተነሳ የሚፈጠር የልብ ምት መዛባት ደግሞ የአትሪየም የልብ ምት መዛባት (atrial arrhythmia) ተብሎ ይጠራል።

     በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ በሚከሰት የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ እክል የተነሳ የሚፈጠር የልብ ምት መዛባት የአትሪዩቬንቲኪዩላር ኖድ የልብ ምት መዛባት (Nodal arrhythmia) ተብሎ የሚመደብ ሲሆን በቬንትሪከ‍እል ውስጥ በሚከሰት የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ እክል የተነሳ የሚፈጠር የልብ ምት መዛባት ደግሞ የቬንትሪክል የልብ ምት መዛባት (ventricular arrhythmia) ተብሎ የሚመደብ ይሆናል።

    የሳይኖአትሪያል የልብ ምት መዛባት (sinus arrhythmia) ፣ የአትሪየም የልብ ምት መዛባት (atrial arrhythmia) እና  የአትሪዩቬንትሪኪዩላር  ኖድ የልብ ምት መዛባት (Nodal arrhythmia)  መነሻው  ከቬንትሪክል በላይ ስለሆነ በአንድ ላይ በሚሰጣቸው ስያሜ ከቬንትሪክል በላይ የሚነሳ የልብ ምት መዛባት (supraventricular tachyarrhythmia) ተብለው ሊጠሩ የሚችሉ ሲሆን በቬንትሪክል ውስጥ የሚነሱ የተዛባ የልብ ምት ዓይነቶች ደግሞ በአንድ ላይ በሚሰጣቸው ስም  በቬንትሪክል ውስጥ የሚነሳ የእቬንትሪክል የልብ ምት መዛባት (ventricular tachyarrhythmia) ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ።