14.1.5. በኢንዶካርዲያል ኮሺን አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠር የጤና ችግር (Endocardial cushion defect)
የኢንዶካርዲያል ኮሺን የልብ ክፍል ለታችኛው የአትሪየም ሴፕተም ፣ ለላይኛው የቬንትሪክል ሴፕተም እንዲሁም በአትሪየም እና ቬንትሪክል መካከል ለሚገኙ በሮች በትክክል መፈጠር በጣም ወሳኝ ወይም አስፈላጊ የሆነ ክፍል ነው። የኢንዶካርዲያል ኮሺን ክፍል በትክክል በማይፈጠርበት ወቅት የአትሪየም ሴፕተም መሽንቆር ፣ የቬንትሪክል ሴፕተም መሽንቆር እንዲሁም የትራይካስፒድ ወይም የሚትራል በር በትክክል አለመስራት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
በኢንዶካርዲያል ኮሺን አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠር የጤና ችግር እንዲከሰት ሊያደርጉ ከሚችሉ ሆኔታዎች መካከል የዳውን ሲንድሮም እንዲሁም በእናትየው ላይ የሚፈጠር የስኳር በሽታ እና ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት ዋንኞቹ ናቸው።
የአትሪየም ሴፕተም ወይም የቬንትሪክል ሴፕተም መሽንቆር በሚከሰትበት ወቅት ደም ከግራ የልብ ክፍል ወደ ቀኝ የልብ ክፍል እንዲግባ እና በቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ የሚገኘው የደም እና የግፊት መጠን እንዲጨምር በማድረግ በፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ የሚከሰተውን የደም ግፊት መጠን ተከትሎ የልብ ድካም በሽታ እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
በኢንዶካርዲያል ኮሺን አፈጣጠር ሂደት ወቅት ከሚፈጠር የጤና ችግር ጋር በተገናኘ በልብ በሮች ላይ የሚከሰት ጉዳት በሚፍጠርበት ወቅት የልብ በሮች በትክክል እንዳይዘጉ በማድረግ ከልብ በር ጋር በተገናኝ የሚከሰት የጤና ችግር እንዲሁም ፅንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ የልብ ድካም እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
በእርግዝና ወቅት የፅንሱን የልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት ተግባር ለመከታተል በሚረዳ የኢኮካርዲዩግራፊ ምርመራ የበሽታውን መከሰት መለየት ወይም ማወቅ የሚቻል ሲሆን በቀዶ ጥገና ህክምናም የተፈጠረውን የጤና ችግር ማስተካከል አስፈላጊ ይሆናል። ።