15.1.4.2. ጀንክሽናል የልብ ምት ፍጥነት እንዲጨምር የሚያደርግ የልብ ምት መዛባት (junctional tachyarrhythmia)
በተለያየ መንገድ በአትሪዩቬንትሪክል ኖድ ውስጥ በሚያልፈው የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ላይ ለውጥ ወይም አክል እንዲከሰት በማድረግ የልብ ምት ፍጥነት እንዲጨምር ከሚያደርጉ እና በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ ወይም በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ አካባቢ ከሚፈጠሩ የጤና ችግሮች መካከል ከአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውጭ በአትሪየም እና በቬንትሪክል መካክል የሚፈጠር ያልተገባ ግንኙነት (re entry) እና በአትሪዪቬንትሪኪዪላር ኖድ ውስጥ የሚሽከረከር የኤሌክትሪክ እንቅሰቃሴ (inra nodal) ዋንኞቹ የጤና ችግሮች ነው። ይህ ዓይነት በቬንትሪክል እና በአትሪየም መካክል የሚፈጠር ያልተገባ ግንኙነት ምክንያት ወይም በአትሪዪቬንትሪኪዪላር ኖድ ውስጥ በሚከሰት የየልብ ኤሌክትሪክ እንቅሰቃሴ መሽከረከር የተነሳ የሚፈጠር የልብ ምት ፍጥነት መጨመር ጀንክሽናል የልብ ምት ፍጥነት እንዲጨምር የሚያደርግ የልብ ምት መዛባት (junctional thacyarrythemia) ተብሎ ይጠራል።
በአትሪየም እና በቬንትሪክል መካክል በሚፈጠር ያልተገባ ግንኙነት (re entry) የተነሳ የሚከሰት የልብ ምት ፍጥነት መጠን መጨመር በዋናነት የሚፈጠረው አትሪየም እና ቬንትሪክልን ከሚያገናኝ የለብ የኤሌክትሪክ አንቅስቃሴ መስመር (bundle of bent) ይዘው በሚወለዱ ሰዎች ላይ ነው። በአትሪየም እና ቬንትሪክል መካከል የልብ የኤሌክትሪክ እንቅሰቃሴን ከሚያገናኝ መሰመር ጋር አብረው የሚወለዱ ሰዎች ያለምንም የጤና ችግር ወይም ምልክት ለረጅም ግዜ ያለምንም ምልክት እኣ ለውጥ መኖር ይችላሉ። ከመገናኛ መስመሩ ጋር በተገናኘ የልብ ምት መዘባት የሚፈጠረው በተለየዩ ምክንያቶች አገናኝ መስመሩ በሚገኝበት የልብ ክፍል ውሰጥ በሚገኙ ሴሎች ላይ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር የሚያደርጉ ሆኔታዎች በሚከሰትበት ወቅት ነው። በዚህም እዲስ በአትሪየም ውስጥ የሚፈጠረው የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በአገናኝ መስመሩ በኩል ወደ ቬንትሪክል ከዚያም ወደ አትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚገባ ይሆናል። በአትሪዩቬትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚገባው የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ እንደገና ተመልሶ በአትሪየም ከዚያም በቬንትሪክል መካከል በመሽከርከር (circuit movement) በተወሰነ የልብ ክፍል ውስጥ የሚፈጠር የልብ ምት ፍጥነት በከፍተኛ መጠን መጨመር እንዲከሰት ያደርጋል።
ይህ ዓይነት ከወልደት ጀምሮ በሚፈጠር ቬንትሪክልን እና እትሪየምን በሚያገናኘው መስመር የተነሳ የልብ ምት ፍጥነት በከፍተኛ መጠን መጨመር እንዲፈጠር የሚያደርግ የጤና ችግር ዎልፍ ፓርኪንሰን ዋይት ሲንድሮም (Wolff Parkinson White Syndrome) ተብሎ ይጠራል። በዎልፍ ፓርኪንሰን ዋይት ሲንድሮም የተጠቁ ሰዎች በተቻለ መጠን በልብ ውስጥ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የሚፈጠሩ እንደ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ፣ የአልኮል መጠጥ ፣ ሴጋራ ማጤስ እና የመሳሰሉትን ሆኔታዎችን እንዲያስወገዱ ይመከራሉ።