Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

16.1.4. ወደ ልብ ሴሎች ከሚደረሰው የደም መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ በልብ ጡንቻ ላይ የሚፈጠር የጤና ችግር  (Chronic Ischemic Cardiomyopathy (CIH)

በተደጋጋሚ ወይም ለረጅም ግዜ በልብ ጡንቻ ውስጥ ለሚገኙ ሴሎች ከሚደርሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተያያዘ ቀስ በቀስ በልብ ጡንቻ ላይ በሚከሰት የጤና ችግር ወይም ጉዳት የተነሳ የሚፈጠር የልብ የጤና ችግር ወደ ልብ ሴሎች ከሚደረሰው የደም መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ በረጅም ግዜ በልብ ጡንቻ ላይ የሚፈጠር የጤና ችግር (Chronic Ischemic Cardiomyopathy / CIH) ተብሎ ይጠራል። 

      አብዛኛዎቹ በረጅም ግዜ በሚከሰት የልብ ሴሎች ጉዳት የተነሳ በልብ ጡንቻ ላይ የሚፈጠር የጤና ችግር የተጠቁ በሽተኞች ከበሽታው ጋር በተገናኘ የተለያየዩ ምልክቶችን ከማሳየታቸው ከብዙ አመታት በፊት የተፈጠረ ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር ይኖራቸዋል።  

   ለረጅም ግዜ ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም መጠን በሚቀንስበት ወቅት ቀስ በቀስ የልብ ጡንቻ ሴሎች እንዲሞቱ በማድረግ በረጅም ግዜ ወስጥ የልብ ደምን የመርጨት ተግባርን ማከናወን አለመቻል ወይም የልብ ድካም በሽታ የሚከሰት ይሆናል። ይህ የጤና ችግር የሚከሰተው እድሚያቸው በገፋ ሰዎች ላይ ሲሆን ቀስ በቀስ በተለያዩ የልብ ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ ሴሎች ላይ በሚፈጠረው ጉዳት የልብ ጡንቻ የመሥራት አቅም አየቀነሰ ስለሚመጣ የልብ ድካም ብሽታ እንዲከሰት ያደርጋል።