15.1.4.1 ጀንክሽናል የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግ የልብ ምት መዛባት / junctional brady arrhythmia
የልብ የኤሌክትሪክ አንቅስቃሴ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ በሚያልፍበት ወቅት ባልተለመደ መልኩ ወይም ከሚጠበቀው ግዜ በላይ የዘገየ ሆኖ መገኘት ጀንክሽናል የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግ የልብ ምት መዛባት (junctional brady arrhythmia) ተብሎ ይጠራል። ይህ ሆኔታ አንድ አንድ ግዜ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚያልፈው የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መዘጋት (heart block) ተብሎ ይጠራል።
የልብ ኤልክትሪክ እንቅስቃሴ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ በሚያልፍበት ወቅት ባለተለመደ መልኩ የሚዘግይበት ፣ የ ፒ አር (PR) ርቀት መርዘም የሚታይበት እና የ ኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሌክስ ሁልግዜ የ ፒ አር (PR) ሴግመንትን ተከትሎ የሚመጣበት ሆኔታ አንደኛ ደረጃ ጀንክሽናል የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግ የልብ ምት መዛባት ወይም (first degree junctional bradyarrhythmia) ወይም አንደኛ ደረጃ የአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ መዘጋት (first degree heart block) ተብሎ ይጠራል። ምንም እንኳን በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚያልፈው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ከሚገባው በላይ ዝግይቶ ወደ ቬንትሪክል ውስጥ የሚደረስ ቢሆንም ዘግይቶ ወደ ቬንትሪክል የሚደርሰው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ በቬንትሪክሎች ውስጥ በማለፍ የቬንትሪክል መኮማተር ወይም የ ኪው አር ኤሰ (QRS) ኮምፕሌክስ መፍጠር ይችላል። ይህም ማለት በኤሌክትረኦካርዲዮግራም ምርመራ የፒ አር (PR) ሲግመንት መርዘም ወይም የ ፒ አር (PR ) ርቀት መጠን መጨመር የሚከሰት እንዲሁም ከያንድ አንዱም የ ፒ አር (PR) ሴግመንት ቀጥሎ የኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሊክስ የሚከትል ይሆናል።
የልብ ኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ በሚያልፍበት ወቅት ባለተለመደ መልኩ የሚዘግይበት እና በዚህም ምክንያት የ ፒ አር (PR) ርቀት መርዘም እና የኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሌክስ ሁልግዜ የ ፒ አር (PR) ሴግመንትን ተከትሎ መምጣት ወይም መታየት የማይችልበት ሆኔታ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ጀንክሽናል የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግ የልብ ምት መዛባት (second degree junctional bradyarrhythmia) ወይም ሁለተኛ ደረጃ የአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ መዘጋት (second degree heart block) ተብሎ ይጠራል። ከሚገባው በላይ ዘግይቶ ወደ ቬንትሪክል ውስጥ ከሚገባው የኤሌከትሪክ እንቅስቃሴ ውስጥ የተወሰነው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ብቻ የቬንትሪክል መኮማተር ወይም የኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሌክስን መፍጠር ስለሚችል ሁሉንም የ ፒ አር (PR) ሴግመንትን ተከትሎ የ ኪው አር ኤስ / QRS ኮምፕሌክስ ላይታይ ይችላል።
ሁለተኛ ደረጃ ጀንክሽናል የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግ የልብ ምት መዛባት የፒ አር (PR) ሴግመንት እና የ ኪው አር ኤስ ( QRS) ኮምፕሌክስ በሚኖራቸው ግንኙነት ላይ በመመስረት በሁለት የተለያዩ ምድቦች ሊከፍል ይችላል። እነዚህም ሞቤትስ አንድ (Mobitz I) እና ሞቢትስ ሁለት (Mobiths II) ተብለው ይጠራሉ።
የሞቢተስ አንድ የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ በሚፈጠርበት ወቅት የ ፒ አር (PR) ሴግመንት በተለያየ መጠን እየጨመረ በመሄድ በድንገት የ ኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሌክስ የሚጠፋበት ወይም የማይታይበት ሆኔታን ይፈጠራል። ሞቢትስ ሁለት የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ በሚፈጠርበት ወቅት ደግሞ የ ፒ አር (PR) ሴግመንት በእኩል መጠን እየረዘመ ወይም እየጨመረ ከመጣ በኋላ በድንገት የ ኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሌክስ የሚጠፋበት ወይም የማይታይበት ሆኔታን ይፈጠራል።
በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚያልፈው የልብ ኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መሉ በሙሉ በሚዘጋበት ወይም የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ በኩል ማለፍ በማይችልበት ወቅት በዋና ማለፊያ ውስጥ የሚገኙ የፐርኪንጂ ሴሎች በራሳቸው ወይም ከሳይኖአትሪያል ኖድ ቁጥጥር ውጭ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን መፍጠር እና መምራት ይጀምራሉ። ይህም ማለት አትሪየም ውስጥ የሚገኘው የኤሌክትሪክ እንቅስቅሴ በሳይኖአትሪያል ኖድ የሚመራ ሲሆን የቬንትሪክል የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ደግሞ የሚመረው አዲስ በቬንትሪኪል ውስጥ በሚፈጠረው የኤሌክትሪክ እንቅሳቃሽ የተነሳ ስለሚሆን የእትሪየም እና የቬንትሪክል መኮማተር እና መለጠጥ የተዘበራረቀ ወይም የማይገናኝ ይሆናል።
ይህ ዓይነት የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ መሉ ለሙሉ ማለፍ በማይችልበት ሆኔታ የሚከሰት የልብ የጤና ችግር ሦስተኛ ደረጃ ጀንክሽናል የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግ የልብ ምት መዛባት ወይም የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ መዘጋት (third degree junctional bradyarrhythmia ) ወይም ሦስተኛ ደረጃ የአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ መዘጋት ( third degree heart block) ተብሎ ይጠራል።
ይህ አይነት የልብ የጤና ችግር በፍጥነት መታከም በማይችልበት ወቅት ድንገተኛ ሞትን ሊያስከትል ይችላል።