19. በልብ ሽፋን ወይም በፔሪካርዲየም ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Pericardial diseases)
ልብ ከሚገኝበት የሰውነት ክፍል ውስጥ ተጣብቆ እንዲቀመጥ እና ከተለያዩ እደጋዎች እንዲጠበቅ እንዲሁም የመለጠጥ እና የመኮማተር ተግባሩ የተቀላጠፈ እንዲሆን በሚያስችሉ የልብ ሸፋኖች በሚገባ ተሸፍኖ የሚገኘ ዋና የሰውነት ክፍል ነው። ልብ እና ከልብ ጋር የተገናኙ ደምን ወደ ልብ የሚመልሱ እንዲሁም ደምን ከልብ የሚቀዱ ትልልቅ የደም ቧንቧዎች ከሚገኙበት የሰውነት ክፍል ጋር ተጣብቀው እንዲቀመጡ የሚረዳ እንዲሁም ከልብ ጋር የተገናኙ የደም ቧንቧዎችን ሽፍኖ የሚገኝው ወፍራሙ እና ከከፍተኛ ስብ የተሰራው የልብ ሽፋን የፋይብረስ የልብ ሽፋን ወይም የፋይብረስ ፔሪካርዲየም (Fibrous pericardium) ተብሎ ይጠራል። ይህ የልብ ሽፋን የውጭኛው የልብ ሽፋን ሲሆን ልብን በሚገኝበት የሰውነት ክፍል ውስጥ ተጣብቆ እንዲቀመጥ ከማድረግ በተጨማሪ ልብን እና ከልብ ጋር የተገናኙ ክፍሎችን ከአድጋ የሚከላከል የልብ ሽፋን ዓይነት ነው። ከፋይብረስ ፔሪካዲየም በሥር በኩል የሚገኘው ሌላው ባለጥንድ የልብ ሽፋን ወይም የፔሪካርዲየም ዓይነት ደግሞ ሴረስ የልብ ሽፋን ወይም ሴረስ ፔሪካርዲየም (serous pericardium) ተብሎ ይጠራል። ሴረስ ፔሪካርዲየም ሁለት የፔሪካርዲየም ዓይነቶችን የያዘ ሲሆን እነሱም የውስጠኛው የሴረስ ፔሪካርዲየም (visceral pericardium) እና የውጭኛው የሴረስ ፔሪካርዲየም (parietal pericardium) ናቸው።
የውጭኛው ሴረስ ፔሪካርዲየም ከፋይበረስ ፔሪካርዲየም ሥር የሚገኝው የፔሪካርዲየም ዓይነት ሲሆን ከውስጠኛው የሴረስ ፒሪካርዲየም በጣም አነሰተኛ መጠን ፈሳሽ በተሞላ ክፍተት ወይም በፔሪካርዲየም ክፍተት (pericardial cavity) የተለየ ሆኖ ከፋይበረሰ ፔሪካርዲየም ጋር ተጣበቆ የሚገኝው የሴረስ ፒሪካርዲየም ክፍል ነው።
ከውጭኛው ከልብ ግድግዳ ክፍል ጋር ተጣብቆ ፣ ከውጭኛው የሴረስ ፔሪካርዲየም ከላይ እንደተጠቀሰው በጣም አነስተኛ መጠን ባለው ፈሳሽ ተለይቶ የሚገኘው የልብ ሽፋን ደግሞ የውስጠኛው ፔሪካርዲየም ተብሎ ይጠራል። በውጭኛው እና በውስጠኛው ፔሪካርዲየሞች መካከል የሚገኘው እና በጣም አነስተኛ መጠን ባለው ፈሳሽ ተሞልቶ የሚገኘው ክፍል በውጭኛው እና በውስጠኛው ፔሪካርዲየሞች መካከል የሚገኝ ክፍተት ወይም የፔሪካርዲየም ክፍተት / (pericardial cavity) ተብሎ ይጠራል።
የተለያዩ በፔሪካርዲየም ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች የሚገኙ ሲሆን በፔሪካርዲየም ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ የጤና ችግሮች መካከል በፍጥነት የሚከሰት የፔሪካረዲየም ብግነት (Acute pericarditis) ፣ በውጭኛው እና በውስጠኛው የፔሪካርዲየም መካከል በሚገኘው ክፍተት ወይም በፔሪካርዲየም ክፍተት ወሰጥ የሚፈጠር የፈሳሽ መጠራቀም (pericardial effusion) ፣ በውጭኛው እና በውስጠኛው ፔሪካርዲየሞች መካከል የልብን ተግባር የሚገድብ የሚችል ከፍተኛ መጠን ያለው የፈሳሽ መጠራቀም (cardiac tamponade) እና በረጅም ጊዜ ወሰጥ የፔሪካርዲየም መወፈር ወይም መጠንከር የሚያሰከትል የፔሪካርዲየም ብግነት (Constrictive pericarditis) ዋንኞቹ ከልብ ሽፋን ወይም ከፔሪካረዲየም ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮች ናቸው።