Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

22.4. ከቂጥኝ ኢንፌክሽን ጋር በተያያዘ በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰት የጤና ችግር (Cardiovascular syphilis) 

     የቂጥኝ ኢንፊክሽን በታዳጊ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ የተለያዩ የልብ እና የደም ቧንቧ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል የሚችል የጤና ችግር ነው። የቂጥኝ በሽታ ትሪፓናማ ፓሊደም (treponema pallidum) በሚባል ተህዋሲ የሚተላለፍ የአባላዘር በሽታ ሲሆን በበሽተኛው ላይ በሚያሳያቸው የተለያዩ ምልክቶች እና ለውጦች መሰረት በተለያዩ ደረጃዎች ሊገለጽ ይችላል። የቂጥኝ በሽታ ከአንደኛ አስከ ሦስተኛ ደረጃ የሚመደብ ሲሆን በሁለተኛ እና በሦስተኛ ደረጃ መካከል የሚገኘው ክፍለ ግዜ በበሽተኛው ላይ ምንም ዓይነት ምልክት እና ለውጥ ሳይታይ  በሽታ አምጭ ተዋሲያኑ በሰውነት ውስጥ የሚቆይበት ግዜ ስለሚሆን ምንም ዓይነት ምልክት እና ለውጥ የማይታበት ክፍለ ግዜ (latent phase) ተብሎ ይጠራል። 

     በሽተኛው ለቂጥኝ ኢንፌክሽን ተጋላጭ ከሆነ በኋላ ክሦስተኛው ሳምንት ጀምሮ በመጀመሪያ የሚፈጠረው በብልት አካባቢ የሚወጣ ምንም ዓይነት ህመም የሌለው ቁስለት ( chancre) ነው። ይህም ቁስለት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ያለምንም ህክምነ በራሱ የሚደን ይሆናል። በብልት አካባቢ ከሚታየው ቁስለት ጋር የሊምፍ አጢዎች ዕብጠት ሊከሰት ይችላል። ይህ በብልት አካባቢ የሚፈጠር ቁስለት የሚታይበት የቂጥኝ ኢንፌክሽን ሆኔታ የመጀመሪያው የቂጥኝ ኢንፌክሽን ደረጃ / primary syphilis ተብሎ ይጠራል።

    የመጀመሪያ የቂጥኝ ኢንፌክሽን ደረጀ ካለፈ ከሁለት አስከ ስምንት ሳምንታት በኋላ የሚመጣው የቂጥኝ ኢንፌክሽን ምልክት ወይም ለውጥ በቆዳ ላይ የሚታይ ሽፍታ ነው። ይህ የቆዳ  ሽፍታ የአጅን እና የእግርን መዳፍ ጨምሮ በጀርባ እና በመላው ሰውነት ላይ ሊታይ ይችላል። በተጨማሪም በዚህ ግዜ ውስጥ በተለያዩ የሰውነት ከፍሎች ውስጥ የሚገኙ የሊምፍ ዕጢዎች ዕብጠት የሚከሰት ይሆናል። በተጨማሪም የሰውነት ሙቀት መጨመር ፣ በአፍ እና በጉሮሮ ውስጥ የሚፈጠር ቁስለት እና ህመም ፣ የክብደት መጠን መቀነስ እንዲሁም በራስ ወይም በቅንድብ ላይ የሚገኘው ጸጉር መርገፍ ሊከሰት ይችላል።  ይህ በሰውነት የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ የሚፈጠር የቆዳ ሽፍታ ፣ የሊምፍ ዕጢዎች ዕብጠት እና ሌሎች ምልክቶች እና ለውጦች የሚታዩበት የቂጥኝ ኢንፌክሽን ክፍለ ግዜ ሁለተኛው የቂጥኝ ኢንፌክሽን ደረጃ (secondary syphilis) ተብሎ ይጠራል። 

   ሁለተኛው የቂጥኝ ኢንፌክሽን ደረጃ ከተከሰተ በኋላ በቆዳ ላይ ታይቶ የነበረው ሽፍታ ይጠፋል። በሽተኛው በቂ ህክምና በማያገኝበት ሆኔታ ውስጥ  ከሁለተኛው የቂጥኝ ኢንፌክሽን ደረጃ በኋላ ቀጥሉ የሚመጣው ክፍለ ግዜ ምንም አይነት ምልክት እና ለውጥ የማይታይበት ክፍለ ግዜ  (latent phase) ነው። በዚህ ክፍለ ግዜ ውስጥ በሽተኛው ከአምሥት አስከ ሃያ አመታት ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ ሊኖር ይችላል።

   በቂጥኝ ኢንፊክሽን ደረጃ ውስጥ በመጨረሻ የሚመጣው ከፍለ ግዜ ሦስተኛው የቂጥኝ ኢንፌክሽን ደረጀ  (tertiary syphilis) ተብሎ ይጠራል። በተገቢው መንገድ ህክምና ሳያገኝ ለረጅም ግዜ የቆየ የቂጥኝ ኢንፌክሽን በሰውነት ላይ የከፋ ጉዳት የሚያስከትለው በዚህ ክፍለ ግዜ ውስጥ ነው። በሦስተኛው የቂጥኝ ኢንፌክሽን ደረጃ ወቅት በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ በሚገኘው ቆዳ ላይ የሚፈጠር ቁስለት ፣ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ላይ የሚከሰት ጉዳት እንዲሁም  በነርቭ ሥርዓት ላይ የሚከሰት ጉዳት የሚታይ ይሆናል።

     በሦስተኛው የቂጥኝ ኢንፌክሽን ደረጃ ወቅት የቂጥኝ አምጭ የሆነው የትሪፓኖማ ፓሊደም ህዋስ ለትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ግድግዳ ደምን በሚያደርሱ ትንንሽ የደም ቧንቧዎች ላይ በሚያስከትለው ጉዳት የተነሳ ወደ ትልቁ የደም ቅዳ ቧንቧ ግድግዳ የሚደርሰው የደም ፍሰት የሚቀንስ ይሆናል። ከሚፈጠረው የደም ፍሰት መቀነስ ወይም መቋርጥ ጋር በተገናኘ በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ግድግዳ ላይ በሚገኙ ጡንቻ ሴሎች ውስጥ በሚፈጠረው የኦክስጂን እጥረት የተነሳ በሂደት  የትልቁ ደም ቅዳ የደም ቧንቧ ግድግዳ መቅጠን እና መሳሳት ይጀምራል።  የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ግድግዳ መቀጠን እና መሳሳትን ተከትሎ የትልቁ ደም ቅዳ ግድግዳ በውስጡ የሚፈሰውን የደም ግፊት መጠን መቋቋም ስለማይችል በተጉዳው የግድግዳ ክፍል ላይ የመለጥጥ እና የመስፋት ወይም የመሰርጎድ ሆኔታ ይከሰታል። ይህ ዓይነት በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ በሚከሰት የደም ቧንቧዎች ግድግዳ መቅጠን እና መሳሳት የተነሳ የሚከሰት የደም ቧንቧ ግድግዳ መለጠጥ ወይም መስፋት ክስተት የደም ቧንቧ ግድግዳ መለጠጥ እና መስርጎድ (aneurysm) ተብሎ ይጠራል። ከላይ በተገለጸው መንገድ በትልቁ የደም ቅዳ ቧንቧ ላይ የሚከሰት የደም ቧንቧ ግድግዳ መለጠጥ እና መሰርጎድ በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ላይ የሚፈጠር የግድግዳ መለጠጥ እና መስርጎድ (aortic aneurysm) ተብሎ ይጠራል። 

 በተጨማሪም የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ግድግዳ መስፋት እና መለጠጥ ወደታችኛው የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ክፍል የሚዘልቅ እና የትልቁ ደም ቅዳ በሮች እስከሚገኙበት ክፍል ድረስ የሚጠጋ ከሆነ የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በርን የሚሰሩት ተካፋቾች በመገጣጠም መዘጋት እንዳይችሉ ስለሚያደርግ ደም ከትልቁ ደም ቅዳ ወደ ቬንትሪክል ውስጥ በተቃራኒ አቅጣጫ መመለስ እንዲችል የሚያደርገው የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መዘጋት አለመቻል (aortic regurgitation የጤና ችግር አንዲፈጠር ያደርጋል። 

   ሦስተኛው የቂጥኝ ኢንፌክሽን ደረጃ በላይኛው የትልቁ ደም ቅዳ ክፍል እና በደረት ውስጥ በሚገኘው የትልቁ ደም ቅዳ  ክፍል ግድግዳ ላይ የካልሲየም ክምችት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።

    ሦስተኛው የቂጥኝ ኢንፌክሽን ደረጃ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ላይ ከሚየስከትለው ጉዳት በተጨማሪ በማሃከላዊ የነርሽ ሥርዓት ( በአንጎል እና በህብለሰረሰር) እንዲሁም በቆዳ ለይ የከፉ የጤነ ችግሮች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። በዚህም የፊት ቆዳ ላይ የሚታዩ የማይድኑ እና ለርጅም ግዜ የሚቆዩ ቁስለቶች፣ በታችኛው የሰውንት ክፍል ላይ የሚስማ የመቆጥቆጥ እና የመድንዘዝ ስሜት ፣ በትክክል ወይም በሚገባ መራመድ አለመቻል ፣ ሽንትን መቆጣጠር ወይም ሽንትን መሽናት አለመቻል እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።