Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.1.2.4. የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ (sinus bradycardia)

  የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ የሚፈጠረው በሳይኖአትሪያል ኖድ ላይ በሚከሰት እክል ወይም በሳይኖአትሪያል ኖድ ላይ ተፅህኖ በማሳደር የልብን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የመፍጠር እና የመምራት አቅም በሚቀንሱ ሆኔታዎች የተነሳ የልብ ምት ፍጥነት በደቂቃ ከ 60 በታች ሆኖ ሲገኝ ነው። 

    ለረጅም ግዜ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የታይሮይድ ሆርሞን መጠን መቀነስ ፣ የሰውነት ሙቀት ከሚገባው በታች መቀነስ እንዲሁም የሲምፓተቲክ የነርቭ ሥርዓትን ተግባር የሚገድቡ ወይም የፓራሲምፓተቲክ የነርቭ ሥርዓትን ተግባር የሚያቀላጥፉ የተለያዩ መድኃኒቶች የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ  እንዲከሰት ከሚያደርጉ ሆኔታዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

 የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ በሚከሰትበት ወቅት በኤሌክትሮካርዲዩግራም ምርመራ ውጤት ላይ  በ አር ( R ) ሞገዶች መካከል የሚኖረው ርቀት የሚጨምር እና አያንድ አንዱ የ ኪው አር ኤስ (QRS)  ኮምፕሌክስም የ ፒ (P) ሞገድን ተከትሎ የሚከሰት ይሆናል።