16.1.5. በፍጥነት የሚከሰት የልብ ተግባር መቆም (Sudden Cardiac Arrest)
በፍጥነት የሚከሰት የልብ ተግባር መቆም (sudden cardiac arrest) በድንገት በልብ ላይ በሚፈጠር የጤና ችግር የተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ሞትን ማሰከተል የሚችል የጤና ችግር ነው። በፍጥነት የሚከሰት የልብ ተግባር መቆም ብዙሁን ግዜ የሚከሰተው የኮሮናሪ አርተሪ ሙሉ ለሙሉ መዘጋትን ተከትሎ በልብ ላይ ከሚፈጠረው ከፍተኛ ጉዳት የተነሳ ልብ እንደ አንጎል እና ልብ ያሉ ወሳኝ የሰወነት ክፍሎች የሚያሰፈልጋቸውን የደም መጠን መረጨት አለመቻል ደረጃ ላይ በሚደርሰበት ወቅት ነው።
በፍጥነት የሚከሰት የልብ ተግባር መቆም በሚከሰትበት ወቅት በፍጥነት የልብ ተግባር ማቆምን ወደ ጤነኛ የልብ ተግባር ለመመለስ የሚረዳ በሰለጠነ ባለሞያ የሚሰጥ ህክምና (cardiopulmonary resuscitation / CPR) ወይም የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን በማስተካከል የልብን ተግባር ለመመለስ የሚረዳ መሣሪያ (External defibrillators) በመጠቀም ልብን ወደ ቀደመ ተግባሩ መመለስ ይቻላል። ይህ የህክምና መንገድ የብዙዎችን ህይውት ከሞት በመታደግ ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው። በፍጥነት የሚከሰት የልብ ተግባር መቆም በተደጋጋሚ የሚከሰት የጤና ችግር ነው። ምንም አንኳን በፍጥነት የሚከሰት የልብ ተግባር መቆም አንድ አንድ ግዜ በዘር በሚተላለፉ እና በልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቅሴ ላይ እክል ከሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች የተነሳ ሊፈጠር የሚችል ቢሆንም አብዛኛውን ግዜ የሚፈጠረው በድንገት በኮሮናሪ አርተሪ ላይ በሚፈጠር የጤና ችግር የተነሳ በልብ ጡንቻ ላይ ከሚከሰት ጉዳት የተነሳ ነው።