15.1.2.5. የሳይኖአትሪያል ኖድ የልብ ምት መጠን መጨመር እና መቀነስ (Sinus tachy – brady syndrome)
የሳይኖአትሪያል ኖድ የልብ ምት መጠን መጨመር እና መቀነስ (Sick sinus syndrome) የሚፈጠረው በሳይኖአትሪያል ኖድ ውስጥ በከፊል ጉዳት በሚያደርሱ የጤና ችግሮች የተነሳ ነው። በሳይኖአትሪያል ኖድ ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ በተለያየ ግዜ የልብ ምት ፍጥነት የሚጨምር እና እንድ አንድ ግዜ ደግሞ የሚቀንስ ይሆናል። የሳይኖአትሪያል ኖድ አንድ አንድ ግዜ የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን በፍጥነት የሚፈጥር እና የሚመራ ሲሆን ሌላ ግዜ ደግሞ ቀስ ብሎ ወይም በዝግታ የሚመራ ይሆናል። ይህም ሆኔታ የልብ ፍጥነት መጠን እንዲጨምር እና እንዲቀንስ በማድረግ የልብ ምት ፍጥነት በየግዜው እንዲለዋወጥ ወይም የተዛባ እንዲሆን ያደርጋል።