Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.1.2.2. ጤነኛ የሆነ ወይም የሚጠበቅ የሳይኖአትሪያል ኖድ የልብ ምት መዛባት (physiological tachyarrhythmia)

  ከላይ እንደተገለጸው የሳይኖአትሪያል ኖድ የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የሚፈጠርበት እና የሚመራበት ዋና ክፍል ነው። ምንም አንኳን የሳይኖአትሪያል ኖድ ያለምንም ውጭያዊ ተጽህኖ የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን የመፍጠር እና የመምራት ችሎታ ቢኖረውም የአውቶኖሚክ የነርቭ ሥርዓት ክፍል የሆኑት የሲምፓተቲክ እና የፓራሲምፓተቲክ የነርቭ ሥርዓት ክፍሎች በሳይኖአትሪያል ኖድ ላይ በሚያሳደሩት ተጽህኖ የተነሳ የአውቶኖሚክ የነርቭ ሥርዓት የልብ ምት ፍጥነትን ይቆጣጠራል። የሲምፓተቲክ የነርቭ ሥርዓት በሳይኖአትሪያል ኖድ ላይ በሚያሳድረው ተጽህኖ የልብ ምት ፍጥነት እንዲጨመር ያደርጋል። የፓራሲምፓታቲክ የነርቭ ሥርዓት ደግሞ በቫገስ ነርቭ በኩል የአሲታይልኮሌን (acetylcholine) የነርቭ ሥርዓት አመላላሽ ኬሚካልን በመጠቀም በሳይኖአትሪያል ኖድ ላይ በሚያሳድረው ተጽህኖ የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ ወይም የዘገየ የልብ ምት እንዲፈጠር ያደርጋል።

የቫገስ ነርቭ ወይም አስረኛው ከአንጎል ውስጥ የሚነሳ ነርቭ (vagus nerve / cranial nerve 10) በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከሚያሳድረው ተፅህኖ በተጨማሪ በልብ ላይ በሚያሳድረው ተፅህኖ የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግ ሲሆን በአተነፋፈስ ሥርዓት ሂደት ላይ በሚያሳድረው ተፅህኖ ደግሞ አየርን ከሳንባ ለማሰውጣት በሚደረገው ሂደት ውስጥ የሚኖረው ሚና እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው። 

       የቫገስ ነርቭ ተግባር ወይም የቫገስ ነርቭ በአተነፋፈስ ሂደት ወይም አየር ወደ ውስጥ በምናስገባበት እና አየር ወደ ውጭ በምናስወጣበት ክፍለ ጌዜ ላይ የተለያየ ነው። ይህም ማለት አየር ወደ ውስጥ በምናስገባበት የእተነፋፈስ ክፍለ ግዜ ወቅት የቫገስ ነርቭ አሰራር ወይም ተጽህኖ የማሳደር አቅም የሚጨምር ስለሆነ በዚህ ክፍለ ግዜ ውስጥ የልብ ምት ፍጥነት የሚቀንስ ይሆናል። በተቃራኒው አየር ወደ ውጭ በምናስወጣበት የአተነፋፋስ ሂደት ክፍለ ግዜ ውስጥ ቫገስ ነርቭ የሚያሳድረው ተጽህኖ ስለሚጨምር የልብ ምት ፍጥነት የሚቀንስ  ይሆናል። ይህ የልብ ምት ፍጥነት ከአተነፋፈስ ሂደት ጋር በተገናኘ የመለዋወጥ ሂደት ጤነኛ የልብ ምት ፍጥነት መለዋወጥ ሆኔታ ነው።

      አንድ አንድ ግዜ የነርቭ ችግር ያለባቸው ሰዎች በተለይም ለረጅም ግዜ በስኳር በሽታ የተጠቁ ሰዎች ከስኳር በሽታ ጋር በተገናኘ በቫገስ ነርቭ ላይ በሚከሰት ጉዳት የተነሳ በአተነፋፈስ ሂደት ጋር በተያያዘ የሚከሰተው የልብ ምት መለዋወጥ ላታይባቸው ይችላል። በተጨማሪም የልብ ንቅለተከላ ህክምና ያደርጉ ሰዎች ልብ ከቫገስ ነርቭ ጋር ያልተገናኘ ስለሆነ በአተነፋፈስ ሂደት ወቅት የሚታየው የልብ ምት ፍጥነት መጠን መለዋወጥ ሊታይባቸው አይችልም።