Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.1.3.1 ከእትሪየም ውስጥ የሚነሳ  የልብ ምት ፍጥነት መጨመር (Atrial tachycardia)

   ከእትሪየም ውስጥ የሚነሳ የልብ ምት ፍጥነት መጨመር የሚፈጠረው በአትሪየም ውስጥ የሚገኙ ሴሎች ከሳይኖአትሪያል ሴሎች በላይ በሆነ ፍጥነት የልብን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መፍጠር እና መምራት ከመጀመራቸው የተነሳ ነው። ስለሆነም የልብ ምት ፍጥነት በደቂቃ ከ 150 አስከ 250 የሚሆን ሲሆን በተወሰነ የአትሪየም ክፍል ውስጥ የሚፈጠረው የኤሌክትሪክል እንቅስቃሴ አጠቃላይ የልብን የኤሌክትሪክ አንቅስቃሴ የሚመራ ይሆናል።

 ከአትሪየም የሚነሳ የልብ ምት ፍጥነት መጨመር በሚከሰትበት ወቅት በኤልክትሮካርዲዮግራም  ምርመራ ውጤት ላይ በጣም የበዙ ነገር ግን በግልፅ የሚታዩ የ ፒ (P) ሞገዶች የሚታዩ ሲሆን ከአንድ በላይ የ ፒ (P) ሞገድ ከተከሰተ በኋላ አንድ የኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሌክስ ተከትሎ የሚመጣ ይሆናል።