20.2. ከደም ግፊት መጠን መጨመር ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች
የደም ግፊት መጠን መጨመር ከረጅም ግዜ በኋላ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ ወይም በጣም በከፍተኛ መጠን ከመጨመሩ በፊት ምንም ዓይነት ምልክት እና ለውጥ ሳያስከትል ለረጅም ግዜ ሊቆይ የሚችል በሽታ ነው። መንስሄው የሚታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር መንስሄ የሆነው የጤና ችግር በሚያስከትላቸው ሌሎች ምልክቶች እና ለውጦች ሊታወቅ ይችላል። የደም ግፊት መጠን መጨመርን ተከትሎ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል ጠዋት ወይም ከእንቅልፍ በሚነቁበት ወቅት የሚጀምር የራስ ምታት ፣ የራስ ማዞር ፣ በጆሮ ውስጥ የሚሰማ የሚጮህ ድምጽ ፣ የአይታ ብዥታ ወይም የማየት ግርዶሽ ፣ ከአንፍንጫ ደም መፍሰስ ፣ በደረት አካባቢ ያለመመቸት ስሜት መሰማት ፣ የልብ ምትን መስማት ወይም ጥንካራ እና በጣም የሚመታ የልብ ምት ፣ የስሜት መሸበር ፣ የድካም ስሜት ወይም በቂ እንቅልፍ ማግኘት አለመቻል ዋንኞቹ ናቸው።
በሽተኛው በጤና አገልግሉት መስጫ ማህከል ውስጥ ሲሆን ወይም ከጤና አገልግሉት መስጫ ጣቢያ ውጭ በሚሆንበት ወቅት በሚደረግ የደም ግፊት መጠን ልኬት ጋር በተገናኘ የደም ግፊት መጠን መጨመር በተለያዩ ምድቦች ሊመደብ ይችላል። እነዚህም ምድቦች በሽተኛው በጤና አገልግሉት መስጫ ማህከላት ውስጥ በሚሆንበት ወቅት ብቻ የሚፈጠር የደም ግፊት መጠን መጨመር (white coat hypertension) እንዲሁም በሽተኛው ከጤና አገልግሉት መስጫ ማህከላት ውጭ በሚሆንበት ወቅት ብቻ የሚፈጠረደ የደም ግፊት መጠን መጨመር (masked hypertension) ናቸው።
በሽተኛው በጤና አገልግሉት መስጫ ማህከላት ውስጥ በሚሆንበት ወቅት ብቻ የሚፈጠር የደም ግፊት መጠን መጨመር (white coat hypertension) ፡ ይህ ዓይነት የደም ግፊት መጠን መጨመር የሚፈጠረው በሽተኞች በጤና አገልግሉት መስጫ ማህከላት ውስጥ በመምጣት የደም ግፊት መጠን ልኬት በሚያደርጉበት ወቅት በሚፈጠርባቸው ጭንቀት የተነሳ እንደሆነ ይታመናል። እነዚህ በሽተኞች በቤታቸው ወይም ከጤና አገልግሎት መስጫ ማህከላት ውጭ የደም ግፊት መጠን ልኬት በሚያደርጉበት ወቅት ጤነኛ የሆነ የደም ግፊት መጠን የሚኖራቸው ይሆናል።
በእነዚህ በሽተኞች ላይ በተለያዩ ቀናት እና በተለያዩ ግዜያት የሚወስዱ የደም ግፊት መጠን ልኬቶችን በመጠቀም ወይም በሽተኞች እረፍት ካደርጉ ወይም ዘና እንዲሉ ከተደረገ በኋላ በሚወሰድ የደም ግፊት መጠን ልኬት በትክክል የደም ግፊት መጠን መጨመር መከሰቱን ማረጋገጥ አስፈላጊ ይሆናል።
በሽተኛው ከጤና አገልግሉት መስጫ ማሃከላት ውጭ በሚሆንበት ወቅት የሚፈጠር የደም ግፊት መጠን መጨመር (masked hypertension) ፡ ይህ ዓይነት የደም ግፊት መጠን መጨመር ሆኔታ የሚፈጠረው የበሽተኛው የደም ግፊት መጠን በቤት ውስጥ ወይም ከጤና አገልግሉት መስጫ ማህከላት ውጭ በሚለካበት ወቅት በተደጋጋሚ የሚጨምር ሆኖ መገኘት እና የደም ግፊት መጠን በጤና አገልግግሉት መስጫ ማህከላት ውስጥ በሚለካበት ወቅት ደግሞ ጤነኛ ሆኖ በሚገኝበት ወቅት ነው።
ከላይ የተገለፁት የደም ግፊት መጠን መጨመር ዓይነቶች በሚፈጠሩበት ወቅት በስውነት ላይ ተደርጉ ለ 24 ሰዓት ውስጥ በሰውነት ውስጥ የሚኖረውን የደም ግፊት መጠን ለኬት ለማወቅ የሚረዳ መሳሪያ (ambulatory blood pressure measurement / ABMM) በመጠቀም ወይም በቤት ውስጥ በሚደረግ የደም ግፊት መጠን ልኬትን (home blood pressure measurement /HBPM) በመጠቀም በትክክል የደም ግፊት መጠን መጨመር መከሰቱን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሊሆን ይቻላል።
ከላይ የተገለፁት የደም ግፊት መጠን መጨመር ዓይነቶች መከሰታቸው በሚታወቅበት ወቅት የህይወት እና አኗኗር ሆኔታን ማሻሻል እንዲሁም በስውነት ላይ ተደርጉ ለ 24 ሰዓት በሰውነት ውስጥ የሚኖረውን የደም ግፊት መጠን ለኬት ለማወቅ የሚረዳ መሳሪያ (ABMM) በመጠቀም ወይም በቤት ውስጥ በሚደረግ የደም ግፊት መጠን ልኬትን (HBPM) በመጠቀም የበሽተኛውን የደም ግፊት መጠን መከታተል አስፈላጊ ይሆናል። በሚደረገው ክትትል የደም ግፊት መጠን እየጨመረ በሚመጣበት ውቅት አስፈላጊውን የምክር እና የመድኃኒት ህክምና መጀመር አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን መጨመር (Isolated systolic hypertension) ፡ ሌላው የደም መጠን ግፊት የመጨመር ዓይነት የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን መጨመር ሲሆን ይህ ሆኔታ የሚፈጠረው በተደጋጋሚ በሚደረግ የደም ግፊት መጠን ልኬት የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ከ 140 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ (≥ 140 mm Hg) በላይ በሚሆንበት እና የዲያስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ደግሞ በጤነኛ የደም ግፊት መጠን ወይም ከ 90 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሚርኮሪ (≤ 90 mm Hg ) በታች ላይ ሆኖ ሲገኝ ነው።
ለሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን መጨመር የጤና ችግር መንስሄ ተብሎ የሚታመነው ከእድሜ መግፋት ጋር በተገናኘ የአርተሪዎች ግድግዳ እየጠነከረ መመጣት ነው። በተጨማሪም በየደቂቃው ከልብ የሚረጨው የደም መጠን እንዲጨምር የሚያደርጉ የጤና ችግሮች ወይም ሆኔታዎችም ( የደም ማነስ (anemia) ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የታይሮይድ ሆርሞን መጠን መጨመር (hyperthyroidism) ፣ ከትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መዘጋት አለመቻል ጋር በተገናኘ ለረጅም ግዜ የቆየ በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር በኩል ደም ወደ ግራ ቬንትሪክል ተመልሶ መግባት (aortic regurgitation) እንዲሁም በአርተሪ እና በቬን መካከል የሚፈጠር ያልተገባ ቀጥተኛ ግንኙነት (AV fistula)) የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን መጨመር እንዲፈጠር ሊያደርጉ የሚችሉ ሆኔታዎች ናቸው።
የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን መጨመር ምንም ዓይነት ምልክት እና ለውጥ ሳያሳይ ለረጅም ግዜ ሊቆይ የሚችል ሲሆን ከሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን መጨመር ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለወጦች መካከል ከልብ ምት ጋር አብሮ የሚሄድ የጭንቅላት ወይም የፊት እንቅስቅሴ መታየት ፣ የራስ ምታት ፣ የራስ ማዞር ፣ የልብ ምት መሰማት ፣ በደረት ላይ የሚሰማ አለመመቸት ስሜት ፣ የትንፋሽ ማጠር እና ሌሎችም መንስሄው በሆነው የጤና ችግር ወይም ከተፈጠረው የሲስቶሊክ የደም መጠን ግፊት መጨመር የተነሳ ጉዳት ከደረሰባቸው የሰውነት ክፍሎች ጋር በተገናኝ የሚፈጠሩ ምልክቶች እና ለውጦች ሊታዩ ይችላሉ።
የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን መጨመር መከሰቱ በሚታወቅበት ወቅት የህይወት እና አኗኗር ዘይቤን ማሻሻል እና አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅትም የደም ግፊት መጠን መጨመርን ለመቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶችን በተለይም ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርጉ የታይዛይድ መድኀኒቶችን (thiazides) ወይም የካልሲየም ተቀባዮችን የሚገድቡ (CCBs) መድኃኒቶችን መጠቀም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።