Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

23.3.2. በፑልሞናሪ ቬን ውስጥ የግፊት መጠን መጨመር (Pulmonary venous hypertension)

ይህ የጤና ችግር የተጣራ ደምን ከሳንባ ወደ ግራ የልብ ክፍል በሚያደርሱ የፑልሞናሪ ቬኖች ውስጥ በሚፈጠር የግፊት መጠን መጨመር የተነሳ የሚከሰት የጤና ችግር ነው። በፑልሞናሪ ቬኖች ውስጥ የደም ግፊት መጠን መጨመር በዋናነት የሚከሰተው በግራ የልብ ክፍል ውስጥ በሚከሰት የጤና ችግር የተነሳ ነው። የሚትራል በር መጥበብ ወይም የሚትራል በር መዘጋት አለመቻል በቀኝ አትሪየም ውስጥ የሚገኘው የግፊት መጠን እንዲጨምር እና ይህም ግፊት ወደ ፑልሞናሪ ቬኖች ውስጥ በመተላለፍ በፑልሞናሪ ቬን ውስጥ የሚኖረው የግፊት መጠን እንዲጨምር ሊያድርግ ይችላል።

     በተለያዩ  የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች በተለይም በእግር ውስጥ በሚገኙ ጡንቻዎች መካከል በሚያልፉ የደም መልስ ቧንቧዎች ወይም ቬኖች ውስጥ የሚፈጠር የደም መርጋት (deep vein thrombosis) ከተፈጠረበት የደም መልስ ቧንቧ ውስጥ በመነሳት እና በደም ውስጥ በመዘዋወር ወደ ቀኝ የልብ ክፍል ወይም የቀኝ አትሪየም ከዚያም በቀኝ ቬንትሪክል ውስጥ ከደረሰ በኋላ  በፑልሞናሪ አርተሪዎች ውስጥ በመስንቀር ወይም በመቀርቀር የደም ፍሰቱን በማስተጓጎል የሚያስከትለው የጤና ችግር የፑልሞናሪ አርተሪ በደም መርጋት ስብርባሪ መዘጋት               (pulmonary embolism) ተብሎ ይጠራል። አንድ አንድ ጊዜ ከደም መርጋት በተጨማሪ በተለያዩ ምክንያቶች በደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚገባ አየር (air embolism) ወይም በአጥንት በተለይም ከዳሌ አጥንት ስብራት ጋር በተገናኘ ስብ ከጥንት መቅኔ ውስጥ በመወጣት (fat embolism) በፑልሞናሪ አርተሪዎች ውስጥ በመስንቀር የፑልሞናሪ አርተሪ እንዲጠብ እና እንዲዘጋ በማድረግ የከፋ የጤና ችግር ወይም ለሞት የሚያደርስ የከፋ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል።

      በልብ እና በሳንባ መካከል በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች የሚያስከትሏቸው ምልክቶች ለውጦች ችግሩ በተፈጠረበት ፍጥነት ፣ በፑልሞናሪ አርቲሪ ውስጥ በተሰነቀረው የስብ ወይም የደም መርጋት ስብርባሪ መጠን ፣ ችግር በደረሰበት የፑልሞናሪ አርተሪ መጠን እንዲሁም ጉዳት በደረሰባቸው የፑልሞናሪ አርተሪዎች መጠን እና ብዛት ዓይነት ሊለያይ ይችላል። 

  በመጠን ትልቅ በሆነ የደም መርጋት ወይም የስብ ክምችት ስብርባሪ የተነሳ በድንገት የሚከሰት የፑልሞናሪ አርተሪ መዘጋት በሚያጋጥምበት ወቅት ድንገተኛ የትንፋሽ ማጠር እና የደረት ህመም እንዲከሰት ያደርጋል። በፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ የሚከሰት የደም ግፊት መጠን ቀስ በቀስ አየጨመረ ሲመጣ ቀስ በቀስ የሚጀምር የትንፋሽ ማጠር ይከሰታል ።  የደም ግፊት መጠን እየጨመረ በሄደ መጠን ደግሞ የደረት ህመም እና እንቅስቃሴ በሚደርግበት ወቅት እራስን መሳት ሊያስከትል ይችላል። 

    በፑልሞናሪ ቬን ውስጥ የሚፈጠር የግፊት መጠን መጨመርን ተከትሎ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች መካከል የአየር ማጠር በተለይም ተንጋለው በሚተኙበት ወቅት የትንፋሽ ማጠር እንዲሁም በሰውነት የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ የተከማቸ ፈሳሽ ወይም የሰውነት ዕብጠት መፈጠር ዋንኞቹ ናቸው።

    በሳንባ ላይ በሚከሰት የጤና ችግር የተነሳ በደም ውስጥ የኦክስጂን መጠን እንዲቀንስ በዚህም በልብ እና በሳንባ መካከል የሚገኙ የደም ቧንቧዎች እንዲጠቡ የሚያደርጉ የሳንባ ወይም የመተንፈሻ ቧንቧዎች የጤና ችግር ላለባቸው ሰዎች የኦክስጂን ህክምና በመስጠት በልብ እና በሳንባ መካከል በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚፈጠረውን የደም ቧንቧ ጡንቻ መኮማተር እና የደም ቧንቧ መጥበብ በመቀነሰ በፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ የደም ግፊት መጠን መጨመር እንዳይከሰት መከላክል ይቻላል። 

 በሳንባ እና በአየር ቧንቧ ላይ የሚከሰቱና በደም ውስጥ የሚኖረው የኦክስጂን መጠን እንዲቀንስ ሊያደርጉ ከሚችሉ የጤና ችግሮች መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየ አየር ከሳንባ እንዳይወጣ የሚያደርጉ የጤና ችግሮች (chronic obstructive disease) ፣ መንስሄው በትክክል የማይታወቅ በሳንባ ላይ የበዛ ጠባሳ እንዲፈጠር የሚያደርግ  የጤና ችግር (idiopathic pulmonary fibrosis) እንዲሁም በሳንባ ሴሎች መካከል የሚገኙ ክፍሎችን የሚያጠቁ የጤና ችግሮች (interstitial lung diseases) ጥቂቶቹ ናቸው።