Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.1.2.3.  የሳይኖአትሪያል ኖድ የልብ ምት ፍጥነት መጨመር (sinus tachycardia)

የሳይኖአትሪያል ኖድ የልብ ምት ፍጥነት መጨመር የሚፈጠረው በሳይነስ ኖድ ላይ በሚከሰት ተጽህኖ የተነሳ የልብ ምት ፍጥነት በደቂቃ ከ 100 በላይ ሆኖ ሲገኝ ነው። ለምሳሌ ፡ አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ ፣ ከሰውነት የሙቀት መጠን መጨመር ወይም ከታይሮይድ ሆርሞን መጠን መጨመር ጋር በተገናኘ የሲምፓተቲክ የነርቭ ሥርዓት በሳይኖአትሪያል ኖድ ላይ የሚያሳድረው ተፅህኖ እንዲጨምር በማድረግ የልብ ምት ፍጥነት እንዲጨምር የሚያደርጉ ሆኔታዎች ናቸው። ጤነኛ የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መጨመር በሚከሰትበት ወቅት በኤሌክትሮካርዲዩግራም ምርመራ ውጤት ላይ የሚታየው የ ፒ (P) ሞገድ በተደጋጋሚ አንዲከሰት የሚያደርግ ሲሆን እያንድ አንዱ የ ፒ / P ሞገደም  ከ ኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሌክስ በፊት የሚመጣ ይሆናል።