Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.1.3.2. የአትሪየም ፍልተር (Atrial flutter)

  የአትሪየም ፍልተር የሚከሰተው በተወሰነ የአትሪየም ክፍል ውስጥ የሚገኙ የልብ ሴሎች  ከሳይኖአትሪያል ሴሎች ወይም ከሳይኖአትሪያል ኖድ በላይ በሆነ ፍጥነት የልብን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መፍጠር እና መምራት ከመጀመራቸው የተነሳ ሲሆን የልብ ምት ፍጥነት በደቂቃ  ከ 250 አስከ 350 ሊደርስ ይችላል። 

   የአትሪየም ፍልተር በአንድ የተወሰነ የአትሪየም ክፍል ውስጥ በሚነሳ እና በሚሽከረከር የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የሚመራ ስለሆነ በዚህ ከፍተኛ የሆነ የልብ ምት ፍጥነት የአትሪየም ጡንቻ በሚገባ መኮማተር ሰ‍ለማይችል በኤሌክትሮካርዲዩግራም ምርመራ ውጤት ላይ የ ፒ (P) ሞገድ በግልፅ የሚታይ አይሆነም። በምትኩም የመጋዝ ጥርስ የመስሉ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የፍልተር ሞገዶች (F waves) የሚታዩ ይሆናል። 

 ከበዙ የፍልተር ሞገዶች በኋላ አንድ የ ኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሌክስ የሚከትል ይሆናል።