Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

 22.1 በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን (Endocarditis) 

  ባክቴሪያ ፣ ፈንገስ ፤ ቫይረስ ወይም ሌሎች ኢንፌክሽን አምጭ የሆኑ ህዋሳት በተለያዩ መንገዶች በሰውነት ውስጥ በመግባት እና በደም ውስጥ በመዘዋወር ልብን ጨምሮ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውሰጥ ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ሊያደርጉ ይችላሉ። በደም ውስጥ በሚዘዋወሩ ኢንፌክሽን – አምጭ ተህዋሲያን የተነሳ ለኢንፌክሽን ከሚጋልጡ የሰወነት ክፍሎች ውስጥ አንዱ እና ዋንኛው ልብ ነው። 

  በደም ውስጥ በተሰራጨ ኢንፌክሽን – አምጭ ህዋስ የልብ ውስጠኛ ግድግዳ ክፍል እንዲሁም የልብ በሮችን የሚያጠቃ የልብ የየጤና ችግር በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን (infective endocarditis) ተብሎ ይጠራል። አብዛኛውን ጊዜ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን የሚከሰተው በባክቲሪያ አማካኝነት ነው። በባክቴሪያ አማካኝነት በልብ የውስጥ ግድግዳ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን በባክቲሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን (Bacterial endocarditis) ተብሎ ይጠራል። 

          በተለያየ መንገድ ወደ ሰውነት ውስጥ የሚገቡ ወይም ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚነሱ እና  በደም ውስጥ መዘዋወር የሚችሉ የባክቴሪያ ዝርያዎች በደም ቧንቧዎች በኩል ወደ ልብ በመድረስ በልብ የውስጠኛ ክፍል ፣ በልብ በሮች እና በደም ቧንቧዎች ውስጥ ኢንፌክሽን እንዲከሰት በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የልብ የጤና ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ። በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ብዙሁን ጊዜ የሚከሰተው የተለያዩ ዓይነት የልብ ችግሮች ባሉባቸው ሰዎች ላይ ነው።

     በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች ፣ የልብ በር ጥገና ወይም የልብ በር ንቅለ ተከላ ህክምና ያደረጉ ሰዎች ፣ አስቀድሞ  በልብ የውስጥ ክፍል ላይ በተፈጠረ ኢንፌክሽን የተጠቁ ሰዎች እንዲሁም ጉዳት የደረሰበት የልብ በር ያላቸው ሰዎች በልብ የውሰጠኛ ከፍል ውሰጥ ወይም በልብ በሮች ላይ ለሚፈጠር ኢንፌክን  ተጋላጭ ናቸው። የልብ ንቅለ ተከላ ህክምና ያደርጉ በሽተኞች በአፍ ፣ በጥርስ ፣ በጎሮሮ ፣ በአንጀት እና በጨጓራ እንዲሁም በሽንት ማስወገጃ ሥርዓት ክፍሎች ላይ የቀዶ ህክምና ከማደረጋቸው በፊት በልብ የወስጠኛ ክፍል ላይ ሊከሰት የሚችል ኢንፌክሽንን ለመከላከል ጸረ ባክቴሪያ መድኃኒቶችን እንዲወስዱ ይመክራል። ምክንያቱም ከነዚህ የሰውነት ከፍሎች ላይ የሚነሱ ባክቴሪያዎች  የልብ የጤና ችግር ባለባቸው ሰዎች ላይ በልብ የውሰጠኛ ከፍሎች ላይ የሚፈጠር ኢንፌከሽን እንዲከሰት ሊያደርጉ ይችላሉ። 

      በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ሊከሰት የሚችለው በተለያዩ የባክቴሪያ ዓይነቶች ሲሆን በልብ ከፍሎች ወስጥ ከሚፈጠረው ኢንፌክሽን ጋር በተገናኘ በሽተኞች የሚከሰቱ ምልክቶችን እና ለውጦችን በሚያሳዩበት ፍጥነት መሠረት በልብ የውስጠኛ ክፍል ውስጥ የሚፈጠር የባክቴሪያ ኢንፌክሽንን ለሁለት ክፍሎ ማየት ይቻላል። እነዚህም በፍጥነት በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን (Acute bacterial endocarditis)  እና ቀስ በቀስ በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን (Subacute bacterial endocarditis)  ናቸው።