Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.2.5. የፑልሞናሪ ቬን ደምን ከሳንባ  ወደ ቀኝ አትሪየም መመለስ (Total anomalous pulmonary venous return / TAPVR)

   በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት ፑልሞናሪ አርተሪ ያልተጣራ ደምን ከቀኝ አትሪየም ወደ ሳንባ የሚያደርስ ሲሆን የፑልሞናሪ ቬን ደግሞ የተጣራ ደምን ከሳንባ በመቀበል ወደ ግራ  አትሪየም ውስጥ እንዲደርስ ያደርጋል። የልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ላይ ችግር በሚያጋጥምበት ውቅት የፑልሞናሪ ቬን ደምን ካሳንባ በመቀበል ወደ ቀኝ አትሪየም እንዲያደርስ ተደርጎ ሊፈጠር ይችላል። በዚህም ምክንያት በፑልሞናሪ ቬን በኩል የሚመጣው የተጣራው ደም በቀኝ አትሪየም ውስጥ ከሚገኘው ያልተጣራ ደም ጋር ይደባለቃል። በዚህም በቀኝ አትሪየም ውስጥ የሚኖረው የደም እና የግፊት መጠን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል።  

    የቀኝ አትሪየም ውስጥ የሚገኘው የግፊት መጠን እየጨመረ ሲመጣ ደም ከቀኝ አትሪየም ወደ ግራ አትሪየም ከዚያም ወደ ግራ ቬንትሪክል ውስጥ በመግባት የተጣራው እና ያልተጣራው ደም ድብልቅ ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በትልቅ ደም ቅዳ ቧንቧ በኩል  ይረጫል። ይህ የተደባለቀ ደም ወደተለያዩ የሰወነት ክፍሎች በሚረጭበት ወቅት በደም ውስጥ የሚገኘው የኦክስጂን መጠን ዝቅተኛ ስለሚሆን ህጻናቱ በሚወለዱበት ወቅት የቆዳ ቀለም ለውጥ እና ሌሎች ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራሉ።

    የፑልሞናሪ ቬን ደምን ከሳንባ ወደ ቀኝ አትሪየም መመለስ የጤና ችግር ጋር በተያያዥነት ከሚከሰቱ ሌሎች የጤና ችግሮች መካከል የአትሪየም ሴፕተም መሽንቆር (ASD) እና የደክተስ አርተሪኦሰስ እንደተከፈተ መቅረት (PDA) ዋንኞቹ ናቸው። 

  ይህን የጤና ችግር ፅንሱ በማህጸን እያለ የኦኮካርዲዮግራም ምርመራ በመስራት መለየት የሚቻል ሲሆን ህጻኑ ከተወለደ በኋላ ደግሞ የኢኮካርዲዮግራም  ምርመራ ፣ የኤሌክትሮካርዲዮግራም  እና የደረት ራጅ ምርመራ ባማድረግ በሽታው መከሰቱን መለየት እንዲሁም ከበሽታው ጋር በተገናኙ የተፈጠሩ ለውጦችን መለየት ይቻላል። ከዚህ የጤና ችግር ጋር ለሚወለዱ ህጻናት የተፈጠረውን ምልክት እና ለውጥ ለመቆጣጠር ወይም በሽታውን ለማከም አስችኳይ የሆነ የቀዶ ጥገና ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል።