20. የደም ግፊት መጠን መጨመር በሸታ (Hypertension)
የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ በአለም ላይ በስስፋት ተሰራጭቶ የሚገኝ ሲሆን ብዙሁን ግዜ ምንም ዓይነት ምልክት እና ለውጥ ሳያሳይ ለረጅም ግዜ መቆየት ስለሚችል ብዙ ሰዎች በሽታው እንዳለባቸው ሳያወቁ ለዓመታት ከበሽታው ጋር ሊኖሩ ይችላሉ። የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ በተለያዩ ሀገሮች ውስጥ በተለያየ መጠን የሚገለጽ ሲሆን በአሜሪካን የልብ ማህበር (American Heart Association / AHA) መመሪያ መሰረት የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ ተከስቷል የሚባለው የደም ግፊት መጠን ከ 130 / 80 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሚርኮሪ (≥ 130/80 mmHg) በላይ ሲሆን ነው።
እንደ ቡድን ስምንት ብሄራዊ የጥምረት ኮሜቲ (Eighth Joint National Committee / JNC 8) መመሪያ መሰረት ደግሞ የደም ግፊት መጠን መጨመር ተከስቷል የሚባለው የደም ግፊት መጠን ከ 140 / 90 ሚሊሜትር ኦፍ ሚርኮሪ (≥ 140/90 mm Hg) በላይ ሲሆን ነው። ደም ግፊት መጠን መጨመር በሸታ መንስሄ በሚሆነው ሆኔታ ላይ በመመስረት በሁለት ምድቦች ይከፈላል። አንደኛው ምድብ መንስሄው የማይታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ (essential / primary hypertension) ሲሆን ሁለተኛው ምደብ ደግሞ መንስሄው የሚታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ (secondary hypertension) ናቸው። ወደ 90 በመቶ የሚሆነው የደም ግፊት መጠን መጨመር በሸታ በአንደኛው ምድብ ማለትም መንስሄው በማይታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ ዓይነት ውስጥ የሚመደብ ነው። ይህ ዓይነት የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ መንሻ ምክንያቱ የማይታወቅ ከመሆኑ የተነሳም መንስሄው የማይታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመርን መቆጣጠር እንጂ አስከ አሁን ባለው የህክምና መንገድ በመጠቀም ማዳን አይቻለም።
መንስሄው ለሚታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር መንስሄ የሚሆነው ነገር የሚታወቅ ስለሆነ መንስሄ የሆነውን የጤና ችግር በማከም ወይም በማስወገድ ወይም በማስተካከል የደም ግፊት መጠን መጨመርን መቆጣጠር ወይም የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታን ማዳን ይቻላል።
መንስሄው ለሚታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር መንስሄ ተብለው ከሚታውቁ የጤና ችግሮች ወይም ሆኔታዎች መካከል ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ፣ በሆርሞን ሥርዓት ላይ የሚፈጠር የጤና ችግር ( የአልዶስትሮን ሆርሞን ከመጠን በላይ መመረት ፣ የኮረቲሶል ሆርሞን ከመጠን በላይ መመረት ፣ በአድሪናል ዕጢ የሚዶላ ክፍል ወሰጥ የሚመረቱ ሆርሞኖች ከመጠን በላይ መመረት) እንዲሁም በደም ቧንቧዎች ላይ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች (በኩላሊት የደም ቧንቧዎች እና የትልቁ ደም ቅዳ አርተሪ መጥበብ ) ዋንኞቹ ናቸው።
ከላይ አንደተገለጸው የደም ግፊት መጠን መጨመር በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ምንም ዓይነት ምልክት እና ለወጥ የማያስከትል ቢሆንም የደም ግፊት መጠን መጨመር በሂደት ወይም ቀስ በቀስ በሚያስከትለው ጉዳት የተነሳ በተደጋጋሚ የከፋ ጉዳት ከሚያስከትልባቸው የሰውነት ክፍሎች መካከል አንጎል ( ስትሮክ) ፣ ልብ ( ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር ፣ የልብ ጡንቻ በከፍተኛ መጠን መጨመር ) ፤ ኩላሊት (ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ) እና አይን ( ማየት አለመቻል ወይም የእይታ ብዥታ ) ዋንኞቹ ናቸው።
የደም ግፊት መጠን መጨመርን ተከትሎ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል የራስ ምታት ፣ ማዞር ወይም እራስን መሳት ፣ በጆሮ ውስጥ የሚሰማ ድምጽ ፣ በደረት ላይ የሚሰማ ህመም ወይም ያለመመቸት ስሜት እና የትንፋሽ ማጠር ዋንኞቹ ናቸው።
የደም ግፊት መጠን በተለያዩ ግዜያት በሚደረግ ልኬት በተደጋጋሚ ከሚጠበቀው መጠን በላይ በሚጨምርበት ወቅት የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ መከሰቱን ያረጋግጣል። የደም ግፊት መጠን መጨመር በሚታይበት ወቅት በሽተኛው ለልብ እና ለደም ቧንቧ የጤና ችግሮች የሚኖረውን ተጋላጭነት ፣ ከደም ግፊት መጠን መጨመር ጋር በተገናኘ ለጉዳት የሚጋለጡ የሰውነት ክፍሎችን የጤንነት ሆኔታ በላብራቶሪ እና በሌሎች ምርመራዎች (የኩላሊትን የማጣራት አቅም ፣ በሽንት ውስጥ የሚገኘውን የፕሮቲን መጠን ለማወቅ የሽንት ምርመራ ፣ በደም ውሰጥ የሚገኘውን ኤሌክትሮላይቶች መጠን ለማወቅ የደም የላብራቶሪ ምርመራ ፣ በልብ ላይ የሚደረሰውን ጉዳት ለማወቅ የኤሌክትሮካርዲዮግራም ወይም የኢኮካርዲዩግራም ምርመራ ፣ የአይን ምርመራ) ማረጋገጥ እና ሌሎች ለደም ግፊት መጠን መጨመር መንስሄ ይሆናሉ ተብለው የሚጠረጠሩ የጤና ችግሮችን እና ሆኔታዎችን ለማወቅ የሚረዱ ምርመራዎችን ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል።
መንስሄው የማይታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታን ሙሉ ለሙሉ ማዳን የሚቻል ባይሆንም የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም የደም ግፊት መጠንን መቆጣጠር ይቻላል። ስለሆነም የደም ግፊት መጠን መጨመርን በመቆጣጠር ከደም ግፊት መጠን መጨመር ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ የጤና ችግሮችን እና ጉዳቶችን መከላከል ይችላል።
መንስሄው የማይታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ከሚረዱ መንገዶች መካከል የህይውት እና የአኗኗር ልምምድን ማስተካከል ፣ የምግብ ሆኔታን ማስተካከል ፣ የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር ፣ ዘወትር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ፣ ሲጋራ ማጤስን ማቆም ፣ የአልኮል መጠጥን መቀነስ ፣ በደም ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል ወይም የስብ መጠን መቆጣጠር ፣ በደም ውስጥ የሚገኘውን የግሎኮስ መጠን መቆጣጠር እና የተለያዩ የደም ግፊት መጠን መጨመርን ለማስተካከል ወይም ለመቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶችን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል።
የደም ግፊት መጠንን ለማስተካከል ወይም ለመቆጣጠር በብዛት በጥቅም ላይ ከሚወሉ የመድኃኒት ዓይነቶች መካከል የቤታ ተቀባዩችን የሚዘጉ መድኃኒቶች (beta blockers ) ፣ አንጂኦቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም ተግባር የሚገድቡ መድኃኒቶች (angiotensin converting enzyme inhibitors / ACEIs) ፣ የአንጂኦቲንሲን ሁለት ሆርሞን ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች (angiotensin receptor blockers። / ARBs) ፣ ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርጉ የታያዛይድ መድኃኒቶች (thiazide diuretics) ፣ የካልሲየም ተቀባዮችን ተግባር የሚገድቡ (calcium channel blockers / CCBs) መድኃኒቶች ዋንኞቹ ናቸው።
በልጆች እና በእርጉዝ ሴቶች ላይ የሚከሰት የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታን ለማከም በጥቅም ላይ የሚወሉ መድኃኒቶች በፅንሱ ወይም በልጆች ዕድገት ላይ ተፅህኖ የማያሳድሩ መሆን ይኖረባቸዋል። ከላይ ከተገለጹት መድኃኒቶች መካከል የተወሰኑት ለልጆች እና ለእርጉዝ ሴቶች የሚሰጡ አይደሉም።
መንስሄው የሚታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመርን ለማከም ለደም ግፊት መጠን መጨመር መንስሄ የሆነውን የጤና ችግር ወይም ሆኔታ ማስወገድ አስፈላጊ ይሆናል።