Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

ሀ) ግራኖሎማ የሚሰራ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ብግነት ወይም የዌገነር በሽታ (Wegner diseases) 

    በዋናነት በመተንፈሻ አካላት እና በኩላሊት ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎችን ግድግዳ በማጥቃት ብግነት ወይም ቁስለት እንዲፈጠር የሚያደርግ የጤና ችግር ነው። ይህ የጤና ችግር በዋናነት በአፍንጫ ፣ በጎሮሮ ፣ በሳንባ እና በኩላሊት ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎችን ያጠቃል። በዚህም በቀኝ እና በግራ አፍንጫ ቀዳዳዎች መካከል በሚገኘው ግድግዳ (nasal septum) ላይ የሚፈጠር መሸንቆር ፣ ለረጀም ጊዜ የቆየ ወይም በተደጋጋሚ በፊት እጥንቶች ውስጥ የሚገኙ አየር ማስተላለፊያዎች ውስጥ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ( chronic sinusitis) ፣ በተደጋጋሚ በጆሮ ውስጥ የሚፈጠር ኢንፌክሽን (otitis media) እንዲሁም የጭንቅላት ወይም የማስቶይድ አጥንት (mastoid bone) ብግነት ወይም ቁስለት እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል።

   ግራኖሎማ የሚሰራ የደም ቧንቧዎች ብግነት ወይም የዌገነር በሽታን ተከትሎ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል ከአፍንጫ የሚወጣ ጤነኛ ያልሆነ ፈሳሽ እና የአፍንጫ መታፈን ፣ ሳል እና ደም የቀላቀለ እክታ ፣ የትንፋሽ ማጠር ፣ ደም የቀላቀለ ሽንት ወይም የሽንት መቅላት ፣ በቆዳ ላይ የሚታይ ሽፍታ እና የጆሮ ኢንፌክሽን ዋንኞቹ ናቸው። 

  ግራኖሎማ የሚሰራ የደም ቧንቧዎች ብግነት መንስሄው በትክክል አይታወቅም። አንድ አንድ ጊዜ የተለያዩ ኢንፌክሽኖችን ተከትሎ ሊከሰት ይችላል።