Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

መ) የሂኖክ ሾንሊን በቆዳ ሥር የደም መድማት በሽታ ( Henoch Schoenlein Purpura) 

ይህ የደም ቧንቧ የጤና ችግር በተለየ ሆኔታ ህጻናትን የሚያጠቃ እና በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ ትንንሽ መጠን ያላቸው የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ቁስለት ወይም ብግነት እንዲፈጠር የሚያደርግ በሽታ ነው።  ይህ የጤና ችግር በተለየ ሆኔታ በቆዳ ፣ በኩላሊት ፣ በአጥንት መገጣጠሚያዎች እና በአንጀት ውስጥ የሚገኙ ትንንሽ የደም ቧንቧዎችን ያጠቃል። 

  ምንም እንኳን ይህ የጤና ችግር በማንኛውም የእድሜ ክልል ውሰጥ የሚገኙ ሰዎችን ሊያጠቃ ቢችልም በዋናነት የሚጠቃው እድሜያቸው በሁለት እና አሥራ አንድ አመት መካከል በሚገኙ ልጆች ላይ ነው። በብዛት በወንድ ልጆች ላይ የሚታይ ሲሆን በአዋቂዎች ላይ በሚከሰትበት ወቅት በህጻናት ላይ ከሚከሰተው በበለጠ የከፋ የጤና ችግር የማስከተል እድሎ እጅግ ከፍ ያለ ነው። 

   ከሂኖክ ሾንሊን በቆዳ ሥር  የደም መድማት በሽታ ጋር በተገናኘ በኩላሊት እና በአንጀት ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ ጉዳት በሚደርስበት ወቅት በሽታውን ተከትለው ሊከሰቱ የሚችሉ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል የሚያስችል ህክምና ማግኘት በጠም አስፈላጊ ይሆናል። 

የሂኖክ ሾንሊን የደም ሥር የደም መድማት በሸታ የሚከሰተው በሰውነት የበሸታ መከላኪያ ሴሎች የሚመረቱ አይነት ኤ የበሽታ መከላኪያ ፕሮቲኖች  (IgA) በቆዳ ፣ በአንጀት ፣ በኩላሊት እና በአጥንት መገጣጠሚያዎች ውስጥ የሚገኙ ትንንሽ የደም ቧንቧዎች ላይ በሚያደርሱት ቁስለት አማካኝነት ነው።

      በዙሁን ጊዜ የሂኖክ ሾንሊን በቆዳ ሥር የደም መድማት በሽታ በተከሰተ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ያለ ምንም ክፍተኛ የጤና ጉዳት ህመሙ በራሱ ይቀንሳል ። በዚህ የጤና ችግር በተጠቁ በሽተኞች ላይ ከሚታዩ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል በክንድ፣ በታፋ ፣ በእግር እና በመቀመጫ አካባቢ በቆዳ ላይ የሚታይ ሽፍታ ፣ በቆዳ ላይ ከፍ ብሎ የሚታይ የቆዳ መበለዝ ፣ የአጥንት መገጣጠሚያዎች ላይ የሚከሰት ህመም ፣ የሆድ ህመም ፣ ደም የቀላቀለ ተቅማጥ እንዲሁም በእግር እና በአጅ ላይ የሚከሰት እብጠት እና ደም የቀላቀለ ሽንት ወይም የሽንት መቅላት ዋንኞቹ ናቸው። በጥቂት በሽተኞች ላይ በኩላሊት ላይ የሚከሰተው የጤና ችግር በፍጥነት የሚከሰት የኩላሊት ጉዳት ወይም የኩላሊት መድከም ሊያስከትል ይችላል።

    ከላይ የተገለጹት ምልክቶች እና ለውጦች ከመከሰታቸው አስቀድሞ ወይም ከሁለት አስከ ሦስት ሳምንታት አስቀድሞ በመተንፈሻ አካላት ላይ በሚፈጠር ኢንፌክሽን የተነሳ እንደ ትኩሳት ፣ የራስ ህመም እና የአጥንት እና የመገጣጠሚያ ህመም የመሳሰሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ። የሂኖክ ሾንሊን በቆዳ ሥር የደም መድማት በሽታ አንድ አንድ ግዜ  በልብ ፣ በእንጎል እና በሳንባ ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

    የሂኖክ ሾንሊን በቆዳ ሥር የደም መድማት በሽታን መከሰት ለማወቅ የበሽታውን ታሪክ መረዳት ፣  በአካላዊ ምርመራ የሚታዩ እንደ የቆዳ ሽፍታ ፣ በቆዳ ላይ ከፍ ብሎ የሚታይ የቆዳ መበለዝ ወይም በቆዳ ሥር መድማት  ፣ የሽንት ቀለም መቀየር ያሉ ምምልክቶችን መለየት አስፈላጊ ይሆናል። በተጨማሪም የከፋ ጉዳት ከተከሰተበት የሰውነት ክፍል ማለትም ከቆዳ ወይም ከኩላሊት ላይ በሚወሰድ ናሙና የፓቶሎጂ ምርመራ በማድረግ በሽታውን በትከከል ማውቅ ይቻላል።