Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

16.1.4.1. የፑልሞናሪ አርተሪ በር መጥበብ (pulmonary stenosis)

  የፑልሞናሪ አርተሪ በር መጥበብ ብዙሁን ግዜ የሚከሰተው በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት ከሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ ሲሆን በተለያዩ ከሮሞዞሞች ላይ ከሚፈጠሩ ለውጦችም ጋር በተያያዘ ሊክሰት ይችላል። በልብ ውስጥ የሚፈጠሩ ዕብጠቶች (tumors) ወይም በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ከሚፈጠሩ እና ወደ ልብ ክፍሎች ወሰጥ ከሚሰራጩ  ዕብጠቶች (carcinoid) ጋር በተገናኘ የፑልሞናሪ በር አርተሪ መጥበብ ሊፈጠር ይችላል። 

  የፑልሞናሪ አርተሪ በር መጥበብ በሚከሰትበት ወቅት ከቀኝ ቬንትሪክል ውስጥ የሚረጨው ደም ሙሉ በሙሉ ወደ ፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ ማለፍ አይችልም። ስለሆነም በቀኝ ቬንትሪክል ውስጥ የሚገኘው የደም እና የግፊት መጠን ይጨምራል። የቀኝ ቬንትሪክል ደምን በከፍተኛ ጎልበት በመግፋት ወደ ፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ ለማስገባት በሚያደርገው ጥረት የቀኝ ቬንትሪክል ግድግዳ እየወፈረ ይመጣል።

  መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የፑልሞናሪ አርተሪ በር መጥበብ የልብ የጤና ችግር ምንም ዓይነት ምልክት እና ለውጥ ሳያሳይ ለረጅም ግዜ መቆየት የሚችል ሲሆን በሽታው አየጠና ሲመጣ ወይም ከግራ ቬንትሪክል የሚረጨው የደም መጠን በከፍተኛ መጠን በሚቀንስበት ወቅት ወደ ልብ ክፍሎች በተለይም ለግራ ቬንትሪክል የሚያስፈልገው የደም መጠን ወደ ግራ ቬንትሪክል ከሚደርሰው የደም መጠን ጋር ስለማይጣጣም በደረት ላይ የሚሰማ ህምም ፣ የትንፋሽ ማጠር እና አጠቃላይ የድካም ስሜት መሰማት ሊከሰት ይችላል።

   በአካላዊ ምርመራ ወቅት ቬንትሪክል በሚኮማተርበት ወቅት በፑልሞናሪ በር ላይ የሚሰማ ጤነኛ ያለሆነ የልብ ምት ድምጽ ( systolic murmur ) ፣ ዓይነት አራት ተጨማሪ የልብ ምት ድምጽ (S4) እንዲሁም በግራ የልብ ክፍል ላይ የሚፈጠር የልብ ድካም በሽታን ተከትሎ የሚፈጠሩ ምልክቶች እና ለውጦች ሊከሰቱ ይችላሉ።

  የኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ የቀኝ ቬንትሪክል መወፈርን እና የቀኝ አትሪየም መጠን መጨመርን ሊያሳይ  ይችላል። በደረት ራጅ ምርመራ የቀኝ ቬንትሪክል እና የቀኝ አትሪየም መጠን መጨመር ሊታይ ይቻላል። በኢኮካርዲዮግራም ምርመራ የፑልሞናሪ አርተሪን በር መጠን እና የመሥራት አቅምን መለካት ፣ በፑልሞናሪ በር በኩል የሚያልፈውን የደም እና የግፊት መጠን ለውጥን እና በቬንትሪክል ውስጥ የሚኖረውን የደም መጠን ማወቅ ይቻላል።

     በፑልሞናሪ አርተሪ ወስጥ የሚኖረውን የደም ግፊት መጠን መጨመርን ለማስተካከል እና በፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ የሚፈጠረውን የግድብት መጠን ለመቀነስ የሚረዱ መድኃኒቶችን መጠቀም ወይም የቀዶ ጥገና ህክምና ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል። ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርጉ መድኃኒቶችን መጠቀም በግራ የልብ ክፍል የሚከሰት የልብ ድካምን ተከትሎ የሚፈጠሩ ምልክቶችን እና ለውጦችን ለመቀነስ ይረዳል። 

የከፋ የፑልሞናሪ በር መጥበብ በሚከሰትበት ወቅት በቀዶ ጥገና ህክምና የፑልሞናሪ በርን መጠገን ወይም የፑልሞናሪ በርን መቀየር አስፈላጊ ሊሆን  ይችላል።