20.5. የደም ግፊት መጠን መጨመርን ለመቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶች (pharmacologic therapy)
የደም ግፊት መጠን መጨመርን ያለ መድኃኒት ሕክምና መቆጣጠር በማይቻልበት ወቅት ወይም የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ በሚሆንበት ወይም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከደም ግፊት መጠን መጨመር ጋር በተገናኘ ጉዳቶች በሚፈጠሩበት ወቅት የተለያዩ የደም ግፊት መጠንን ለመቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶችን መጠቀም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
ለደም ግፊት መጠን መጨመር ህክምና ተመራጭ የሚሆነው የመድኃኒት ዓይነት እና መጠን በተለያዩ ሆኔታዎች ላይ የሚመሰረት ይሆናል። ከእነዚህም ሆኔታዎች መካከል የበሽተኛው እድሜ ፣ የደም ግፊት መጠኑ የሚገኝበት ደረጃ ፣ ከደም ግፊት መጠን መጨመር ጋር በተገናኘ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የተፈጠረ ጉዳት ፣ በበሽተኛው ላይ የተከሰቱ ሌሎች ተጓዳኝ የጤና ችግሮች ፣ በሽተኛው የሚወስዳቸው ሌሎች የመድኃኒት ዓይነቶች ፣ እርግዝና እና የጡት ማጥባት ሆኔታ ዋንኞቹ ሆኔታዎች ናቸው።
ለደም ግፊት መጠን መጨመር በመጀመሪያ ደረጃ የሚሰጡ መድኃኒቶች (initial medications)
|
የመድኃኒት ምድብ አይነቶች |
በዚህ መድብ ውስጥ የሚካተቱ መድኃኒቶች |
የጎንዮሽ ጉዳቶች |
|
የመጀመሪያ ተመራጭ መድኃኒቶች |
||
|
አንጂኦቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም ተግባር የሚገድቡ መድኃኒቶች (ACEIs) |
ሊሲኖፕሪል (Lisinopril) ፣ ኢናላፕሪል (Enalapril) ፣ ካፕቶፕሪል (Captopril) ለስኳር በሽተኞች እንዲሁም ለኩላሊት በሽተኞች ተመራጭ መድኃኒቶች ናቸው።
እርጉዝ ሴቶች እና የሚያጠቡ እናቶች በዚህ ምድብ ውስጥ የሚመደቡ መድኃኒቶችን እንዲጠቀሙ አይመከርም።
|
ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ደረቅ ሳል ፣ የደም ግፊት መጠን መቀነስ ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የፖታሲየም መጠን መጨመር ፣ በሽንት መልክ የሚወገደው የፕሮቲን መጠን መጨመር ፣ በፅንስ አፈጣጠር ላይ ጉድለት መፈጠር ፣ በምላስ ላይ የጣህም ለውጥ ፣ በቆዳ ላይ የሚፈጠር ሽፍታ ፣ በሰውነት ክፍሎች ላይ የሚፈጠር እብጠት (angioedema) |
|
የአንጂኦቲንሲን ሁለት ሆርሞን ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች (ARBs) |
ሎሳርታን (Losartan)፣ ቫልሳርታን (valsartan) (ለስኳር በሽተኞች እንዲሁም ለኩላሊት በሽተኞች ተመራጭ መድኃኒቶች ናቸው።) |
የደም ግፊት መጠን መቀነስ ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የፖታሲየም መጠን መጨመር ፣ በፅንስ አፈጣጠር ላይ ጉድለት መፈጠር ፣ በምላስ ላይ የሚፈጠር የጣህም ለውጥ ፣ በቆዳ ላይ የሚፈጠር ሽፍታ ፣ በሰውነት ክፍሎች ላይ የሚፈጠር እብጠት (angioedema) |
|
ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርጉ የታያዛይድ መድኃኒቶች (thiazide diuretics) |
ክሎርታሊዶን (Chlorthalidone) ፣ አይድሮክሎርታያዛይድ (hydrochlorothiazide) |
በደም ውስጥ የሚገኘው የፖታሲየም ፣ የሶዲየም እና የማግኒዚየም መጠን መቀነስ በደም ውስጥ የሚገኘው የካልሲየም፣ የግሎኮስ እና ዩሪክ አሲድ መጠን መጨመር ሚታቦሊክ አሲዶሲስ (metabolic acidosis) |
|
በደም ቧንቧዎች ላይ የሚገኙ የካልሲየም ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች (Dihydropyridine CCBs) |
አሚሎዲፒን (amlodipine) ፣ ኒፌዲፒን (Nifedipine)
|
የራስ ምታት ፣ በእግር ላይ የሚፈጠር አብጠት ፣ የሰውነት ቆዳ መቅላት ወይም ደም መልበስ (flushing) ፣ የልብ ምት ፍጥነት መጠን መጨመር |
|
በደም ቧንቧ ወይም በልብ ሴሎች ላይ የሚገኙ የካሊየም ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / None Dihdropyridol CCBs |
ዲልቲአዜም (Diltiazem) ፣ ቬራፓሚል (Verapamil)
|
የልብ ጡንቻ የመኮማተር አቅም መቀነስ ፣ የልብ ምት ፍጥነት መጠን መቀነስ ፣ የደድ መወፈር ወይም የድድ መጠን መጨመር ቬራፓሚል /Verapamil – የአይነ ምድር ድርቀት ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የፕሮላክቲን መጠን መጨመር በደም ውስጥ የሚገኘው የካልሲየም እና የኮሌስትሮል መጠን መጨመር የደም ማነስ ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የፕሌትሌት መጠን መቀነስ |
|
ሁለተኛ ተመራጭ መድኃኒቶች |
||
|
የቤታ ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / beta blockers
|
የአልፋ እና የቤታ ተቀባዩችን ሳይለዩ የሚገድቡ መድኃኒቶች ፡ ካርቬዲሎል / Carvedilol ፣ ላቤቶሎል / labetalol
የቤታ አንድን እና የቤታ ሁለት ተቀባዩችን የሚገድቡ መድኃኒቶች ፡ ናዶሎል / Nadolol ፣ ፕሮፕራኖሎል / Propranolol
በልብ ሴሎች ላይ የሚገኙ ቤታ አንድ ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች ፡ አቴኒሎል / Atenolol ፣ ቢሶፕሮሎል / Bisoprolol ፣ ሜቶፕሮሎል / Metoprolol |
የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ ፣ የልብ ምት መዛባት ፤ የደም ግፊት መጠን መጨመር ፣ የሰውነት ድካም ስሜት ፣ ድብርት ፣ እንፍርፍሬት ፣ የእንቅልፍ ማጣት ፣
የአየር ቧንቧ መጥበብ ፣ የብልት መገተር አቅም መቀነስ ወይም ስንፈተ ወሲብ ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የትራይግላይሲራይድ እና የግሎኮስ መጠን መጨመር
|
|
ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርጉ የሎፕ መድኃኒቶች / loop diuretics |
ፉርሴማይድ / Furosemide ቶርሴማይድ / Torsemide
|
በደም ውስጥ የሚገኘው የፖታሲየም ፣ የሶዲየም እና የማግ ኒዚየም መጠን መቀነስ በደም ውስጥ የሚገኘው የግሎኮስ እና ዩሪክ አሲድ መጠን መጨመር ሚታቦሊክ አሲዶሲስ በጆሮ ውስጥ በሚገኙ ሴሎች ላይ የሚፈጠር ጉዳት ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የካሊስየም መጠን መቀነስ የሰውነት ፈሳሽ መጠን መቀነስ |
|
በሰውነት ውስጥ የሚገኘው የፖታሲየም መጠን እንዲጨምር የሚያደርጉ ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርጉ መድኃኒቶች / K sparing diuretics |
የአልዶስቲሮን ሆርሞንን ተግባር የሚገድቡ፡ ስፓይሮኖላክቶን / Spironolactone ኢፕሌሬኖን / Eplerenone በኩላሊት የመሰብሰቢያ ቧንቧ የሴል ሸፋን ላይ የሚገኙ የሶዲየም በሮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች ፡ አሚሎይድ (Amiloride)፣ ትሪአምቴሬን (Triamterene) |
በደም ውስጥ የሚገኘው የፖታሲየም መጠን መጨመር ስፓይሮኖላክቶን ፡ በወንዶች – የወንድ ብልት መገተር አለመቻል ፣ የጡት መጠን መጨመር በሴቶች – የወር አበባ መቅረት
|
|
የሪኒን ኢንዛይምን ተግባር የሚገድቡ መድኃኒቶች / renin inhibitors |
አሊስኪሬን ( Aliskiren) |
የደም ግፊት መጠን መቀነስ ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የፖታሲየም መጠን መጨመር ፣ በፅንስ አፈጣጠር ላይ ጉድለት መፈጠር ፣የጣህም ለውጥ ፣ በቆዳ ላይ የሚፈጠር ሽፍታ ፣ በሰውነት ክፍሎች ላይ የሚፈጠር እብጠት / angioedema ፤ ትቅማጥ |
|
አይነት አንድ የአልፋ ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / alpha 1 blockers |
ፕራዞሲን (Prazosin) ዶክሳዞሲን (Doxazosin) – ከእድሜ መግፋት ጋር በተገናኘ የፕሮስቴት መጠን መጨመር ለሚከሰትባቸው ሰዎች ተመራጭ ነው። |
የደም ግፊት መቀነስ ፣ ከመተኛት ወይም ከመቀመጥ በመነሳት ወይም በመቆም ከሁለት ደቂቃ በኃላ በሚደረግ የደም ግፊት መጠን ልኬት የደም መጠን መቀነስ (orthostatic hypotension) |
|
አይነት ሁለት የአልፋ ተቀባዮችን የሚያነቃቁ መድኃኒቶች/ Alpha 2 Agonists |
ክሎኒዲን / Clonidine ፣
ሜታይልዶፓ / Methyldopa
|
የደም ግፊት መጠን መቀነስ ፣ የደም ምት ፍጥነት መቀነስ ፣ የአፍ ድርቀት
የፕሮላክቲን ሆርሞን መጠን መጨመር ፤ የሰውነት እብጠት ፣ የእንቅልፍ ስሜት ውስጥ መግባት |
|
በቀጥታ የአርተሪ የደም ቧንቧዎች እንዲሰፉ የሚያደርጉ መድኃኒቶች |
ሃይድራላዚን (hydralazine) ፣ ሚኖክሲዲል (Minoxidil) |
የደም ግፊት መጠን መቀነስ ፣ የልብ ምት ፍጥነት መጨመር ፣ በቆዳ ላይ የሚፈጠር ሽፍታ |
ለደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ በመጀመሪያ ደረጃ የሚሰጡ መድኃኒቶችን ለመመረጥ የሚከትሉትን ሆኔታዎች ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
- የሲሰቶሊክ ደም ግፊት መጠን ከ 130 – 139 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ (130–139 mm Hg) ወይም የዳያስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ከ 80 – 89 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ (80–89 mm Hg) ወይም ደረጃ አንድ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሚከስትበት ወቅት በአንድ መድኃኒት ህክምናውን መጀመር አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
- የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ከ 140 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ በላይ (≥ 140 mm Hg) ወይም የዲያስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ከ 90 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ ( ≥ 90 mmHg ) ወይም ከጤነኛው የደም ግፊት መጠን በላይ የደም ግፊት መጠን ከ 20 / 10 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ በላይ (> 20/10 mmHg ) በሚጨምርበት ወቅት ከአንድ በላይ መድኃኒቶችን መጀመር አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። በብዛት በአንድ ላይ ከሚጀመሩ መድኃኒቶች መካከል አንጂቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም ተግባር የሚገድቡ መድኃኒቶች (ACEIs) ወይም የአንጂኦቲኒሲን ሁለት ሆርሞን ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች (ARB) እና ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርጉ የታይዛይድ መድኃኒቶች (thiazides) ወይም የካልሲየም በሮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች (CCBs) ዋንኞቹ ናቸው።
- በተጨማሪም የበሽተኛውን እድሜ እና ሌሎች ተጓዳኝ የጤና ችግሮችን ከግንዛቤ ማስገባት አስፈላጊ ይሆናል።
|
ተያያዥ የጤና ችግሮች |
የሚመከር የህክምና አይነት |
|
ስትሮክ ወይም ከ 24 ሰዓት በታች ለሆነ ግዜ ወደ አንጎል ከሚደርሰው የደም መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ በነርቭ ሥርዓት ላይ የሚከሰት ጉዳት / TIA
|
የመጀመሪያ ተመራጭ መድኃኒት አንድ መድኃኒት ፡ የታያዛይድ መድኃኒቶች ፣ አንጂኦቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም የሚገድቡ መድኃኒቶች /ACEIs ፣ የአንጂኦቲንሲን ሁለት ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / ARBs ከአንድ በላይ መድኃኒቶች ፡ የታይዛይድ መድኃኒቶች እና አንጂኦቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም ተግባር የሚገድቡ መድኃኒቶች ወይም የአንጂኦቲንሲን ሁለት ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች መጠቀም የህክምና ጎል ፡ የደም ግፊት መጠን ከ 130 / 80 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ በታች ( < 130/80 ) እንዲሆን ማድረግ |
|
ወደ ልብ ከሚደርሰው የኢክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ በሽታ / stable ischemic heart disease
|
የመጀመሪያ ተመራጭ መድኃኒቶች ፡ አንጂኦቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም የሚገድቡ መድኃኒቶች / ACEIs ወይም የአንጂኦቲንሲን ሁለት ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / ARBs እና የቤታ ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / beta blockers ተጨማሪ መድኃኒቶች ፡ የካሊስየም ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / CCBs ፣ ታያዛይድ ወይም የአልዶስቲሮንን ሆርሞንን ተግባር የሚገድቡ መድኃኒቶች / aldosterone antagonist የህክምና ጎል : የደም ግፊት መጠን ከ 130 / 80 <ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ በታች ( 130/80 mm Hg) እንዲሆን ማድረግ |
|
ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ / chronic renal diseases |
የመጀመሪያ ተመራጭ መድኃኒቶች ፡ አንጂኦቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም የሚገድቡ መድኃኒቶች / ACEIs ወይም የአንጂኦቲንሲን ሁለት ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / ARBs . የህክምና ጎል ፡ የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠ ከ 120 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ በታች (< 120 mm Hg) እንዲሆን ማድረግ |
|
የስኳር በሽታ
|
የመጀመሪያ ተመራጭ መድኃኒቶች ፡ አንጂኦቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም የሚገድቡ መድኃኒቶች / ACEIs ወይም የአንጂኦቲንሲን ሁለት ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / ARBs . የህክምና ጎል : < 130/80 mm Hg |
|
የልብ ድካም / heart failure / HF
|
የመጀመሪያ ተመራጭ መድኃኒቶች ፡ ከልብ የሚረጨው የደም መጠን እንዲቀንስ የሚያደርግ የልብ ድካም / systolic HF – የቤታ ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች ( ካርቬዲሎል / Carvedilol ፣ ሜቶፕሮሎል /metoprolol ፣ ቢሶፕሮሎል / bisoprolol ) ፤ የታይዛይድ መድኃኒቶች ፣ የአልዶስቲሮን ሆርሞንን ተግባር የሚገድቡ መድኃኒቶች ፣ አንጂኦቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም የሚገድቡ መድኃኒቶች / ACEIs ፣ የአንጂኦቲንሲን ሁለት ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / ARBs የህክምና ጎል ፡ < 130/80 mm Hg ወደ ልብ ከሚገባው ደም ውስጥ ከልብ የሚረጨው የደም መጠን እንዲቀንስ የሚያደርግ የልብ ድካም / diastolic HF : ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርጉ የታይዛይድ መድኃኒቶች ወይም አንጂኦቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም የሚገድቡ መድኃኒቶች / ACEIs ፣ የአንጂኦቲንሲን ሁለት ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / ARBs የህክምና ጎል ፡ የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ከ 130 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ በታች (< 130 mm Hg) እንዲሆን ማድረግ |
|
የአስም በሽታ
|
የመጀመሪያ ተመራጭ መድኃኒቶች : የአንጂኦቲንሲን ሁለት ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / ARBs ፣ የካልሲየም ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / CCBs ፣ፈሳሽ ከሰውነት የሚያደርግ የታያዛይድ መድኃኒቶች የቤታ ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች ማስወገድ አስፈላጊ ይሆናል። |
|
የአጥንት መሳሳት / Osteoporosis |
የመጀመሪያ ተመራጭ መድኃኒቶች : ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርጉ የታያዛይድ መድኃኒቶች |
|
በደም ውስጥ የሚገኘው የዩሪክ አሲድ በአጥንት መገጣጠሚያዎች ውስጥ መከማቸት እና ብግንት መፈጠር / gout |
የመጀመሪያ ተመራጭ መድኃኒቶች: የአንጂኦቲንሲን ሁለት ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / ARBs ፤ አንጂኦቲንሲን አንድን ወደ አንጂኦቲንሲን ሁለት የሚቀይረውን ኢንዛይም የሚገድቡ መድኃኒቶች / ACEIs እና የካሊስየም ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች / CCBs ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርግ የታያዛይድ መድኃኒቶችን ማስወገድ ያስፈልጋል። |
|
ሚግሪይን (Migraine) |
የመጀመሪያ ተመራጭ መድኃኒቶች : የቤታ ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች (beta blockers) ወይም የካሊስየም ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶች (CCBs) |
4. በሽተኞች ከሚወስዷቸው እና የደም ግፊት መጠን መጨመርን ለመቆጣጠር ከሚረዱ መድኃኒቶች ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን መከታተል እና አስፈላጊውን ህክምና ማግኘት አስፈላጊ ይሆናል።