18.2. የልብ ጡንቻ ከመጠን በላይ መወፈር (Hypertrophic Cardiomyopathy)
የግራ ቬንትሪክል ጡንቻ ከመጠን በላይ በሚወፍርበት ወቅት በበቂ መጠን መለጠጥ እና ደምን ከአትሪየም መቀበል አይችልም። ይህም ሆኔታ የግራ ቬንትሪካል ደምን የመቀበል አቅም እንዲቀንስ ያደርጋል። ምንም አንኳን ወደ ቬንትሪክል ውስጥ የሚገባው የደም መጠን የሚቀነስ ቢሆንም ከቬንትሪክል ጡንቻ መወፈር ጋር በተገናኘ ከሚፈጠረው የግፊት መጠን መጨመር የተነሳ ወደ ቬንትሪክል ከሚገባው ደም ውስጥ በያንድ አንዱ የቬንትሪክል መኮማተር ወቅት ከቬንትሪክል የሚረጨው የደም መጠን የሚጨምር ይሆናል። የግራ ቬንትሪክል በከፍተኛ ደረጃ የመኮማተር አቅም ጋር በተገናኘ የግራ ቬንትሪክል ከተቀበለው የደም መጠን ውስጥ ከሚጠበቀው በላይ የሚሆነውን የደም መጠን ወደ ተለያዩ የሰወነት ክፍሎች እንዲደረስ መርጨት ይችላል።
የልብ ጡንቻ ከመጠን በላይ መወፈር የጤና ችግር ጋር በተገናኘ የሚፈጠር እና በግራ እና በቀኝ ቬንትሪክሎች መካከል የሚገኘው ግደግዳ ወይም የቬንትሪክል ሴፕተም ከመጠን በላይ መወፈር የተነሳ ደም ከቬንትሪክል እንዳይወጣ በማድረግ ከልብ የሚረጨው የደም መጠን እንዲቀንስ የሚያደርግ የጤና ችግር የልብ ጡንቻ ከመጠን በላይ መወፈር የተነሳ ከቬንትሪክል የሚወጣውን ደም ፍሰት መዘጋት የሚያስከትል የልብ የጤና ችግር (hypertrophic obstructive cardiomyopathy) ተብሎ ይጠራል።
ከግራ ቬንትሪክል ጡንቻ መወፈር ጋር በተገናኘ ከቬንትሪክል የሚወጣውን የደም ፍሰት መዘጋት የሚከሰተው በሁለቱ ቬንትርክሎች መካከል የሚገኘው ግድግዳ ወይም የቬንትሪክል ሴፕተም (ventricular septum) ከተቀረው የልብ ክፍል በበለጠ ሆኔታ ከመወፈሩ የተነሳ ነው። የቬንትሪክል ሴፕተም ውፍረት ደም ከግራ ቬንትሪክል ወደ ትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ውስጥ እንዳያልፍ በማድረግ ከቬንትሪክል የሚረጨው የደም መጠን በከፍተኛ መጠን እንዲቀንስ ሊያድርግ ይችላል። የልብ ጡንቻ ከመጠን በላይ መወፈር የተነሳ ከቬንትሪክል የሚወጣውን ደም ፍሰት መዘጋት የሚያስከትል የልብ የጤና ችግር ብዙሁን ጊዜ የሚከሰተው በዘር መል ወይም ክሮሞዞም ላይ ከሚከሰት ለውጥ ወይም ጉዳት የተነሳ ሲሆን እንድ አንድ ጊዜ በማንኛውም ሰው ላይ ሊከሰት ይችላል።
በበክሮሞዞም 14 (chromosome 14) ላይ በሚከሰት ለውጥ ወይም ጉዳት ምክንያት በዘር የሚተላለፍ እና የልብ የጤና ችግር የቬንትሪክል ሴፕተም ከሌላው የቬንተሪክል ግድግዳ ከፍል በበለጠ መጠን እንዲወፍር በማድረግ ከቬንትረክል የሚወጣው የደም ፍሰት እንዲዘጋ ሊያደርግ ይችላል።
የልብ ጡንቻ ከመጠን በላይ መወፈር በሚከሰትበት ወቅት ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶቸእ እና ለውጦች መካከል የትንፋሽ ወይም የአየር ማጠር ፣ የልብ ጡንቻ መጠን መጨመርን ተከትሎ ወደ ልብ ሴሎች ከሚደርሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚከሰት በደረት ላይ የሚሰማ ህመም ፣ ከፍተኛ ሥራ ወይም አካላዊ እንቅስቃሴ በሚሰራበት ወቅት እራስን መሳት እንዲሁም የልብ ምት መሰማት ዋንኞቹ ናቸው። በተጨማሪም ከልብ ምት ጋር የሚሰሙ አራተኛው ተጨማሪ የልብ ምት ድምጽ ሊሰማ ይችላል። በዚህ አይነት የልብ የጤና ችግር የተጠቁ በሽተኞች ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳዩ በወጣትነት እደሜያቸው በድንገት የሚክሰት የሞት አደጋ ሊያስከትል ይችላል።
የልብ ጡንቻ ከመጠን በላይ መወፈር የልብ የጤና ችግር መከሰቱን ለማወቅ የተለየዩ የምርመራ መንገዶችን መጠቀም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። በኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ የግራ ቬንትሪክል መወፈር እና በግራ ቬንትሪክል ላይ የሚታይ የልብ ምት መዛባት ሊታይ ይችላል። በኢኮካርዲዮግራም ምርመራ የግራ ቬንትሪክል መወፈርን ፣ ቬንትሪክል በሚኮማተርበት ወቅት የሚታይ የሚትራል በር ክፍሎች እንቅስቃሴ እና ያል ግዜው የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መዘጋት ሊታይ ይችላል።
የልብ ጡንቻ ከመጠን በላይ መወፈርን የሚያስክከትል የጤና ችግርን ለማከም ከሚረዱ የህክምና መንገዶች መካከል በልብ ላይ የሚገኙ የቤታ አንድ ተቀባዮችን የሚገድቡ መድኃኒቶችን (beta 1 blockers) ፣ የካልሲየም በሮችን የሚዘጉ መድኃኒቶች (calcium channel blockers) ፣ የልብ ምት መዛባትን ለማስተካከል የሚረዳውን መሳሪያ መጠቀም ወይም የቀዶ ጥገና ህክምናን በመጠቀም ከመጠን በላይ በመጠን የጨመረውን የቬንትሪክል ግድግዳ ክፍል በመቀነስ (septoplasty) ደም ከግራ ቬንትሪክል ወደ ትልቁ የደም ቧንቧ ውስጥ እንዲያልፍ እና የተዘጋው የደም ፍሰት እንዲስተካከል ማድረግ ይቻላል።