Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

20.1. የደም ግፊት መጠን (blood pressure) 

     የደም ግፊት መጠን ማለት ከልብ የሚረጨው የደም መጠን በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ በሚያሳድረው ጫና የተነሳ በደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የግፊት መጠን ማለት ነው። በደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠረው የደም ግፊት መጠን ደም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ እንዲንቀሳቀስ ወይም እንዲፍስ የሚያደርገው ሃይል ነው። 

   የደም ግፊት መጠን የሚለካው እና የሚገለጸው በሁለት ቁጥሮች ነው። የመጀመሪያው ወይም ከላይ በኩል የሚገኘው ወይም የሚቀመጠው ቁጥር ቬንትሪክል በሚኮማተርበት ወቅት ወይም ከቬንትሪክል የሚረጨው ደም በአርተሪ የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠረውን የግፊት ሃይል የሚገለጽ ሲሆን ይህም ግፊት የሴስቶሊክ የደም ግፊት መጠን (systolic pressure) ተብሎ ይጠራል። 

 ሁለተኛው ወይም ከታች በኩል የሚቀመጠው ቁጥር ደግሞ የቬንትሪክል ጡንቻ በሚለጠጥበት ወይም ደምን ከአትሪየም በሚቀበልበት ወቅት በአርትሪ ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚፈጠረውን የግፊት መጠን የሚገልጽ ነው። ይህም የግፊት መጠን የዲያሰቶሊክ የግፊት መጠን (diastolic pressure) ተበሎ ይጠራል። ጤነኛ የደም መጠን ግፊት በእድሜ ላይ በመመሰረት የተለያየ ሲሆን የአንድ ጤነኛ አዋቂ አማካይ የደም ግፊት መጠን 120 / 80 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሚርኮሪ (120 / 80 mmHg ) ነው።

   የደም ግፊት መጠን መጨመር በተለያዩ ሀገሮች ፣ የጤና ሙያ ማህበራት እና የጤና ማህከላት ውስጥ የተለያዩ መጠን ሊሰጠው ይችላል። የደም ግፊት መጠን የሚለካበት መሰፈሪያ ሚሊ ሜትር ኦፍ ሚርኮሪ ተብሎ ይጠራል። 

       እንደ አሜሪካ የልብ ማህበር መመሪያ መሰረት የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ ተከስቷል የሚባለው የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን በተደጋጋሚ ልኬት ከ 130 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ ( ≥ 130 mm Hg)  በላይ በሚሆንበት ወይም የዲያስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ከ 80 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ በላይ ( ≥ 80 mm Hg)  በሚሆንበት ወቅት ነው።

   አንደ ቡድን ስምንት ብሂራዊ የጥምረት ኮሜቲ (JNC 8) መመሪያ መሰረት ደግሞ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ ተከስቷል የሚባለው የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን በተደጋጋሚ ልኬት ከ 140 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ (≥ 140 mm Hg) በላይ  ሲሆን ወይም የዳያስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ከ 90 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ (≥ 90 mm Hg ) በላይ ሲሆን ነው።

 በልጆች (እድሜያቸው ከ 13 አመት በታች ) ላይ የደም ግፊት መጠን መጨመር ተከስቷል የሚባለው የደም ግፊት መጠን ከ  ≥ 95ኛው  ፐርሰንታይል ወይም የሴስቶሊክ የደም ግፊት መጠን ከ 130 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሚርኮሪ (≥ 130 mm Hg ) ወይም የዲያስቶለ‍ኢክ የደም ግፊት መጠን ከ 80 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ  (≥ 130 mm Hg )  በላይ ሲሆን ነው።

መንስሄው የማይታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር ( essential / primary hypertension) ፡ ለደም ግፊት መጠን መጨመር መንስሄ ወይም ምክንያት የሆነው ሆኔታ የማይታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ ዓይነት ነው። 

መንስሄው የሚታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር (Secondary hypertension)፡ ለደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ መፈጠር መንስሄ ወይም መነሻ ምክንያት በሚታወቅበት  ሆኔታ ውስጥ የሚከሰት የደም መጠን መጨመር በሽታ ዓይነት ነው።

የደም መጠን መጨመር በሽታን ለመቆጣጠር ለሚረዱ መድኃኒቶች ምላሽ የማይሰጥ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ (resistant hypertension) : ሦስት አና ከሦስት ዓይነት በላይ የተለያዩ መድኃኒቶችን በመጠቀም የደም ግፊት መጠንን መቆጣጠር የማይቻልበት ሆኔታ ወይም የደም ግፊት መጨመርን ለመቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶችን እየተጠቀሙ ነገር ግን የደም ግፊት መጠን ከ 130 / 80 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ (≥ 130/80 mm Hg) በላይ የሚሆንበት ሆኔታ ማለት ነው።

የደም ግፊት መጠን በተለያዩ ምደቦች ሊከፋፈል ይችላል። የደም ግፊት መጠን እየጨመረ በሄደ መጠን በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎቸ እና በእነዚህ የደም ቧንቧዎች  በኩል ደምን የሚቀበሉ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እየጨመረ ይመጣል። 

ምድብ

የአሜሪካን የልብ ማህበር (AHA)

ምድብ ስምንት ብሄራዊ የጥምረት ኮሜቲ (NJC 8)

ጤነኛ የደም ግፊት መጠን

የሲስቶሊክ  የደም   ግፊት መጠን < 120 mm Hg

 እና ዳያስቶሊክ   የደም ግፊት መጠን < 80 mm Hg

የደም ግፊት መጠን መጨመር

የሲስቶሊክ 120–129 mm Hg

እና የዲያስቶሊክ < 80 mm Hg

ሲስቶሊክ  120–139 mm Hg  ወይም ዳያስቶሊክ 80–89 mm Hg

አንደኛ ደረጃ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ (stage 1)

ሲስቶሊክ 130–139 mm Hg ወይም ዳያስቶሊክ  80–89 mm Hg

ሲስቶሊክ 140–159 mm Hg

ወይም  ዳያስቶሊክ 90–99 mm Hg

ሁለተኛ ደረጃ የደም ግፊት መጠን መጨመር

    (stage 2)

ሲስቶሊክ ≥ 140 mm Hg

ወይም ዳያስቶሊክ  ≥ 90 mm Hg

ሲስቶሊክ  ≥ 160 mm Hg

ወይም  ዳያስቶሊክ ≥ 100 mm Hg

መንስሄው የማይታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር ፡ መንስሄው ለማይታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሸታ መፈጠር የዘረ መል (genetic) እና አካባቢያዊ ሆኔታዎች (environmental factors) የጎላ ሚና እንደሚጫወቱ ይታመናል። 

  ለደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ በደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠረው የግድብት መጠን እና በየደቂቃው ከልብ የሚረጨው የደም መጠን ወሳኝ ሆኔታዎች ናቸው። በደም ቧንቧ ውስጥ የሚኖረው የግድብት (resistance) መጠን መጨመር ወይም / እና በየደቂቃው ከልብ የሚረጨው የደም መጠን ( cardiac out put) መጨመር አጠቃላይ የደም ግፊት መጠን መጨመር እንዲፈጠር ሊያደርጉ ይችላሉ። 

   መንስሄው ለማይታወቅ የደም መጠን መጨመር አጋላጭ ናቸው ተብለው የሚታመኑ ሆኔታዎችን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። እነሱም ሊቀየሩ የሚችሉ ለደም ግፊት መጠን መጨመር የሚያጋልጡ ሆኔታዎች እና ሊቀየሩ የማይችሉ ለደም ግፊት መጠን መጨመር አጋላጭ ሆኔታዎች ናቸው።

ሊቀየሩ የማይችሉ (non modifiable) ለደም ግፊት መጠን መጨመር አጋላጭ ሆኔታዎች ተብለው የሚጠቀሱት በቤተስብ ውስጥ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ ያለበት ሰው መኖር ፣ በዘር አፍሪካዊ መሆን እና የእድሜ መግፋት ናቸው ። 

  ሊቀየሩ ከሚችሉ (modifiable) ለደም ግፊት መጠን መጨመር አጋላጭ ሆኔታዎች መካከል ደግሞ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት ፣ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የስኳር በሽታ ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ሶዲየም እና ዝቅተኛ መጠን ያለው ፖታሲየም መመገብ  ፣  ሲጋራ ማጤስ ፣ ከመጠን ያለፈ የአልኮል መጠጥ መወሰድ ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ እንዲሁም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ተጠቃሽ አጋላጭ ሆኔታዎች ናቸው።

መንስሄው የሚታወቅ የደም ግፊት መጠን መጨምር እንዲፈጠር ከሚያደርጉ የጤና ችግሮች መካከል የታይሮድ ሆርሞን የጤና ችግር (የታይሮይድ ሆርሞን መጠን መጨመር ወይም መቀነስ)  ፣ መካከለኛ መጠን ያላቸው የደም ቧንቧዎች እንዲጠቡ የሚያደርግ በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰት የጤና ችግር (fibromuscular dysplasia) ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የአልዶስቲሮን ሆርሞን መጠን መጨመር ፣ ከአድሪናል ዕጢ የሚዶላ ክፍል ውሰጥ የሚመረቱ የካቲኮላማይን ሆርሞኖች ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መልኩ መመረት ፣ ከላይኛው የመተነፍሻ ቧንቧ መዘጋት ጋር በተገናኘ የሚከሰት የእንቅልፍ ችግር (obstructive sleep apnea እንዲሁም  የኩላሊት አርተሪ መጥበብ (renal artery stenosis) ዋነኞቹ ናቸው። 

  በኩላሊት ላይ የሚፈጠሩ የጤና ችግርች ፣ መካከለኛ መጠን ያላቸው የደም ቧንቧዎች እንዲጠቡ የሚያደርግ በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰት የጤና ችግር (fibromuscular dysplasia) እንዲሁም የትልቁ ደም ቅዳ የደም ቧንቧ መጥበብ (coarctation of the aorta) ዋንኞቹ በልጆች እና በወጣቶች ላይ የደም ግፊት መጨመር በሽታን የሚያስከትሉ የጤና ችግሮች ናቸው።