Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

14.1.4 የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ (coarctation of the Aorta)

    በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ የተነሳ በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ውስጥ የሚኖረው የደም ዘውውር ሂደት እንዲሰተጓል እና ወደታችኛው የሰውነት ከፍሎች የሚደርሰው የደም ፍሰት መጠን መቀነስ እንዲፈጠር የሚያደርግ የጤና ችግር የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ ወይም ኮአርክቴሽን ኦፍ አኦርታ (coarctation of the aorta) ተብሎ ይጠራል። ብዙህን ይህ በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ላይ የሚፈጠረው የትልቁ ደም ቧንቧ መጥበብ የሚከሰተው ከትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መታጠፊያ በታች እና የደክተስ አርተሪኦሰስ በሚገኘብት ክፍል ላይ ነው።  አንድ አንድ ግዜ የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ በሆድ ውስጥ ወደታች በሚወርደው የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ክፍል ላይም ሊከሰት ይችላል። 

   የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ መንሥሄ በትከክል የሚታወቅ ባይሆንም የትልቁ ደም ቅዳ በር ባለ ሦስት ካፕሲድ ከመሆን ይልቅ ባለ ሁለት ካፕሲድ ሆኖ ከመፈጠር ሆኔታ (Bicuspid aortic valve) እንዲሁም በዘረመል ወይም በክሮሞዞም ላይ ከሚከሰት ለውጥ ጋረደ በተገናኘ ከሚፈጠረው የተርነር ሲንድሮም (Turner’s  syndrome ጋር አብሮ ሊከሰት ይችላል።   

   የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ መከሰት የደክተስ አርተሪኦሰስ ማሻገሪያ ከሚገኝበት ክፍል አንጻር በሁለት ይከፈላል። እነዚህም ሁለት የትልቁ የደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ የጤና ችግር ዓይነቶች ከደክተስ አርተሪኦሰስ በፊት የሚከሰት የትልቁ ደም ቅዳ መጥበብ (preductal coarctation) እና ከደክተስ አርተሪኦሰስ በኋላ የሚከሰት የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ (postductal coarctation) ናችው ።

  ከደክተስ አርተሪኦሰስ በፊት የሚከሰት የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ ፡  የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ የሚፈጠረው ከደክተስ አርተሪኦሰስ በፊት ስለሆነ ጥበቱ ከተከሰተበት ክፍል በታች በኩል በሚገኘው የትልቁ ደም ቧንቧ ውስጥ የሚኖረው የግፊት መጠን ዝቀተኛ ይሆናል። ስለሆነም ከጥበቱ በኃላ በሚገኘው የትልቁ የደም ቧንቧ ውስጥ ከሚፈጠረው ዝቅተኛ ግፊት ዝቅተኛ ግፊት የተነሳ በዚህ ዓይነት የጤና ችግር የተጠቁ ህጻናት ላይ የደክተስ አርተሪኦሰስ ማሻገሪያ ክፍት እንደሆነ ይቆያል። ሰለሆነም ከቀኝ ቬንትሪክል የሚረጨው ያልተጣራ ደም ወደ ሳንባ ከመጓዝ ይልቅ በቀላሉ በቀጥታ በደክተስ አርተሪኦሰስ በኩል አልፎ ወደ ትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ውስጥ በመግባት ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚረጭ ይሆናል። በዚህም ምክንያት ህጻናቱ በሚወለዱበት ወቅት በቆዳ ላይ የሚታይ የቀለም ለውጥ እና ሌሎች ምልክቶች እና ለውጦች ሊታዩ ይችላሉ።

 ከደክተስ አርተሪኦሰስ በኋላ የሚከሰት የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ፡ ከደክተስ አርተሪኦሰስ በኋላ የሚከሰተው የትልቁ ደም ቅዳ መጥበብ በበዛት የሚከሰት የትልቁ ደም ቅዳ መጥበብ ዓይነት ነው ። በዚህ የጤና ችግር የተጠቁ ህጻናት ላይ በትልቁ የደም ቅዳ ቧንቧ ውሰጥ ከሚፈጠረው ከፍተኛ የግፊት መጠን የተነሳ የደክተስ አርተሪኦሰስ ማሻገሪያ የተዘጋ ስለሚሆን ከቀኝ ቬንትሪክል  በደክተስ አርተሪኦሰስ አልፎ  ወደ ትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ውስጥ የሚገባ ያልተጣራ ደም አይኖርም። 

 ከደከተስ አርተሪኦሰስ በኋላ የሚከሰት የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጠበብ ከሚከሰትበት ክፍል በላይ በሚገኝው የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ውስጥ የሚኖረው የግፊት መጠን ከፍተኛ ስለሚሆን ከትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ ከሚከሰትበት ክፍል በላይ በሚነሱ እና ደምን ወደ ላይኛው የሰውነት ክፍሎች በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚኖረው የደም እና የግፊት መጠን ከፍተኛ እንዲሆን ያደርጋል። በዚህም ምክንያት በላይኛው እና በታችኛው የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚገኘው የደም ግፊት መጠን እና ትርታ ወይም ግፊተ – ሞገድ የተለያየ እንዲሆን ያደርጋል። ስለሆነም  በሰውነት የላይኛው ክፍል ላይ ( በጭንቅላት ፧ በአንገት እና ክንድ) ከፍተኛ የደም ግፊት መጠን መጨመር የሚከሰተ ሲሆን በታችኛው የሰውነት ክፍል ላይ ደግሞ የደም ግፊት መጠን መቀነስ ሊከሰት ይችላል። 

በተጨማሪም በላይኛው የሰውነት ክፍሎች ጠንካራ ትርታ ወይም ግፊተ – ሞገድ የሚታይ ሲሆን በታችኛው የሰውነት ክፍሎች ላይ ደግሞ  ደካማ ትርታ ወይም ግፊተ  – ሞገድ ይኖራል።

  ከትልቁ የደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ ጋር በተገናኘ ወደታችኛው የሰውነት ክፍል ውስጥ የሚደርሰው የደም መጠን መቀነስን ተከትሎ ለታችኛው የሰውነት ክፍል በቂ የደም መጠን እንዲደረስ ለማድረግ በደረት እና በወገብ አካባቢ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች በደረት ውስጥ ከሚገኘው የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ክፍል ላይ ከሚነሱ የደም ቧንቧዎች ጋር በሚፈጠሩት ግንኙነት የተነሳ በወገብ እና በደረት የሰውነት ክፍል አካባቢ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች በመጠን እንዲጨምሩ ወይም እንዲገታተሩ ያደርጋል።

  ይህ ዓይነት የትልቁ የደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ በላይኛው የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ውስጥ በሚፈጥረው ከፍተኛ የደም ግፊት መጠን መጨመር የተነሳ ለልብ ድካም ፣ በአንጎል ውስጥ ለሚፈጠር ደም መፍሰስ ፣ ለትልቁ የደም ቅዳ ቧንቧ ግድግዳ መቀደድ (aortic rupture) እንዲሁም በልብ የውስጠኛ  ክፍሎች እና በልብ በሮች ላይ ለሚፈጠር ኢንፌክሽን (endocarditis) ተጋላጭነት እንዲጨምር ያደርጋል። 

  ከትልቁ የደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ ምልክቶችን እና ለውጦችን ለመቆጣጠር ወይም ለማከም የፕሮስታግላንዲን ሆርሞንን በመድኃኒት  መልክ መጠቀም ፣ በቀዶ ጥገና ወይም በጠበበው የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ውስጥ ካቴተር ወይም ቀጭን ቧንቧ መስል በማሳለፍ የጠበበውን የትልቅ ደም ቅዳ ቧንቧ ማስፋት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። 

      የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ ሳይታከም ለረጀም ግዜ በሚቆይበት ወቅት ሊፈጠሩ ከሚችሉ ሆኔታዎች መካከል በላይኛው የሰውነት ክፍል ላይ የደም ግፊት መጠን መጨመር ፣ የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ግድግዳ መስንጠቅ ወይም መቀደድ ፣ በትልቁ ደም ቧንቧ እና በሌሎች የሰውነት ክፍሎች በተለይም በአንጎል ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ መለጠጥ እና መስርጎድ ( aneurysm) ፣ የልብ ድካም በሽታ እንዲሁም በልብ የወስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን  ዋንኞቹ ናቸው።